ዘፍጥረት 22:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእግዚአብሔር መልአክም ከሰማይ ጠራና፥ “አብርሃም! አብርሃም” አለው፤ እርሱም፥ “እነሆኝ” አለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእግዚአብሔር መልአክ ግን ከሰማይ፣ “አብርሃም! አብርሃም!” ብሎ ጠራው። አብርሃምም፣ “እነሆ፤ አለሁ” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን የጌታ መልአክ “አብርሃም! አብርሃም!” ሲል ከሰማይ ተጣራ። አብርሃምም “እነሆ፥ አለሁኝ!” አለ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን የእግዚአብሔር መልአክ ከሰማይ “አብርሃም! አብርሃም!” ብሎ ጠራው። አብርሃምም “እነሆ፥ አለሁኝ!” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእግዚአብሔር መልአክም ከሰማይ ጠራና፦ አብርሃም አብርሃም አለው፤ |
እግዚአብሔርም የሕፃኑን ጩኸት ሰማ፤ የእግዚአብሔርም መልአክ ከሰማይ አጋርን እንዲህ ሲል ጠራት፥ “አጋር ሆይ፥ ምን ሆንሽ? እግዚአብሔር የልጅሽን ድምፅ ባለበት ስፍራ ሰምቶአልና አትፍሪ።
ከእነዚህም ነገሮች በኋላ እንዲህ ሆነ። እግዚአብሔር አብርሃምን ፈተነው፤ እንዲህም አለው፥ “አብርሃም! አብርሃም ሆይ፥” እርሱም፥ “እነሆ፥ አለሁ” አለ።
እርሱም፥ “በብላቴናው ላይ እጅህን አትዘርጋ፤ አንዳችም አታድርግበት፤ ለምትውድደው ልጅህ ከእኔ አልራራህለትምና አንተ እግዚአብሔርን የምትፈራ እንደሆንህ አሁን ዐውቄአለሁ” አለው።
“እግዚአብሔር በራሴ ማልሁ ይላል፤ ይህን ነገር አድርገሃልና፥ ለምትወድደው ልጅህም ከእኔ አልራራህምና መባረክን እባርክሃለሁ፤
ከአባቴ ቤት፥ ከተወለድሁባት ምድር ያወጣኝ፦ ‘ይህችንም ምድር ለአንተና ለዘርህ እሰጥሃለሁ’ ብሎ የነገረኝና የማለልኝ የሰማይና የምድር አምላክ እግዚአብሔር፥ እርሱ መልአኩን በፊትህ ይሰድዳል፤ ከዚያም ለልጄ ሚስትን ትወስዳለህ።
እስራኤልም ዮሴፍን፥ “ወንድሞችህ በሴኬም በጎችን የሚጠብቁ አይደሉምን? ወደ እነርሱ እልክህ ዘንድ ና” አለው። እርሱም፥ “እሺ” አለው።
ከከፉ ነገር ሁሉ የአዳነኝ መልአክ እርሱ እነዚህን ብላቴኖች ይባርክ፤ ስሜም፥ የአባቶች የአብርሃምና የይስሐቅም ስም በእነርሱ ይጠራ፤ በምድር ላይ ይብዙ፤ የብዙ ብዙም ይሁኑ፤”
የእግዚአብሔርም መልአክ ለሙሴ በእሳት ነበልባል በቍጥቋጦ መካከል ታየው፤ እነሆም፥ ቍጥቋጦው በእሳት ሲነድድ፥ ቍጥቋጦውም ሳይቃጠል አየ።
እግዚአብሔር እርሱ ይመለከት ዘንድ እንደ መጣ በአየ ጊዜ እግዚአብሔር ከቍጥቋጦው ውስጥ እርሱን ጠርቶ፥ “ሙሴ! ሙሴ!” አለው እርሱም፥ “ይህ ምንድን ነው?” አለ።
የጌታንም ድምፅ፥ “ማንን እልካለሁ? ማንስ ወደዚያ ሕዝብ ይሄድልናል?” ሲል ሰማሁ? እኔም፥ “እነሆኝ፥ ጌታዬ፥ እኔን ላከኝ” አልሁ።
ሁላችንም በምድር ላይ በወደቅን ጊዜ በዕብራይስጥ ቋንቋ፦ ‘ሳውል ሳውል ለምን ታሳድደኛለህ? በሾለ ብረት ላይ መርገጥ ለአንተ ይብስሃል’ የሚለኝን ቃል ሰማሁ።
የእግዚአብሔርም መልአክ ከገልገላ ወደ ቀላውትምኖስ ወደ ቤቴል ወደ እስራኤል ቤት ወጥቶ እንዲህ አላቸው፥ “እግዚአብሔር እኔ ከግብፅ አውጥቼአችኋለሁ፤ እሰጣችሁም ዘንድ ለአባቶቻችሁ ወደ ማልሁላቸው ምድር አግብቻችኋለሁ፤ እኔም፦ ከእናንተ ጋር ያደረግሁትን ቃል ኪዳን ለዘለዓለም አላፈርስም፤