ለርብቃም ታላቁ ልጅዋ ዔሳው ያለው ተነገራት፤ ታናሹን ልጅዋን ያዕቆብንም ልካ ጠራችው፤ አለችውም፥ “እነሆ ወንድምህ ዔሳው ያድድንሃል፤ ሊገድልህም ይፈልጋል።
ዘፍጥረት 27:41 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዔሳውም አባቱ ስለ ባረከው በያዕቆብ ቂም ያዘበት፤ ዔሳውም በልቡ አለ፥ “ለአባቴ የልቅሶ ቀን ትቅረብ፤ ወንድሜን ያዕቆብን እገድለዋለሁ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም አባቱ ያዕቆብን ስለ መረቀው፣ ዔሳው በያዕቆብ ላይ ቂም ያዘ፤ በልቡም፣ “ግድ የለም፤ የአባቴ መሞቻው ተቃርቧል፤ ከልቅሶው በኋላ ወንድሜን ያዕቆብን እገድላለሁ” ብሎ ዐሰበ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዔሳውም አባቱ ስለ ባረከው በያዕቆብ ቂም ያዘበት፥ ዔሳውም በልቡ አለ፦ “ለአባቴ የልቅሶ ቀን ቀርቦአል፥ ከዚያም በኋላ ወንድሜን ያዕቆብን እገድለዋለሁ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አባቱ ስለ መረቀው ዔሳው ያዕቆብን አጥብቆ ጠላው፤ በልቡም “አባቴ በቅርብ ቀን ይሞታል፤ ከዚያ በኋላ ወንድሜን ያዕቆብን እገድለዋለሁ” ብሎ አሰበ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዔሳው፥ አባቱ ስለ ባረከው በያዕቆብ ቂም ያዘበት ዔሳውም በልቡ አለ፦ ለአባቴ የልቅሶ ቀን ቀርቦአል ከዚያም በኍላ ወንድሜን ያዕቆብን እገድለዋለሁ። |
ለርብቃም ታላቁ ልጅዋ ዔሳው ያለው ተነገራት፤ ታናሹን ልጅዋን ያዕቆብንም ልካ ጠራችው፤ አለችውም፥ “እነሆ ወንድምህ ዔሳው ያድድንሃል፤ ሊገድልህም ይፈልጋል።
አቤቱ ከወንድሜ ከዔሳው እጅ አድነኝ፤ መጥቶ እንዳያጠፋኝ፥ እናትን ከልጆችዋ ጋር እንዳያጠፋ እኔ እፈራዋለሁና።
የላካቸው መልእክተኞችም ወደ ያዕቆብ ተመልሰው እንዲህ አሉት፥ “ወደ ወንድምህ ወደ ዔሳው ሄደን ነበር፤ እርሱም ደግሞ ሊቀበልህ ይመጣል፤ ከእርሱም ጋር አራት መቶ ሰዎች አሉ።”
ወንድሞቹም፥ “በእኛ ላይ ልትነግሥብን ይሆን? ወይስ ገዢ ትሆነን ይሆን?” አሉት። እንደገናም ስለ ሕልሙና ስለ ነገሩ የበለጠ ጠሉት።
የዮሴፍም ወንድሞች አባታቸው እንደ ሞተ በአዩ ጊዜ እንዲህ አሉ፥ “ምናልባት ዮሴፍ ያደረግንበትን ክፋት ያስብብን ይሆናል፤ ባደረግንበትም ክፋት ሁሉ ብድራት ይመልስብን ይሆናል።”
ብላቴኖቹም ከሰረገላው አውርደው ለእርሱ በነበረው በሁለተኛው ሰረገላ ውስጥ አስቀመጡት፤ ወደ ኢየሩሳሌምም አመጡት፤ እርሱም በዚያ ሞተ፤ በአባቶቹም መቃብር ተቀበረ፤ ይሁዳና ኢየሩሳሌምም ሁሉ ለኢዮስያስ አለቀሱ።
የዘለዓለም ጠላት ሁነሃልና፥ በመከራቸውም ጊዜ በኀይለኛይቱ የኀጢአታቸው ቀጠሮ ጊዜ የእስራኤልን ልጆች በሰይፍ እጅ ጥለሃቸዋልና፤
የእስራኤልም ልጆች በዮርዳኖስ በኢያሪኮ አቅራቢያ በሞዓብ ሜዳ ሠላሳ ቀን ለሙሴ አለቀሱለት፤ ለሙሴም ያለቀሱለት የልቅሶው ወራት ተፈጸመ።
እኛ ደግሞ አስቀድመን የማናስተውል ነበርንና፤ የማንታዘዝ፥ የምንስት፥ ለምኞትና ለልዩ ልዩ ተድላ እንደ ባሪያዎች የምንገዛ፥ በክፋትና በምቀኝነት የምንኖር፥ የምንጣላ፥ እርስ በርሳችን የምንጠላላ ነበርን።