Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፍጥረት 16:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አ​ክም በውኃ ምንጭ አጠ​ገብ በሱር በረሃ በመ​ን​ገድ አገ​ኛት።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 የእግዚአብሔር መልአክ አጋርን በአንድ የውሃ ምንጭ አጠገብ በምድረ በዳ አገኛት፤ ምንጩም ወደ ሱር በሚወስደው መንገድ ዳር ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 የእግዚአብሔር መልአክም በውኃ ምንጭ አጠገብ በበረሀ አገኛት፥ ምንጩም ወደ ሱር በምትወስደው መንገድ አጠገብ ነው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 የእግዚአብሔር መልአክ አጋርን በበረሓ በሚገኘው በአንድ ምንጭ አጠገብ አገኛት፤ ይህም ምንጭ ወደ ሹር በሚወስደው መንገድ ላይ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 የእግዚአብሔር መልአክም በውኃ ምንጭ አጠገብ በበረሀ አገኛት፤ ምንጩም ወደ ሱር በምትወስደው መንገድ አጠገብ ነው።

Ver Capítulo Copiar




ዘፍጥረት 16:7
13 Referencias Cruzadas  

አብ​ር​ሃ​ምም ከዚያ ተነ​ሥቶ ወደ አዜብ ምድር አቅ​ጣጫ ሄደ፤ በቃ​ዴ​ስና በሱር መካ​ከ​ልም ኖረ፤ በጌ​ራ​ራም በእ​ን​ግ​ድ​ነት ተቀ​መጠ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የሕ​ፃ​ኑን ጩኸት ሰማ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ ከሰ​ማይ አጋ​ርን እን​ዲህ ሲል ጠራት፥ “አጋር ሆይ፥ ምን ሆንሽ? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የል​ጅ​ሽን ድምፅ ባለ​በት ስፍራ ሰም​ቶ​አ​ልና አት​ፍሪ።


ተነሺ፤ ልጅ​ሽ​ንም አንሺ፤ በእ​ጅ​ሽም አጽ​ኚው፤ ትልቅ ሕዝብ አደ​ር​ገ​ዋ​ለ​ሁና።”


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለአ​ጋር ዐይ​ን​ዋን ከፈ​ተ​ላት፤ የውኃ ጕድ​ጓ​ድ​ንም አየች፤ ሄዳም አቍ​ማ​ዳ​ውን በውኃ ሞላች፤ ልጅ​ዋ​ንም አጠ​ጣ​ችው።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አ​ክም ከሰ​ማይ ጠራና፥ “አብ​ር​ሃም! አብ​ር​ሃም” አለው፤ እር​ሱም፥ “እነ​ሆኝ” አለ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አ​ክም አብ​ር​ሃ​ምን ከሰ​ማይ ሁለ​ተኛ ጊዜ ጠራው፤ እን​ዲ​ህም አለው፦


ከአ​ባቴ ቤት፥ ከተ​ወ​ለ​ድ​ሁ​ባት ምድር ያወ​ጣኝ፦ ‘ይህ​ች​ንም ምድር ለአ​ን​ተና ለዘ​ርህ እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ’ ብሎ የነ​ገ​ረ​ኝና የማ​ለ​ልኝ የሰ​ማ​ይና የም​ድር አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ እርሱ መል​አ​ኩን በፊ​ትህ ይሰ​ድ​ዳል፤ ከዚ​ያም ለልጄ ሚስ​ትን ትወ​ስ​ዳ​ለህ።


ይስ​ማ​ኤ​ልም የኖ​ረ​በት የዕ​ድ​ሜው ዘመን መቶ ሠላሳ ሰባት ዓመት ነው ፤ ሸም​ግሎ ሞተ፤ ወደ ወገ​ኖ​ቹም ተጨ​መረ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሕ​ልም፦ ‘ያዕ​ቆብ ያዕ​ቆብ’ አለኝ፤ እኔም፦ ‘እነ​ሆኝ ምን​ድን ነው?’ አል​ሁት።


ሙሴም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ከኤ​ር​ትራ ባሕር አው​ጥቶ ወደ ሱር ምድረ በዳ ወሰ​ዳ​ቸው። በም​ድረ በዳም ሦስት ቀን ተጓዙ፤ ይጠ​ጡም ዘንድ ውኃ አላ​ገ​ኙም።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ ለሙሴ በእ​ሳት ነበ​ል​ባል በቍ​ጥ​ቋጦ መካ​ከል ታየው፤ እነ​ሆም፥ ቍጥ​ቋ​ጦው በእ​ሳት ሲነ​ድድ፥ ቍጥ​ቋ​ጦ​ውም ሳይ​ቃ​ጠል አየ።


የእግዚአብሔር ዐይኖች በሁሉ ቦታ ናቸው፤ ክፉዎችንና ደጎችንም ይመለከታሉ።


ሳኦ​ልም አማ​ሌ​ቃ​ው​ያ​ንን ከኤ​ው​ላጥ ጀምሮ በግ​ብፅ ፊት እስ​ካ​ለ​ችው እስከ ሱር ድረስ መታ​ቸው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos