Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዕብራውያን 5:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 እንደ አሮ​ንም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከተ​ጠራ በቀር፥ ማንም ለራሱ ክብ​ርን የሚ​ወ​ስድ የለም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 አሮን እንደ ተጠራ በእግዚአብሔር መጠራት አለበት እንጂ፣ ይህን ክብር ለራሱ የሚወስድ ማንም የለም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 እንደ አሮንም በእግዚአብሔር ካልተጠራ በቀር ማንም ክብሩን ለራሱ የሚወስድ የለም።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 እንደ አሮን በእግዚአብሔር የተጠራ ካልሆነ በቀር ማንም ይህን ክብር በገዛ ራሱ አያገኝም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 እንደ አሮንም በእግዚአብሔር ከተጠራ በቀር ማንም ክብሩን ለራሱ የሚወስድ የለም።

Ver Capítulo Copiar




ዕብራውያን 5:4
16 Referencias Cruzadas  

የእ​ን​በ​ረም ልጆች አሮ​ንና ሙሴ ነበሩ፤ አሮ​ንም ለቅ​ድ​ስተ ቅዱ​ሳን የተ​ቀ​ደሰ ይሆን ዘንድ ተመ​ረጠ፤ እር​ሱና ልጆቹ ለዘ​ለ​ዓ​ለም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያጥ​ኑና ያገ​ለ​ግሉ ነበር፤ በስ​ሙም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይባ​ርኩ ነበር።


ንጉ​ሡ​ንም ዖዝ​ያ​ንን እየ​ተ​ቃ​ወሙ፥ “ዖዝ​ያን ሆይ፥ ዕጣን ማጠን ለተ​ቀ​ደ​ሱት ለአ​ሮን ልጆች ለካ​ህ​ናቱ ነው እንጂ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታጥን ዘንድ ለአ​ንተ አይ​ገ​ባ​ህም፤ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ርቀ​ሃ​ልና ከመ​ቅ​ደሱ ውጣ፤ ይህም በአ​ም​ላክ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ዘንድ ለአ​ንተ ክብር አይ​ሆ​ን​ህም” አሉት።


የአ​ቢሱ ልጅ፥ የፊ​ን​ሐስ ልጅ፥ የአ​ል​ዓ​ዛር ልጅ፥ የመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ካህን የአ​ሮን ልጅ፥


“አን​ተም ወን​ድ​ም​ህን አሮ​ንን ከእ​ር​ሱም ጋር ልጆ​ቹን ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች መካ​ከል ለይ​ተህ በክ​ህ​ነት ያገ​ለ​ግ​ሉኝ ዘንድ ወደ አንተ አቅ​ርብ፤ አሮ​ንን የአ​ሮ​ን​ንም ልጆች፥ ናዳ​ብን፥ አብ​ዩ​ድ​ንም፥ አል​ዓ​ዛ​ር​ንም ኢታ​ም​ር​ንም አቅ​ርብ።


“አሮ​ንን፥ ከእ​ር​ሱም ጋር ልጆ​ቹን፥ ልብ​ሱ​ንም፥ የቅ​ብ​ዐ​ቱ​ንም ዘይት፥ ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕ​ትም የሆ​ነ​ውን ወይ​ፈን፥ ሁለ​ቱ​ንም አውራ በጎች፥ የቂ​ጣ​ው​ንም እን​ጀራ መሶብ ውሰድ፤


አን​ተን ከአ​ን​ተም ጋር የሌ​ዊን ልጆች ወን​ድ​ሞ​ች​ህን ሁሉ ወደ እርሱ አቅ​ር​ቦ​አል፤ ካህ​ና​ትም ትሆኑ ዘንድ ትፈ​ል​ጋ​ላ​ች​ሁን?


እሳ​ትም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ወጥታ ያጥኑ የነ​በ​ሩ​ትን ሁለት መቶ አምሳ ሰዎች በላች።


እንደ ቆሬና ከእ​ር​ሱም ጋር እንደ ተቃ​ወ​ሙት ሰዎች እን​ዳ​ይ​ሆን፥ ከአ​ሮን ልጆች ያል​ሆነ ሌላ ሰው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ዕጣን ያጥን ዘንድ እን​ዳ​ይ​ቀ​ርብ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሙሴ ቃል እንደ ተና​ገ​ረው፥ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች መታ​ሰ​ቢያ አደ​ረ​ጋ​ቸው።


ለቆ​ሬም ለማ​ኅ​በ​ሩም ሁሉ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ነገ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የእ​ርሱ የሚ​ሆ​ኑ​ትን፥ ቅዱ​ሳ​ንም የሆ​ኑ​ትን ያያል፥ ያው​ቃ​ልም፤ የመ​ረ​ጣ​ቸ​ው​ንም ሰዎች ወደ እርሱ ያቀ​ር​ባ​ቸ​ዋል።


ነገም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እሳት አድ​ር​ጉ​ባ​ቸው፤ ዕጣ​ንም ጨም​ሩ​ባ​ቸው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የሚ​መ​ር​ጠው ይህ ሰው ለሌዊ ልጆች ቅዱስ ይሁ​ን​ላ​ቸው።”


አን​ተም ከአ​ን​ተም ጋር ልጆ​ችህ እንደ መሠ​ዊ​ያ​ውና፥ በመ​ጋ​ረ​ጃ​ውም ውስጥ እን​ዳ​ለው ሥር​ዐት ሁሉ ክህ​ነ​ታ​ች​ሁን ጠብቁ፤ የሀ​ብተ ክህ​ነት አገ​ል​ግ​ሎ​ታ​ች​ሁ​ንም አድ​ርጉ፤ ከሌ​ላም ወገን የሆነ ሰው ቢቀ​ርብ ይገ​ደል።”


በክ​ህ​ነት ያገ​ለ​ግሉ ዘንድ የተ​ቀ​ቡና እጆ​ቻ​ቸ​ውን የተ​ቀ​ደሱ የአ​ሮን ልጆች ስም ይህ ነው።


ዮሐ​ን​ስም መልሶ እን​ዲህ አለ፥ “ሰው ከሰ​ማይ ካል​ተ​ሰ​ጠው በስ​ተ​ቀር እርሱ ራሱ ጸጋን ገን​ዘብ ሊያ​ደ​ርግ ምንም አይ​ች​ልም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos