ዘፍጥረት 19:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሎጥንም ጠርተው እንዲህ አሉት፥ “በሌሊት ወደ አንተ የገቡት ሰዎች ወዴት ናቸው? እናውቃቸው ዘንድ ወደ እኛ አውጣቸው።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሎጥንም ጠርተው፣ “በዚህች ምሽት ወደ ቤትህ የገቡት ሰዎች የት አሉ? ሩካቤ ሥጋ እንድንፈጽምባቸው ወደ ውጭ አውጣልን” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሎጥንም ጠርተው እንዲህ አሉት፦ “በዚህ ሌሊት ወደ ቤትህ የገቡት ሰዎች ወዴት ናቸው? እናውቃቸው ዘንድ ወደ እኛ አውጣቸው።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሎጥንም ጠርተው “ከአንተ ጋር ለማደር ወደዚህ የገቡት ሰዎች የት አሉ? ከእነርሱ ጋር ግንኙነት ለማድረግ ስለምንፈልግ ወደ እኛ አውጣቸው!” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሎጥንም ጠርተው እንዲህ አሉት፤ በዚህ ሌሊት ወደ ቤትህ የገቡት ሰዎች ወዴት ናችው? እናውቃቸው ዘንድ ወደ እኛ አውጣቸው። |
በምድርም ሁሉ ዐመፅ ነበረ፥ ከእስራኤልም ልጆች ፊት እግዚአብሔር ያሳደዳቸው የአሕዛብን ርኵሰት ሁሉ ያደርጉ ነበር።
ዛሬም ክብራቸው ተዋርዷልና፥ ፊታቸውም አፍሯልና ኀጢአታቸው እንደ ሰዶምና እንደ ገሞራ ኀጢአት ተቃወመቻቸው፤ በላያቸውም ተገልጣ ታወቀች።
ለጕስቍልናሽ ከብዙዎች እረኞች ጋር ኖርሽ የአመንዝራም ሴት ፊት ነበረብሽ፥ በሁሉም ዘንድ ያለ ኀፍረት ሄድሽ። ስለዚህ የመከርና የበልግ ዝናም ተከለከለ።
ርኩስ ነገርን ስለ ሠሩ አፍረዋልን? ምንም አላፈሩም፤ ውርደትንም አላወቁም፤ ስለዚህም ከሚወድቁ ጋር ይወድቃሉ፤ በጐበኘኋቸው ጊዜ ይዋረዳሉ፥” ይላል እግዚአብሔር።
እነሆ የእኅትሽ የሰዶም ኀጢአት ይህ ነበረ፤ ትዕቢት፥ እንጀራን መጥገብ፥ መዝለልና ሥራን መፍታት፥ ይህ ሁሉ በእርስዋና በልጆችዋ ነበር፤ የችግረኛውንና የድሀውንም እጅ አላጸናችም።
ሰማርያም የኀጢአትሽን እኩሌታ አልሠራችም፤ አንቺ ግን ከእኅቶችሽ ይልቅ ኀጢአትን አበዛሽ፤ በሠራሽውም ኀጢአት ሁሉ አጸደቅሻቸው።
ማናቸውም ሰው ከሴት ጋር እንደሚተኛ ከወንድ ጋር ቢተኛ ሁለቱ ጸያፍ ነገር አድርገዋል፤ ፈጽመው ይገደሉ፤ በደለኞች ናቸው።
ዐመፀኞች የእግዚአብሔርን መንግሥት እንደማይወርሱ አታውቁምን? አያስቱአችሁ፤ ሴሰኞች፥ ወይም ጣዖትን የሚያመልኩ፥ ወይም አመንዝራዎች፥ ወይም ቀላጮች፥ ወይም በወንድ ላይ ዝሙትን የሚሠሩ፥ የሚሠሩባቸውም ቢሆኑ፤
ጻድቅ ሎጥም በመካከላቸው ሲኖር እያየና እየሰማ ዕለት ዕለት በዐመፀኛ ሥራቸው ጻድቅ ነፍሱን አስጨንቆ ነበርና በዐመፀኞች ሴሰኛ ኑሮ የተገፋውን ያን ጻድቅ ካዳነ፥
እንዲሁም እንደ እነርሱ ዝሙትን ያደረጉና ሌላን ሥጋ የተከተሉ ሰዶምና ገሞራ በዙሪያቸውም የነበሩ ከተማዎች በዘላለም እሳት እየተቀጡ ምሳሌ ሆነዋል።
ሰውነታቸውንም ደስ ባሰኙ ጊዜ የኃጥኣን ልጆች የሆኑ የከተማው ሰዎች ቤቱን ከበቡ፤ በሩንም ይደበድቡ ነበር፤ ባለቤቱንም ሽማግሌውን ሰው፥ “ወደ ቤትህ የገባውን ሰው እንድንደርስበት አውጣልን” አሉት።