ዕዝራ 7:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአቢሱ ልጅ፥ የፊንሐስ ልጅ፥ የአልዓዛር ልጅ፥ የመጀመሪያው ካህን የአሮን ልጅ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የአቢሱ ልጅ፣ የፊንሐስ ልጅ፣ የአልዓዛር ልጅ፣ የታላቁ ካህን የአሮን ልጅ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የአቢሹዓ ልጅ፥ የፊንሐስ ልጅ፥ የኤልዓዛር ልጅ፥ የታላቁ ካህን የአሮን ልጅ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቡቂ የአቢሹዓ ልጅ፥ አቢሹዓ የፊንሐስ ልጅ፥ ፊንሐስ የአልዓዛር ልጅ፥ አልዓዛር የሊቀ ካህናቱ የአሮን ልጅ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የአቢሱ ልጅ፥ የፊንሐስ ልጅ፥ የአልዓዛር ልጅ፥ የታላቁ ካህን የአሮን ልጅ፤ |
እነሆም፥ ለእግዚአብሔር በሚሆነው ነገር ሁሉ የካህናቱ አለቃ አማርያ፥ በንጉሡም ነገር ሁሉ የይሁዳ ቤት አለቃ የይስማኤል ልጅ ዝባድያስ በላያችሁ ተሾመዋል፤ ጸሐፍቱና ሌዋውያኑ ደግሞ በፊታችሁ አሉ፤ በርትታችሁም አድርጉ፤ እግዚአብሔር መልካም ከሚያደርግ ጋር ይሁን።
ታላቁ ካህን ዓዛርያስ፥ ካህናቱም ሁሉ ተመለከቱት፤ እነሆም፥ በግንባሩ ላይ ለምጽ ነበረ፤ ፈጥነውም አባረሩት፤ እርሱም ደግሞ እግዝአብሔር ቀሥፎት ነበርና ይወጣ ዘንድ ቸኰለ።
ይህም ዕዝራ ከባቢሎን ወጣ፤ እርሱም የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ለሙሴ የሰጠውን ሕግ ዐዋቂ ነበረ፤ የአምላኩም የእግዚአብሔር እጅ በእርሱ ላይ ነበረችና ንጉሡ ያሻውን ሁሉ ሰጠው።
የአሮንም ልጅ አልዓዛር ከፋትኤል ልጆች ሚስትን አገባ፤ እርስዋም ፊንሐስን ወለደችለት። እነዚህም በየወገኖቻቸው የሌዋውያን አባቶች አለቆች ናቸው።
ሙሴም አሮንን፥ የተረፉለትን ልጆቹን አልዓዛርንና ኢታምርን አላቸው፥ “ቅዱሰ ቅዱሳን ነውና ለእግዚአብሔር ከሆነው ከእሳት ቍርባን የቀረውን የስንዴውን ቍርባን ውሰዱ፤ ቂጣም አድርጋችሁ በመሠዊያው አጠገብ ብሉት፤
ሙሴም የኀጢአቱን መሥዋዕት ፍየል እጅግ ፈለገው፤ በፈለገውም ጊዜ እነሆ ተቃጥሎ ነበር፤ ሙሴም የቀሩትን የአሮንን ልጆች አልዓዛርንና ኢታምርን ተቈጣቸው፤ እንዲህም አላቸው፦
ሙሴም አሮንን፥ ልጆቹንም አልዓዛርንና ኢታምርን፥ “እንዳትሞቱ፥ በማኅበሩም ላይ ሁሉ ቍጣ እንዳይወርድ ራሳችሁን አትንጩ፤ ልብሳችሁንም አትቅደዱ፤ እግዚአብሔር ስላቃጠላቸው ማቃጠል ግን ወንድሞቻችሁ የእስራኤል ቤት ሁሉ ያልቅሱ።
በምስክሩም ድንኳን ደጃፍ አጠገብ በሙሴና በካህኑ በአልዓዛር፥ በአለቆቹም፥ በማኅበሩም ሁሉ ፊት ቆመው እንዲህ አሉ፦
ሙሴና ካህኑ አልዓዛርም ወርቁን ከሻለቆችና ከመቶ አለቆች ወሰዱ፤ በእግዚአብሔርም ፊት ለእስራኤል ልጆች መታሰቢያ ወደ ምስክሩ ድንኳን አገቡት።
ሙሴም ከየነገዱ አንድ ሺህ ከሠራዊታቸውና ከካህኑ ከአሮን ልጅ ከአልዓዛር ልጅ ከፊንሐስ ጋር ሰደደ፤ ንዋያተ ቅድሳቱና ምልክት መስጫ መለከቶችም በእጆቻቸው ነበሩ።
የእስራኤልም ልጆች በከነዓን ምድር የወረሱት ካህኑ አልዓዛርና የነዌ ልጅ ኢያሱ፥ የእስራኤልም ልጆች ነገድ የአባቶቻቸው አለቆች ያወረሱአቸው ርስት ይህ ነው።
የእስራኤልም ልጆች በገለዓድ ምድር ወዳሉት ወደ ሮቤል ልጆችና ወደ ጋድ ልጆች ወደ ምናሴም ነገድ እኩሌታ የካህኑ የአሮንን ልጅ የአልዓዛርን ልጅ ፊንሐስን ላኩ።
የካህኑም የአልዓዛር ልጅ ፊንሐስ ለሮቤል ልጆችና ለጋድ ልጆች ለምናሴም ነገድ እኩሌታ፥ “ይህን መተላለፍ በእግዚአብሔር ላይ አላደረጋችሁምና እግዚአብሔር በመካከላችን እንዳለ ዛሬ እናውቃለን፤ አሁን የእስራኤልን ልጆች ከእግዚአብሔር እጅ አድናችኋል” አላቸው።
የአሮንም ልጅ ሊቀ ካህናቱ አልዓዛር ሞተ፤ በተራራማውም በኤፍሬም ሀገር ለልጁ ለፊንሐስ በተሰጠችው በጊብዓት መሬት ቀበሩት።
በዚያም ዘመን የአሮን ልጅ የአልዓዛር ልጅ ፊንሐስ በፊቷ ይቆም ነበርና። “ከወንድሞቻችን ከብንያም ልጆች ጋር ለመዋጋት ዳግመኛ እንውጣን? ወይስ እንቅር?” አሉ። እግዚአብሔርም፥ “ነገ በእጃችሁ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁና ውጡ” አላቸው።