ዘፍጥረት 12:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የፈርዖንም አለቆች አዩአት፤ በፈርዖንም ፊት አደነቁአት፤ ወደ ፈርዖን ቤትም ወሰዱአት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የፈርዖንም ሹማምት ባዩአት ጊዜ፣ ለፈርዖን አድንቀው ነገሩት፤ ወደ ቤተ መንግሥትም ወሰዷት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የፈርዖንም አለቆች አዩአት፥ በፈርዖንም ፊት አመሰገኑአት፥ ሴቲቱንም ወደ ፈርዖን ቤት ወሰዱአት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲሁም አንዳንድ የፈርዖን ባለሟሎች ባዩአት ጊዜ ስለ ቁንጅናዋ ለፈርዖን ተናገሩ፤ ስለዚህ ወደ ቤተ መንግሥት ተወሰደች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የፈርዖንም አለቆች አዩአት በፈርዖንም ፊት አመስመገኑአት ሴቲቱንም ወደ ፈርዖን ቤት ወሰዱአት። |
አብርሃምም ሚስቱን ሣራን “እኅቴ ናት” አላቸው፤ የከተማዪቱ ሰዎች ስለ እርስዋ እንዳይገድሉት “ሚስቴ” ናት ማለትን ፈርቶአልና፤ የጌራራ ንጉሥ አቤሜሌክም ላከና ሣራን ወሰዳት።
ሰሎሞንም ለግብፅ ንጉሥ ለፈርዖን አማች ሆነ፤ የፈርዖንንም ልጅ አገባ፤ ቤቱንና የእግዚአብሔርንም ቤት፥ በኢየሩሳሌምም ዙሪያ ያለውን ቅጥር ሠርቶ እስኪፈጽም ድረስ ወደ ዳዊት ከተማ አምጥቶ አስገባት።
እነሆ፥ በዚህ በተቀጠቀጠ በሸምበቆ በትር በግብፅ ትታመናለህ፤ ሰው ቢመረኰዘው ተሰብሮ በእጁ ይገባል፥ ያቈስለውማል፤ የግብፅ ንጉሥ ፈርዖን ለሚታመኑበት ሁሉ እንዲሁ ነው።
ፈርዖንም ይህን ነገር ሰማ፤ ሙሴንም ሊገድለው ፈለገ። ሙሴ ግን ከፈርዖን ፊት ኰበለለ፤ በምድያምም ምድር ተቀመጠ፤ ወደ ምድያም ምድር በደረሰ ጊዜም በውኃው ጕድጓድ አጠገብ ዐረፈ።
የፈርዖንም ሴት ልጅ ልትታጠብ ወደ ወንዝ ወረደች፤ ደንገጥሮችዋም በወንዝ ዳር ይሄዱ ነበር፤ ሣጥኑንም በቄጠማ ውስጥ አየች፤ ደንገጥርዋንም ልካ አስመጣችው።
“የሰው ልጅ ሆይ! ስለ ግብፅ ንጉሥ ስለ ፈርዖን ሙሾ አሙሽ፤ እንዲህም በለው፦ የአሕዛብን አንበሳ መስለህ ነበር፤ ነገር ግን እንደ ባሕር ዘንዶ ሆነሃል፤ ወንዞችህንም ወግተሃል፤ ውኃውንም በእግርህ አደፍርሰሃል፥ ወንዞችህንም በተረከዝህ ረግጠሃል።
መጋባት በሁሉ ዘንድ ክቡር ነው፥ ለመኝታቸውም ርኵሰት የለውም፤ ሴሰኞችንና አመንዝሮችን ግን እግዚአብሔር ይፈርድባቸዋል።