Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፀአት 6:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 የአ​ሮ​ንም ልጅ አል​ዓ​ዛር ከፋ​ት​ኤል ልጆች ሚስ​ትን አገባ፤ እር​ስ​ዋም ፊን​ሐ​ስን ወለ​ደ​ች​ለት። እነ​ዚ​ህም በየ​ወ​ገ​ኖ​ቻ​ቸው የሌ​ዋ​ው​ያን አባ​ቶች አለ​ቆች ናቸው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 የአሮን ልጅ አልዓዛር ከፉትኤል ሴት ልጆች አንዷን አገባ፤ እርሷም ፊንሐስን ወለደችለት። እነዚህ እንደየነገዳቸው የሌዋውያን ጐሣዎች አለቆች ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 የአሮንም ልጅ ኤልዓዛር ከፑቲኤል ልጆች አንዷን ሚስት አገባ፥ እርሷም ፒንሐስን ወለደችለት። እነዚህ እንደ ወገኖቻቸው የሌዋውያን አባቶች አለቆች ናቸው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 የአሮን ልጅ አልዓዛር የፑቲኤልን ልጅ አገባ፤ እርስዋም ፊኒሐስን ወለደችለት፤ እነዚህ ሁሉ የሌዊ የነገድ አባቶችና አለቆች ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 የአሮንም ልጅ አልዓዛር ከፉትኤል ልጆች ሚስት አገባ፤ እርስዋም ፊንሐስን ወለደችለት። እነዚህ እንደ ወገኖቻቸው የሌዋውያን አባቶች አለቆች ናቸው።

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 6:25
9 Referencias Cruzadas  

የአ​ቢሱ ልጅ፥ የፊ​ን​ሐስ ልጅ፥ የአ​ል​ዓ​ዛር ልጅ፥ የመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ካህን የአ​ሮን ልጅ፥


የሌዊ ልጆች በየ​ወ​ገ​ና​ቸው የተ​ቈ​ጠ​ሩት እነ​ዚህ ናቸው፤ ከጌ​ድ​ሶን የጌ​ድ​ሶ​ና​ው​ያን ወገን፥ ከቀ​ዓት የቀ​ዓ​ታ​ው​ያን ወገን፥ ከሜ​ራሪ የሜ​ራ​ራ​ው​ያን ወገን።


ሙሴም ከየ​ነ​ገዱ አንድ ሺህ ከሠ​ራ​ዊ​ታ​ቸ​ውና ከካ​ህኑ ከአ​ሮን ልጅ ከአ​ል​ዓ​ዛር ልጅ ከፊ​ን​ሐስ ጋር ሰደደ፤ ንዋ​ያተ ቅድ​ሳ​ቱና ምል​ክት መስጫ መለ​ከ​ቶ​ችም በእ​ጆ​ቻ​ቸው ነበሩ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በገ​ለ​ዓድ ምድር ወዳ​ሉት ወደ ሮቤል ልጆ​ችና ወደ ጋድ ልጆች ወደ ምና​ሴም ነገድ እኩ​ሌታ የካ​ህኑ የአ​ሮ​ንን ልጅ የአ​ል​ዓ​ዛ​ርን ልጅ ፊን​ሐ​ስን ላኩ።


የአ​ሮ​ንም ልጅ ሊቀ ካህ​ናቱ አል​ዓ​ዛር ሞተ፤ በተ​ራ​ራ​ማ​ውም በኤ​ፍ​ሬም ሀገር ለልጁ ለፊ​ን​ሐስ በተ​ሰ​ጠ​ችው በጊ​ብ​ዓት መሬት ቀበ​ሩት።


በዚ​ያም ዘመን የአ​ሮን ልጅ የአ​ል​ዓ​ዛር ልጅ ፊን​ሐስ በፊቷ ይቆም ነበ​ርና። “ከወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ከብ​ን​ያም ልጆች ጋር ለመ​ዋ​ጋት ዳግ​መኛ እን​ው​ጣን? ወይስ እን​ቅር?” አሉ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “ነገ በእ​ጃ​ችሁ አሳ​ልፌ እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለ​ሁና ውጡ” አላ​ቸው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos