Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መዝሙር 51:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 የሚ​ያ​ሰ​ጥም የም​ላስ ነገ​ርን ሁሉ ወደ​ድህ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 በቃልህ ትጸድቅ፣ በፍርድህም ንጹሕ ትሆን ዘንድ፣ አንተን፣ በርግጥ አንተን ብቻ በደልሁ፤ በፊትህም ክፉ ነገር አደረግሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ከበደሌ ፈጽሞ እጠበኝ፥ ከኃጢአቴም አንጻኝ፥

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 እኔ ያመፅኩት በአንተ ላይ ነው፤ የበደልኩትም አንተን ብቻ ነው፤ አንተ የምትጠላውን ነገር አደረግሁ፤ ስለዚህ በእኔ ላይ መፍረድህና እኔንም መቅጣትህ ትክክል ነው።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 51:4
23 Referencias Cruzadas  

ልጁም፦ ‘አባቴ ሆይ፥ በሰ​ማ​ይም፥ በፊ​ት​ህም በደ​ልሁ፤ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ ልጅህ ልባል አይ​ገ​ባ​ኝም፤ ነገር ግን ከአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ እንደ አንዱ አድ​ር​ገኝ’ አለው።


መጽ​ሐፍ፥ “በነ​ገ​ርህ ትጸ​ድቅ ዘንድ፥ በፍ​ር​ድ​ህም ታሸ​ንፍ ዘንድ” ብሎ እንደ ተና​ገረ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እው​ነ​ተና ነውና፥ ሰውም ሁሉ ሐሰ​ተና ነውና።


በዚህ ቤት ከእኔ የሚ​በ​ልጥ ሰው የለም፤ ሚስቱ ስለ​ሆ​ንሽ ከአ​ንቺ በቀር ያል​ሰ​ጠኝ ነገር የለም፤ እን​ዴት ይህን ትልቅ ክፉ ነገር አደ​ር​ጋ​ለሁ? በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እን​ዴት ኀጢ​አ​ትን እሠ​ራ​ለሁ?”


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሕ​ልም አለው፥ “ይህን በል​ብህ ቅን​ነት እን​ዳ​ደ​ረ​ግህ እኔ ዐወ​ቅሁ፤ እኔም ደግሞ በፊቴ ኀጢ​አ​ትን እን​ዳ​ት​ሠራ ጠበ​ቅ​ሁህ፤ ስለ​ዚ​ህም ትቀ​ር​ባት ዘንድ አል​ተ​ው​ሁ​ህም።


የውሃውም መልአክ “ያለህና የነበርህ ጌታ ሆይ! ቅዱስ ሆይ! እንዲህ ስለፈረድህ ጻድቅ ነህ፤


ለሰው ፊት ግን ብታደሉ ኀጢአትን ትሠራላችሁ፤ ሕግም እንደ ተላላፊዎች ይወቅሳችኋል።


ነገር ግን ልቡ​ና​ህን እንደ ማጽ​ና​ትህ፥ ንስ​ሓም እንደ አለ​መ​ግ​ባ​ትህ መጠን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እው​ነ​ተና ፍርድ በሚ​ገ​ለ​ጥ​በት ቀን መቅ​ሠ​ፍ​ትን ለራ​ስህ ታከ​ማ​ቻ​ለህ።


በመ​ረ​ጠው ሰው እጅ በዓ​ለም በእ​ው​ነት የሚ​ፈ​ር​ድ​ባ​ትን ቀን ወስ​ኖ​አ​ልና፤ እር​ሱን ከሙ​ታን ለይቶ በማ​ስ​ነ​ሣ​ቱም ብዙ​ዎ​ችን ወደ ሃይ​ማ​ኖት መል​ሶ​አ​ልና።”


ሕዝ​ቡም ሁሉ ቀራ​ጮ​ችም በሰሙ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጻድቅ ነው አሉት፤ የዮ​ሐ​ን​ስን ጥም​ቀት ተጠ​ም​ቀው ነበ​ርና።


እነሆ፥ እው​ነ​ትን ወደ​ድህ፤ የማ​ይ​ነ​ገር ስውር ጥበ​ብ​ህን አስ​ታ​ወ​ቅ​ኸኝ።


አን​ተን ብቻ በደ​ልሁ፥ በፊ​ት​ህም ክፋ​ትን አደ​ረ​ግሁ፥ በነ​ገ​ርህ ትጸ​ድቅ ዘንድ በፍ​ር​ድ​ህም ታሸ​ንፍ ዘንድ።


ልጁ​ንም በእ​ሳት ሠዋ፤ ሞራ ገላ​ጭም ሆነ፤ አስ​ማ​ትም አደ​ረገ፤ መና​ፍ​ስት ጠሪ​ዎ​ች​ንና ጠን​ቋ​ዮ​ች​ንም ሰበ​ሰበ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት እጅግ ክፉ ነገር አደ​ረገ፤ ኣስ​ቈ​ጣ​ውም።


ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ው​ንም በእ​ሳት ሥዉ​አ​ቸው፤ ምዋ​ር​ተ​ኞ​ችና አስ​ማ​ተ​ኞ​ችም ሆኑ፤ ያስ​ቈ​ጡ​ትም ዘንድ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ ነገር ለማ​ድ​ረግ ራሳ​ቸ​ውን ሸጡ።


እርሱ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ንስሓ ገብ​ቶ​አ​ልና።”


የሰ​ውን ደም የሚ​ያ​ፈ​ስስ ሁሉ ስለ​ዚያ ደም ፈንታ ደሙ ይፈ​ስ​ሳል፤ ሰውን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መልክ ፈጥ​ሬ​ዋ​ለ​ሁና።


ሰማይም ተከፍቶ አየሁ፤ እነሆም አምባላይ ፈረስ፤ የተቀመጠበትም የታመነና እውነተኛ ይባላል፤ በጽድቅም ይፈርዳል፤ ይዋጋልም።


ባታመነዝርም፥ ነገር ግን ብትገድል፥ ሕግን ተላላፊ ሆነሃል።


የይ​ሁ​ዳም የበ​ኵር ልጅ ዔር በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ ነበረ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቀሠ​ፈው።


መተ​ላ​ለ​ፍን፦ ስለ እኔ ስለ ራሴ ስል የም​ደ​መ​ስስ እኔ ነኝ፤ ኀጢ​አ​ት​ህ​ንም አላ​ስ​ብም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios