Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ዜና መዋዕል 13:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 አብ​ያም ኢዮ​ር​ብ​ዓ​ምን ተከ​ትሎ አሳ​ደ​ደው፤ ከእ​ር​ሱም ከተ​ሞ​ቹን ቤቴ​ል​ንና መን​ደ​ሮ​ች​ዋን፥ ይሳ​ና​ንና መን​ደ​ሮ​ች​ዋን፥ ዔፍ​ሮ​ን​ንና መን​ደ​ሮ​ች​ዋን ወሰደ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 አብያም ኢዮርብዓምን አሳድዶ የቤቴልን፣ የይሻናንና የዔፍሮንን ከተሞች ከነመንደሮቻቸው ወሰደበት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 አብያም ኢዮርብዓምን አሳደደው፥ ከእርሱም ከተሞቹን፥ ቤቴልንና መንደሮችዋን፥ ይሻናንና መንደሮችዋን፥ ዔፍሮንንና መንደሮችዋን ወሰደ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 አቢያ የኢዮርብዓምን ሠራዊት አሳደደ፤ ከኢዮርብዓም ከተማዎች መካከልም ቤትኤልን፥ ይሻናንና ዔፍሮንን በአካባቢያቸው የሚገኙትን መንደሮች ጭምር በድል አድራጊነት ያዘ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 አብያም ኢዮርብዓምን አሳደደው፤ ከእርሱም ከተሞቹን ቤቴልንና መንደሮችዋን፥ ይሻናንና መንደሮችዋን፥ ዔፍሮንንና መንደሮችዋን ወሰደ።

Ver Capítulo Copiar




2 ዜና መዋዕል 13:19
11 Referencias Cruzadas  

ያዕ​ቆ​ብም ያን ስፍራ ቤቴል ብሎ ጠራው፤ አስ​ቀ​ድሞ ግን የዚያ ከተማ ስም ሎዛ ነበረ።


በዚ​ያም ጊዜ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ተዋ​ረዱ፤ የይ​ሁ​ዳም ልጆች በአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው አም​ላክ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታም​ነው ነበ​ርና አሸ​ነፉ።


ኢዮ​ር​ብ​ዓ​ምም ከዚያ በኋላ በአ​ብያ ዘመን አል​በ​ረ​ታም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቀሠ​ፈው፤ ሞተም።


አሳም ይህን ቃልና የነ​ቢ​ዩን የአ​ዳ​ድን ልጅ የአ​ዛ​ር​ያ​ስን ትን​ቢት በሰማ ጊዜ ጸና፤ ከይ​ሁ​ዳና ከብ​ን​ያ​ምም ሀገር ሁሉ በተ​ራ​ራ​ማው በኤ​ፍ​ሬም ሀገር ከያ​ዛ​ቸው ከተ​ሞች ርኵ​ሰ​ትን ሁሉ አስ​ወ​ገደ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት ፊት የነ​በ​ረ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መሠ​ዊያ አደሰ።


በተ​መ​ሸ​ጉ​ትም በይ​ሁዳ ከተ​ሞች ሁሉ ሠራ​ዊ​ቱን አኖረ፤ በይ​ሁ​ዳም ሀገር፥ አባ​ቱም አሳ በወ​ሰ​ዳ​ቸው በኤ​ፍ​ሬም ከተ​ሞች መሳ​ፍ​ን​ቱን አስ​ቀ​መጠ።


ከዚ​ያም ወዲያ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ በአ​ይ​ሁድ መካ​ከል በግ​ልጥ አል​ተ​መ​ላ​ለ​ሰም፤ ነገር ግን ለም​ድረ በዳ አቅ​ራ​ቢያ ወደ ሆነች ምድር፥ ኤፍ​ሬም ወደ​ም​ት​ባል ከተማ ሄደ፤ በዚ​ያም ከደቀ መዛ​ሙ​ርቱ ጋር ተቀ​መጠ።


እና​ንተ ግን አት​ዘ​ግዩ፤ ጠላ​ቶ​ቻ​ች​ሁ​ንም እስከ መጨ​ረ​ሻው ተከ​ታ​ት​ላ​ችሁ ያዙ​አ​ቸው፤ አም​ላ​ካ​ች​ሁም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ጃ​ችሁ አሳ​ልፎ ሰጥ​ቶ​አ​ቸ​ዋ​ልና ወደ ከተ​ሞ​ቻ​ቸው እን​ዳ​ይ​ገቡ ከል​ክ​ሉ​አ​ቸው፤” አለ።


እር​ስ​ዋ​ንም፥ ንጉ​ሥ​ዋ​ንም፥ ከተ​ሞ​ች​ዋ​ንም ያዙ፤ በሰ​ይ​ፍም ስለት መቱ​አ​ቸው፤ በእ​ነ​ር​ሱም ውስጥ ያሉ​ትን ነፍ​ሳት ሁሉ ፈጽ​መው አጠፉ፤ ማን​ንም አላ​ስ​ቀ​ረም፤ በኬ​ብ​ሮ​ንና በን​ጉ​ሥ​ዋም እን​ዳ​ደ​ረ​ገው እን​ዲሁ በዳ​ቤ​ርና በን​ጉ​ሥዋ አደ​ረገ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አገ​ል​ጋይ ሙሴ እን​ዳ​ዘ​ዘው፥ ኢያሱ የእ​ነ​ዚ​ህን መን​ግ​ሥ​ታት ከተ​ሞች ሁሉ፥ ንጉ​ሦ​ቻ​ቸ​ው​ንም ሁሉ ያዘ፤ በሰ​ይ​ፍም መታ​ቸው፤ ፈጽ​ሞም አጠ​ፋ​ቸው።


ድን​በ​ሩም ከተ​ራ​ራው ራስ ወደ ኔፍቶ ውኃ ምንጭ ይሄ​ዳል፤ ወደ ዔፍ​ሮ​ንም ተራራ ይደ​ር​ሳል፤ ወደ ኢያ​ሪም ከተማ ወደ በኣላ ይደ​ር​ሳል።


በሸ​ለ​ቆ​ውም ማዶና በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ የነ​በሩ እስ​ራ​ኤ​ላ​ው​ያን የእ​ስ​ራ​ኤል ሰዎች እንደ ሸሹ፥ ሳኦ​ልና ልጆ​ቹም እንደ ሞቱ ባዩ ጊዜ ከተ​ሞ​ቹን ለቅ​ቀው ሸሹ፤ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም መጥ​ተው ተቀ​መ​ጡ​ባ​ቸው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos