La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፍጥረት 15:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ደግ​ሞም የሚ​ያ​ሠ​ቃ​ዩ​አ​ቸ​ውን እኔ እፈ​ር​ድ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ። ከዚ​ህም በኋላ ከብዙ ገን​ዘብ ጋር ወደ​ዚህ ይወ​ጣሉ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ነገር ግን በባርነት የሚገዛቸውን ሕዝብ እቀጣዋለሁ፤ ከዚያም ብዙ ሀብት ይዘው ይወጣሉ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ደግሞም በባርነት በሚገዙአቸው ሕዝብ ላይ እኔ እፈርዳለሁ፥ ከዚያም በኋላ በብዙ ከብት ይወጣሉ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በባርነት የሚገዛቸውን ሕዝብ እቀጣለሁ፤ ከዚያም በኋላ ብዙ ሀብት ይዘው ከዚያ አገር ይወጣሉ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ደግሞም በባርነት በገዙአቸው ሕዝብ ላይ እኔ እፈርዳለሁ ከዚያም በኍላ በብዙ ከብት ይወጣሉ።

Ver Capítulo



ዘፍጥረት 15:14
24 Referencias Cruzadas  

እስ​ራ​ኤ​ልም ዮሴ​ፍን፥ “እነሆ፥ እኔ እሞ​ታ​ለሁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከእ​ና​ንተ ጋር ይሆ​ናል፤ ወደ አባ​ቶ​ቻ​ች​ሁም ምድር ይመ​ል​ሳ​ች​ኋል፤


ዮሴ​ፍም ወን​ድ​ሞ​ቹን አላ​ቸው፥ “እኔ እሞ​ታ​ለሁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መጐ​ብ​ኘ​ትን ይጐ​በ​ኛ​ች​ኋል፤ ከዚ​ህ​ችም ምድር ያወ​ጣ​ች​ኋል። ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን ለአ​ብ​ር​ሃ​ምና ለይ​ስ​ሐቅ ለያ​ዕ​ቆ​ብም ወደ ማለ​ላ​ቸው ምድር ያገ​ባ​ች​ኋል።”


ጠላ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም አሠ​ቃ​ዩ​አ​ቸው፥ ከእ​ጃ​ቸ​ውም በታች ተዋ​ረዱ።


እስ​ራ​ኤ​ልን በመ​ካ​ከሉ ያሳ​ለፈ፤ ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና፤


ለጨ​ረ​ቃና ለከ​ዋ​ክ​ብት ሌሊ​ትን ያስ​ገ​ዛ​ቸው፤ ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና፤


የሚ​ያ​ሰ​ጥም የም​ላስ ነገ​ርን ሁሉ ወደ​ድህ።


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ እኩለ ሌሊት በሆነ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዙ​ፋን ከተ​ቀ​መ​ጠው ከፈ​ር​ዖን በኵር ጀምሮ እስከ ውኃ ቀጅዋ ምር​ኮኛ በኵር ድረስ፥ በግ​ብፅ ምድር በኵ​ሩን ሁሉ፥ የእ​ን​ስ​ሳ​ው​ንም በኵር ሁሉ መታ።


አሁ​ንም ና፤ ወደ ግብፅ ንጉሥ ወደ ፈር​ዖን እል​ክ​ሃ​ለሁ። ሕዝ​ቤን የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ከግ​ብፅ ምድር ታወ​ጣ​ቸ​ዋ​ለህ።”


ደግ​ሞም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አለ፤ ባሮች አድ​ር​ገው በሚ​ገ​ዙ​አ​ቸው ወገ​ኖች እኔ እፈ​ር​ድ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ከዚ​ህም በኋላ ይወ​ጣሉ፤ በዚ​ህም ሀገር ያመ​ል​ኩ​ኛል።’


እና​ን​ተን ግን እንደ ዛሬው ሁሉ የር​ስቱ ሕዝብ ትሆ​ኑ​ለት ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወስዶ ከብ​ረት እቶን ከግ​ብፅ አወ​ጣ​ችሁ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በግ​ብ​ፅና በፈ​ር​ዖን በቤ​ቱም ሁሉ ላይ በፊ​ታ​ችን ታላ​ቅና ክፉ ምል​ክት፥ ተአ​ም​ራ​ትም አደ​ረገ።


እኛ​ንና አባ​ቶ​ቻ​ች​ንን ከባ​ር​ነት ቤት ከግ​ብፅ ምድር ያወ​ጣን፥ በዐ​ይ​ና​ች​ንም ፊት እነ​ዚ​ያን ታላ​ላቅ ተአ​ም​ራት ያደ​ረገ፥ በሄ​ድ​ን​ባ​ትም መን​ገድ ሁሉ፥ ባለ​ፍ​ን​ባ​ቸ​ውም አሕ​ዛብ ሁሉ መካ​ከል የጠ​በ​ቀን፥ እርሱ አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነውና።


ያዕ​ቆ​ብና ልጆቹ ወደ ግብጽ በገቡ ጊዜ ግብ​ጻ​ው​ያን አስ​ጨ​ነ​ቁ​አ​ቸው፤ አባ​ቶ​ቻ​ች​ሁም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኹ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴ​ንና አሮ​ንን ላከ፤ አባ​ቶ​ቻ​ች​ሁ​ንም ከግ​ብጽ አው​ጥ​ተው በዚህ ቦታ አኖ​ሩ​አ​ቸው።