Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ነገሥት 13:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 እር​ሱም፥ “እኔ ደግሞ እን​ዳ​ንተ ነቢይ ነኝ፤ መል​አ​ክም፦ እን​ጀራ ይበላ ዘንድ ውኃም ይጠጣ ዘንድ ከአ​ንተ ጋር ወደ ቤትህ መል​ሰው ብሎ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ተና​ገ​ረኝ” አለው። ዋሽ​ቶም ተና​ገ​ረው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ሽማግሌው ነቢይ ግን፣ “እኔም እኮ እንደ አንተው ነቢይ ነኝ፤ መልአክ በእግዚአብሔር ቃል፣ ‘እንጀራ እንዲበላና ውሃ እንዲጠጣ መልሰህ ወደ ቤትህ አምጣው’ ብሎኝ ነው” አለው፤ ነገር ግን ውሸቱን ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ከዚህ በኋላ ከቤትኤል የመጣው ሽማግሌ ነቢይ “እኔም እንዳንተው ነቢይ ነኝ፤ ከእኔ ጋር ወደ ቤቴ ወስጄ እንዳስተናግድህ ከጌታ የታዘዘ መልአክ ነግሮኛል” አለው፤ ነገር ግን ዋሽቶ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 ከዚህ በኋላ ከቤትኤል የመጣው ሽማግሌ ነቢይ “እኔም እንዳንተው ነቢይ ነኝ፤ ከእኔ ጋር ወደ ቤቴ ወስጄ እንዳስተናግድህ ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክ ነግሮኛል” አለው፤ ሽማግሌው ነቢይ የተናገረው ግን በመዋሸት ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 እርሱም “እኔ ደግሞ እንደ አንተ ነቢይ ነኝ፤ መልአክም ‘እንጀራ ይበላ ዘንድ ውሃም ይጠጣ ዘንድ ከአንተ ጋር ወደ ቤትህ መልሰው፤’ ብሎ በእግዚአብሔር ቃል ተናገረኝ፤” አለው። ዋሽቶም ተናገረው።

Ver Capítulo Copiar




1 ነገሥት 13:18
36 Referencias Cruzadas  

አለ​ውም፥ “አንተ ልጄ ዔሳው ነህን?” እር​ሱም፥ “እኔ ነኝ” አለ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክም ሴቲ​ቱን፥ “ይህን ለምን አደ​ረ​ግሽ?” አላት። ሴቲ​ቱም አለች፥ “እባብ አሳ​ተ​ኝና በላሁ።”


መለ​ሰ​ውም፥ በቤ​ቱም እን​ጀራ በላ፤ ውኃም ጠጣ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፦ በምን ታስ​ተ​ዋ​ለህ? አለው፤ እር​ሱም ወጥቼ በነ​ቢ​ያቱ ሁሉ አፍ ሐሰ​ተኛ መን​ፈስ እሆ​ና​ለሁ አለ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፦ ማሳ​ሳ​ትስ ታሳ​ስ​ተ​ዋ​ለህ፤ ይሆ​ን​ል​ሃ​ልም፤ ውጣ፤ እን​ዲ​ሁም አድ​ርግ አለ።


የጻድቃን ከንፈሮች ምስክርነትን ያቀናሉ፥ የሚቸኩል ምስክር ግን ክፉ አንደበት አለው።


ሐሰተኛ ከንፈር በእግዚአብሔር ዘንድ አስጸያፊ ነው፤ እውነትን የሚያደርጉ ግን በእርሱ ዘንድ የተወደዱ ናቸው።


ሐሰተኛ ምስክር ሳይቀጣ አይቀርም፥ በግፍዕ የሚከስም አያመልጥም።


አሁ​ንም በውኑ ያለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትእ​ዛዝ እና​ጠ​ፋ​ችሁ ዘንድ ወደ​ዚህ ሀገር ዘም​ተ​ና​ልን? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፦ ወደ ሀገ​ራ​ቸው ዘም​ታ​ችሁ አጥ​ፉ​አ​ቸው” አለን።


ሽማ​ግ​ሌ​ውና ለፊት የሚ​ያ​ደ​ላው እርሱ ራስ ነው፤ ዐመ​ፅ​ንም የሚ​ያ​ስ​ተ​ምር ነቢይ እርሱ ጅራት ነው።


በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ነቢ​ያት ላይ የሚ​ያ​ስ​ደ​ነ​ግ​ጥን ነገር አይ​ቻ​ለሁ፤ ያመ​ነ​ዝ​ራሉ፤ በሐ​ሰ​ትም ይሄ​ዳሉ፤ ማንም ከክ​ፋቱ እን​ዳ​ይ​መ​ለስ የክፉ አድ​ራ​ጊ​ዎ​ችን እጅ ያበ​ረ​ታሉ፤ ሁሉም እንደ ሰዶም፥ የሚ​ኖ​ሩ​ባ​ትም እንደ ገሞራ ሆኑ​ብኝ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ለሚ​ያ​ቃ​ልሉ ሰላም ይሆ​ን​ላ​ች​ኋል፥ በፍ​ላ​ጎ​ታ​ቸ​ውና በል​ቡ​ና​ቸው ክፋት ለሚ​ሄ​ዱም ሁሉ፦ ክፉ ነገር አያ​ገ​ኛ​ች​ሁም” ይላሉ።


እነሆ ሐሰ​ትን በሚ​ያ​ልሙ፥ በሚ​ና​ገ​ሩም፥ በሐ​ሰ​ታ​ቸ​ውና በድ​ፍ​ረ​ታ​ቸ​ውም ሕዝ​ቤን በሚ​ያ​ስቱ በነ​ቢ​ያት ላይ ነኝ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ እኔም አል​ላ​ክ​ኋ​ቸ​ውም፤ አላ​ዘ​ዝ​ኋ​ቸ​ው​ምም፤ ለእ​ነ​ዚህ ሕዝብ በማ​ና​ቸ​ውም አይ​ረ​ቡ​አ​ቸ​ውም፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ አሔ​ል​ማ​ዊው ስለ ሸማያ እን​ዲህ ይላል ብለህ ወደ ምር​ኮ​ኞች ሁሉ ላክ፦ እኔ ሳል​ል​ከው ሸማያ ትን​ቢት ተና​ግ​ሮ​ላ​ች​ኋ​ልና፥ በሐ​ሰ​ትም እን​ድ​ት​ታ​መኑ አድ​ር​ጓ​ች​ኋ​ልና።


ስለ​ዚህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ አሔ​ል​ማ​ዊ​ውን ሸማ​ያ​ንና ዘሩን እቀ​ጣ​ለሁ፤ እኔም ለሕ​ዝቤ የማ​ደ​ር​ገ​ውን መል​ካ​ሙን ነገር የሚ​ያይ ሰው በመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ አይ​ኖ​ር​ላ​ቸ​ውም፤ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ ዐመ​ፃን ተና​ግ​ሮ​አ​ልና።”


የይ​ሁ​ዳም ወገ​ኖች በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዋሹ፤ እን​ዲ​ህም አሉ፥ “እን​ደ​ዚህ አይ​ደ​ለም፤ ክፉ ነገ​ርም አይ​መ​ጣ​ብ​ንም ሰይ​ፍ​ንና ራብ​ንም አና​ይም፤


ነቢ​ያት በሐ​ሰት ትን​ቢት ይና​ገ​ራሉ፥ ካህ​ና​ትም በእ​ጃ​ቸው ያጨ​በ​ጭ​ባሉ፥ ሕዝ​ቤም እን​ዲህ ያለ​ውን ነገር ይወ​ድ​ዳሉ፤ በፍ​ጻ​ሜ​ውስ ምን ታደ​ር​ጋ​ላ​ችሁ?


እኔም ያል​መ​ለ​ስ​ሁ​ትን የጻ​ድ​ቁን ልብ ወደ ዐመፃ መል​ሳ​ች​ኋ​ልና፥ በሕ​ይ​ወ​ትም ይኖር ዘንድ ከክፉ መን​ገድ እን​ዳ​ይ​መ​ለስ የኀ​ጢ​አ​ተ​ኛ​ውን እጅ አበ​ር​ት​ታ​ች​ኋ​ልና፤


ስለ​ዚህ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ከንቱ ነገ​ርን ስለ ተና​ገ​ራ​ችሁ፥ ሐሰ​ተኛ ራእ​ይ​ንም ስለ አያ​ችሁ፥ ስለ​ዚህ እነሆ እኔ በእ​ና​ንተ ላይ ነኝ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


የእ​ግ​ዚ​እ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ በለ​ዓ​ምን፥ “ከሰ​ዎቹ ጋር ሂድ፤ ነገር ግን የም​ና​ገ​ር​ህን ቃል ብቻ ለመ​ና​ገር ተጠ​ን​ቀቅ” አለው። በለ​ዓ​ምም ከባ​ላቅ አለ​ቆች ጋር ሄደ።


ሐሰተኞች ክርስቶሶችና ሐሰተኞች ነቢያት ይነሣሉና፤ ቢቻላቸውስ የተመረጡትን እንኳ እስኪያስቱ ድረስ ታላላቅ ምልክትና ድንቅ ያሳያሉ።


“የበግ ለምድ ለብሰው ከሚመጡባችሁ በውስጣቸው ግን ነጣቂዎች ተኵላዎች ከሆኑ ከሐሰተኞች ነቢያት ተጠንቀቁ።


እነ​ርሱ ለጌ​ታ​ችን ለኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ያይ​ደለ ለሆ​ዳ​ቸው ይገ​ዛ​ሉና፤ በነ​ገር ማታ​ለ​ልና በማ​ለ​ዛ​ዘ​ብም የብ​ዙ​ዎች የዋ​ሃ​ንን ልብ ያስ​ታሉ፤


ነገር ግን እባብ ሔዋ​ንን በተ​ን​ኰሉ እን​ዳ​ሳ​ታት፥ አሳ​ባ​ችሁ ከክ​ር​ስ​ቶስ የዋ​ህ​ነ​ትና ንጽ​ሕና ምና​ል​ባት እን​ዳ​ይ​ለ​ወጥ ብዬ እፈ​ራ​ለሁ።


እና​ንተ ግን የእ​ኛን ፍለጋ ተከ​ተሉ፤ እና​ን​ተስ እኛም ብን​ሆን ወይም መል​አክ ከሰ​ማይ ወርዶ እኛ ካስ​ተ​ማ​ር​ና​ችሁ ወን​ጌል ሌላ ቢሰ​ብ​ክ​ላ​ችሁ ውጉዝ ይሁን።


መንፈስ ግን በግልጥ “በኋለኞች ዘመናት አንዳንዶች የሚያስቱ መናፍስትንና በውሸተኞች ግብዝነት የተሰጠውን የአጋንንትን ትምህርት እያደመጡ፥ ሃይማኖትን ይክዳሉ፤” ይላል፤ በገዛ ሕሊናቸው እንደሚቃጠሉ ደንዝዘው፥


ነገር ግን ሐሰተኞች ነቢያት ደግሞ በሕዝቡ መካከል ነበሩ፤ እንዲሁም በመካከላችሁ ደግሞ ሐሰተኞች አስተማሪዎች ይሆናሉ፤ እነርሱም የዋጃቸውን ጌታ እንኳ ክደው የሚፈጥንን ጥፋት በራሳቸው ላይ እየሳቡ የሚያጠፋ ኑፋቄን አሹልከው ያገባሉ፤


ወዳጆች ሆይ፥ መንፈስን ሁሉ አትመኑ፥ ነገር ግን መናፍስት ከእግዚአብሔር ሆነው እንደ ሆነ መርምሩ፤ ብዙዎች ሐሰተኞች ነቢያት ወደ ዓለም ወጥተዋልና።


አውሬውም ተያዘ፤ በእርሱም ፊት ተአምራትን እያደረገ የአውሬውን ምልክት የተቀበሉትን ለምስሉም የሰገዱትን ያሳተ ሐሰተኛው ነቢይ ከእርሱ ጋር ተያዘ፤ ሁለቱም በሕይወት ሳሉ በዲን ወደሚቃጠል ወደ እሳት ባሕር ተጣሉ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ ለሴ​ቲቱ ተገ​ልጦ እን​ዲህ አላት፥ “እነሆ፥ አንቺ መካን ነሽ፤ ልጅም አል​ወ​ለ​ድ​ሽም፤ ነገር ግን ትፀ​ን​ሻ​ለሽ፤ ወንድ ልጅም ትወ​ል​ጃ​ለሽ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos