Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -


ኢያሱ 16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)


ለኤ​ፍ​ሬ​ምና ለም​ናሴ ነገድ እኩ​ሌታ የተ​ሰጠ ርስት

1 የዮ​ሴ​ፍም ልጆች ድን​በ​ራ​ቸው በኢ​ያ​ሪኮ አን​ጻር በም​ሥ​ራቅ በኩል ካለው ከዮ​ር​ዳ​ኖስ አን​ሥቶ በም​ድረ በዳ​ውና በተ​ራ​ራ​ማው በኩል ከኢ​ያ​ሪኮ ሎዛ ትባል ወደ ነበ​ረ​ችው ቤቴል ይደ​ር​ሳል፤

2 ከቤ​ቴል ሎዛም በከ​ሮ​ንቲ ዳርቻ በኩል ወደ አጣ​ሮት አው​ራጃ ይደ​ር​ሳል፤

3 ወደ ምዕ​ራ​ብም እስከ የፍ​ሌ​ጣ​ው​ያን ዳርቻ እስከ ታች​ኛው ቤቶ​ሮን ዳርቻ ድረስ ይወ​ር​ዳል፤ መው​ጫ​ውም በባ​ሕሩ አጠ​ገብ ነበረ።

4 የዮ​ሴ​ፍም ልጆች ምና​ሴና ኤፍ​ሬም ርስ​ታ​ቸ​ውን ወረሱ።


የኤ​ፍ​ሬም ልጆች ርስት

5 የኤ​ፍ​ሬ​ምም ልጆች ድን​በር በየ​ወ​ገ​ኖ​ቻ​ቸው እን​ደ​ዚህ ነበረ፤ የር​ስ​ታ​ቸው ድን​በር ከአ​ጣ​ሮ​ትና፥ ከኤ​ሮሕ ምሥ​ራቅ ከጋ​ዛራ እስከ ላይ​ኛው ቤቶ​ሮን ድረስ ነበረ፤

6 ድን​በ​ሩም ወደ ምዕ​ራብ ወደ አካ​ስ​ሞን በቴ​ርማ ሰሜን ያል​ፋል፤ ወደ ምሥ​ራ​ቅም ወደ ቲና​ስና ሴላስ ይዞ​ራል፥ ከም​ሥ​ራ​ቅም ወደ ኢያ​ኖክ ያል​ፋል።

7 ከኢ​ያ​ኖ​ክም ወደ መአ​ኮና፥ ወደ አጣ​ሮ​ትም፥ ወደ መን​ደ​ሮ​ቻ​ቸ​ውም ያል​ፋል፤ ወደ ኢያ​ሪ​ኮም ይገ​ባል፥ ወደ ዮር​ዳ​ኖ​ስም ይወ​ጣል።

8 ድን​በ​ሩም ከጣፉ ወደ ባሕር እስከ ኬል​ቃን ወንዝ ድረስ ያል​ፋል፥ መው​ጫ​ውም በባ​ሕሩ አጠ​ገብ ነበረ። የኤ​ፍ​ሬም ልጆች ነገድ ርስት በየ​ወ​ገ​ኖ​ቻ​ቸው ይህ ነበረ።

9 ይኸ​ውም በም​ናሴ ልጆች ርስት መካ​ከል ለኤ​ፍ​ሬም ልጆች ከተ​ለዩ ከተ​ሞች ጋር፥ ከተ​ሞች ሁሉ ከመ​ን​ደ​ሮ​ቻ​ቸው ጋር ነው።

10 በጋ​ዜ​ርም የተ​ቀ​መ​ጡ​ትን ከነ​ዓ​ና​ው​ያ​ንን ኤፍ​ሬም አላ​ጠ​ፋ​ቸ​ውም፤ እስከ ዛሬም ድረስ ከነ​ዓ​ና​ው​ያን በኤ​ፍ​ሬም መካ​ከል ተቀ​ም​ጠ​ዋል፤ ገባ​ርም ሆኑ።

Síguenos en:



Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos