ከዚያም በቤቴል ምሥራቅ ወዳለው ተራራ ወጣ፤ በዚያም ቤቴልን ወደ ምዕራብ፥ ጋይን ወደ ምሥራቅ አድርጎ ድንኳኑን ተከለ፤ በዚያም ለእግዚአብሔር መሠውያን ሠራ፤ የእግዚአብሔርንም ስም ጠራ።
ዘፍጥረት 28:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያዕቆብም ያን ስፍራ ቤቴል ብሎ ጠራው፤ አስቀድሞ ግን የዚያ ከተማ ስም ሎዛ ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ያን ቦታ ቤቴል ብሎ ሰየመው፤ ቀደም ሲል ግን የከተማዪቱ ስም ሎዛ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ያዕቆብም ያንን ስፍራ ቤቴል ብሎ ጠራው፥ አስቀድሞ ግን የዚያች ከተማ ስም ሎዛ ነበረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ያንንም ስፍራ “ቤትኤል” ብሎ ሰየመው፤ ይህ ስፍራ ከዚያ በፊት ሎዛ እየተባለ ይጠራ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ያዕቆብም ይንን ስፍራ ቤቴል ብሎ ጠራው አስቀድሞ ግን የዚያች ከተማ ስም ሎዛ ነበረ። |
ከዚያም በቤቴል ምሥራቅ ወዳለው ተራራ ወጣ፤ በዚያም ቤቴልን ወደ ምዕራብ፥ ጋይን ወደ ምሥራቅ አድርጎ ድንኳኑን ተከለ፤ በዚያም ለእግዚአብሔር መሠውያን ሠራ፤ የእግዚአብሔርንም ስም ጠራ።
ወደ አንድ ስፍራም ደረሰ፤ ፀሐይም ጠልቃ ነበርና በዚያ አደረ፤ ከዚያም ስፍራ ድንጋዮች አንድ ድንጋይ አነሣ፤ ከራሱም በታች ተንተርሶ በዚያ ስፍራ ተኛ።
ሐውልቱን ዘይት በቀባህባት፥ በዚያች ለእኔ ስእለት በተሳልህባት ሀገር የተገለጥሁልህ ፈጣሪህ እግዚአብሔር እኔ ነኝ። አሁንም ተነሥተህ ከዚህ ሀገር ውጣ፤ ወደ ተወለድህባትም ምድር ተመለስ፤ እኔም ከአንተ ጋር እኖራለሁ።”
እግዚአብሔርም ያዕቆብን አለው፥ “ተነሥተህ ወደ ቤቴል ውጣ፤ በዚያም ኑር፤ ከወንድምህ ከዔሳው ፊት በሸሸህ ጊዜ ለተገለጥሁልህ ለእኔ መሥውያን ሥራ።”
ያዕቆብም እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር በተነጋገረበት ቦታ የድንጋይ ሐውልት ተከለ፤ የመጠጥ መሥዋዕትንም በእርሱ ላይ አፈሰሰ፤ ዘይትንም አፈሰሰበት።
በዚያም መሠውያዉን ሠራ፤ የዚያንም ቦታ ስም ቤቴል ብሎ ጠራው፤ እርሱ ከወንድሙ ከዔሳው ፊት በሸሸበት ጊዜ እግዚአብሔር በዚያ ተገልጦለት ነበርና።
ኤልያስም ኤልሳዕን፥ “እግዚአብሔር ወደ ቤቴል ልኮኛልና በዚሁ ቈይ” አለው። ኤልሳዕም፥ “ሕያው እግዚአብሔርን! ሕያው ነፍስህንም አልለይህም” አለው። ወደ ቤቴልም ደረሱ።
አብያም ኢዮርብዓምን ተከትሎ አሳደደው፤ ከእርሱም ከተሞቹን ቤቴልንና መንደሮችዋን፥ ይሳናንና መንደሮችዋን፥ ዔፍሮንንና መንደሮችዋን ወሰደ።
እስራኤል ሆይ! አንተ አላዋቂ አትሁን፤ አንተም ይሁዳ! ወደ ጌልጌላ አትሂድ፤ ወደ ቤትአዊንም አትውጡ፤ በሕያው እግዚአብሔርም አትማሉ።
ድንበሩም ከዚያ በደቡብ በኩል ቤቴል ወደምትባል ወደ ሎዛ ዐለፈ፤ ድንበሩም በታችኛው ቤቶሮን ደቡብ በኩል ባለው ተራራ ወደ ማአጣሮቶሬክ ወረደ።
የእስራኤልም ልጆች ሁሉ ሕዝቡም ሁሉ ወጥተው ወደ ቤቴል መጡ፤ አለቀሱም፤ በዚያም በእግዚአብሔር ፊት ተቀመጡ፤ በዚያም ቀን እስከ ማታ ድረስ ጾሙ፤ በእግዚአብሔርም ፊት የሚቃጠል መሥዋዕትንና የደኅንነት መሥዋዕትን አቀረቡ።
ከዚያም ደግሞ አልፈህ፥ ወደ ትልቁ የታቦር ዛፍ ትደርሳለህ፤ በዚያም ሦስት ሰዎች፥ አንዱ ሦስት የፍየል ጠቦቶች ሲነዳ፥ ሁለተኛው ሦስት የዳቦ ስልቻ፥ ሦስተኛውም የወይን ጠጅ አቁማዳ ይዘው ወደ እግዚአብሔር ወደ ቤቴል ሲወጡ ታገኛለህ፤
በየዓመቱም ወደ ቤቴል፥ ወደ ጌልጌላና ወደ መሴፋ ይዞር ነበር፤ በእነዚያም በተቀደሱ ስፍራዎች ሁሉ በእስራኤል ላይ ይፈርድ ነበር።