Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዮናስ 1:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 እነ​ዚ​ያም ሰዎች ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እንደ ኰበ​ለለ እርሱ ስለ ነገ​ራ​ቸው ዐው​ቀ​ዋ​ልና እጅግ ፈር​ተው፥ “ይህ ያደ​ረ​ግ​ኸው ምን​ድን ነው?” አሉት።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 እርሱ አስቀድሞ ነግሯቸው ስለ ነበር፣ ከእግዚአብሔር እንደ ኰበለለ ዐወቁ፣ ስለዚህም በሁኔታው በመደንገጥ፣ “ይህ ያደረግኸው ምንድን ነው?” አሉት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ሰዎቹም እጅግ ፈሩ፥ እንዲህም አሉት፦ “ይህ ያደረግኸው ምንድነው?” እርሱ ስለ ነገራቸው፥ ከጌታ ፊት እንደ ኰበለለ አውቀዋልና።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 አስቀድሞ በነገራቸው መሠረት ዮናስ ከእግዚአብሔር ፊት የኰበለለ መሆኑን ዐወቁ፤ ስለዚህም በጣም ፈርተው “ይህን ያደረግኸው ለምንድን ነው?” አሉት።

Ver Capítulo Copiar




ዮናስ 1:10
8 Referencias Cruzadas  

ዮናስ ግን ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ወደ ተር​ሴስ ይሸሽ ዘንድ ተነሣ፤ ወደ ኢዮ​ጴም ወረደ፤ ወደ ተር​ሴ​ስም የም​ታ​ልፍ መር​ከብ አገኘ፤ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ኰብ​ልሎ ከእ​ነ​ርሱ ጋር ወደ ተር​ሴስ ይሄድ ዘንድ ዋጋ ሰጥቶ ወደ እር​ስዋ ገባ።


በእ​ር​ሱም ላይ የማ​ያ​ው​ቀው ይመ​ጣ​በ​ታል፤ አይ​ራ​ራ​ለ​ትም፥ ከእ​ጁም ፈጥኖ መሸሽ ይወ​ድ​ዳል።


ጲላ​ጦ​ስም ይህን ነገር ሰምቶ እጅግ ፈራ።


ኢዮ​አ​ብም ንጉ​ሡን፥ “የጌ​ታዬ የን​ጉሡ ዐይን እያየ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዛሬ ካለው ሕዝብ መጠን በላይ መቶ እጥፍ ይጨ​ም​ር​በት፤ ጌታዬ ንጉሡ ግን ይህን ነገር ለምን ይፈ​ል​ጋል?” አለው።


ኢያ​ሱም፥ “ለምን አጠ​ፋ​ኸን? ዛሬ እን​ዳ​ጠ​ፋ​ኸን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዛሬ ያጥ​ፋህ” አለው፤ እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ በድ​ን​ጋይ ወገ​ሩት፤ በእ​ሳ​ትም አቃ​ጠ​ሉት፤ በድ​ን​ጋ​ይም ወገ​ሩ​አ​ቸው።


ባሕሩ ይታ​ወክ ነበ​ርና፥ ታላቅ ማዕ​በ​ልም ተነ​ሥቶ ነበ​ርና፥ “ባሕሩ ጸጥ ይል​ልን ዘንድ እን​ግ​ዲህ ምን እና​ድ​ር​ግህ?” አሉት።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክም ሴቲ​ቱን፥ “ይህን ለምን አደ​ረ​ግሽ?” አላት። ሴቲ​ቱም አለች፥ “እባብ አሳ​ተ​ኝና በላሁ።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios