ዘፍጥረት 20:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም በሕልም አለው፥ “ይህን በልብህ ቅንነት እንዳደረግህ እኔ ዐወቅሁ፤ እኔም ደግሞ በፊቴ ኀጢአትን እንዳትሠራ ጠበቅሁህ፤ ስለዚህም ትቀርባት ዘንድ አልተውሁህም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔርም በሕልሙ እንዲህ አለው፤ “አንተ ይህን ያደረግኸው በቅን ልቡና መሆኑን ዐውቄአለሁ፤ በእኔም ላይ ኀጢአት እንዳትሠራ የጠበቅሁህና እንዳትነካትም ያደረግሁት ለዚሁ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እግዚአብሔርም በሕልም እንዲህ አለው፦ “ይህን በልብህ ቅንነት እንዳደረግህ እኔ አወቅሁ፥ እኔም ደግሞ በፊቴ ኃጢአትን እንዳትሠራ ከለከልሁህ፥ ስለዚህም ትነካት ዘንድ አልተውኩህም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔርም በሕልም እንዲህ አለው፦ “በንጹሕ ኅሊና እንዳደረግህ ዐውቄአለሁ፤ ወደ እርስዋ ቀርበህ በእኔ ፊት ኃጢአት እንዳትሠራ ያደረግኩህም ስለዚህ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም በሕልም አለው፤ ይህን በልብህ ቅንነት እንዳደረግህ እኔ አወቅሁ፥ እኔም ደግሞ በፊቴ ኃጢአትን እንዳትሠራ ከለከልሁህ፤ ስለዚህም ትነካት ዘንድ አልተውሁም። |
እግዚአብሔርም ወደ ሶርያዊው ወደ ላባ በሌሊት በሕልም መጥቶ፥ “በባሪያዬ በያዕቆብ ላይ ክፉ ነገር እንዳትናገር ተጠንቀቅ” አለው።
አባታችሁ ግን አሳዘነኝ፥ ደመወዜንም ዐሥር ጊዜ ለወጠ፤ እግዚአብሔር ግን ክፉን ያደርግብኝ ዘንድ አልፈቀደለትም።
እስራኤልም ከሴቄም ሄደ፤ እግዚአብሔርንም መፍራት በዙሪያቸው ባሉት ከተሞች ሁሉ ወደቀ፤ የእስራኤልንም ልጆች ለማሳደድ አልተከተሉአቸውም።
በዚህ ቤት ከእኔ የሚበልጥ ሰው የለም፤ ሚስቱ ስለሆንሽ ከአንቺ በቀር ያልሰጠኝ ነገር የለም፤ እንዴት ይህን ትልቅ ክፉ ነገር አደርጋለሁ? በእግዚአብሔር ፊት እንዴት ኀጢአትን እሠራለሁ?”
አሕዛብን ከፊትህ በአወጣሁ ጊዜ ሀገርህን አሰፋለሁ፤ በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊትም ለመታየት በዓመት ሦስት ጊዜ ስትወጣ ማንም ምድርህን አይመኝም።
“ሰው ኀጢአትን ቢሠራ፥ የእግዚአብሔርንም ትእዛዝ ቸል ቢል፥ ያኖረበትን አደራ ወይም የኅብረትን ገንዘብ ወስዶ ባልንጀራውን ቢክድ፥ ወይም ቢቀማ፥ ወይም በባልንጀራው ላይ ግፍ ቢሠራ፥
እርሱም በፍርድ ወንበር ተቀምጦ ሳለ ሚስቱ “ስለ እርሱ ዛሬ በሕልም እጅግ መከራ ተቀብያለሁና በዚያ ጻድቅ ሰው ምንም አታድርግ፤” ብላ ላከችበት።
ስለዚህም “ከመካከላቸው ተለይታችሁ ውጡ፤ ከእነርሱም ተለዩ፤ ወደ ርኩሳንም አትቅረቡ፥ እኔም እቀበላችኋለሁ።
ስለዚህም ምክንያት፥ በእውነት ያላመኑ ነገር ግን በዐመፅ ደስ ይላቸው የነበሩ ሁሉ ፍርድን እንዲቀበሉ ሐሰትን ያምኑ ዘንድ እግዚአብሔር የስሕተትን አሠራር ይልክባቸዋል።
አሁንም ጌታዬ ሆይ! ሕያው እግዚአብሔርን! በሕያው ነፍስህ እምላለሁ! ወደ ንጹሕ ደም እንዳትገባና፥ እጅህን እንድታድን የከለከለህ እግዚአብሔር ነው፤ አሁንም ጠላቶችህና በጌታዬ ላይ ክፉ የሚሹ ሁሉ እንደ ናባል ይሁኑ።
ነገር ግን ክፉ እንዳላደርግብሽ የከለከለኝ የእስራኤል አምላክ ሕያው እግዚአብሔርን! እኔን ለመገናኘት ፈጥነሽ ባልመጣሽ ኖሮ፥ እስኪነጋ ድረስ ለናባል አጥር ተጠግቶ የሚሸን አንድ ስንኳ ባልቀረውም ብዬ ነበር።”