La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፀአት 39:42 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን እን​ዳ​ዘዘ ሁሉ እን​ዲሁ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሥራ​ውን ሁሉ ሠሩ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እስራኤላውያን ልክ እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው ሥራውን ሁሉ አከናወኑ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የእስራኤልም ልጆች ጌታ ሙሴን እንዳዘዘው ሁሉ ልክ እንደዛው አድርገው ሠሩ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እስራኤላውያን ሥራውን ሁሉ እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት ሠሩ፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘ ሁሉ እንዲሁ የእስራኤል ልጆች ሥራውን ሁሉ ሠሩ።

Ver Capítulo



ዘፀአት 39:42
15 Referencias Cruzadas  

በዐ​ሥራ አን​ደ​ኛ​ውም ዓመት ቡል በሚ​ባል በስ​ም​ን​ተ​ኛው ወር ቤቱ እንደ ክፍ​ሎ​ቹና እንደ ሥር​ዐቱ ሁሉ ተጨ​ረሰ። በሰ​ባት ዓመ​ትም ሠራው።


እነ​ር​ሱም ንጉሡ ስለ ነገሩ ሁሉና ስለ መዝ​ገቡ ካህ​ና​ቱ​ንና ሌዋ​ው​ያ​ኑን ያዘ​ዘ​ውን ነገር ሁሉ አል​ተ​ላ​ለ​ፉም።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ሄዱ፤ እን​ዲ​ህም አደ​ረጉ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴ​ንና አሮ​ንን እንደ አዘ​ዛ​ቸው እን​ዲሁ አደ​ረጉ።


“በእ​ና​ንተ ዘንድ ያለ፥ በልቡ ጥበ​በኛ የሆነ ሁሉ መጥቶ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያዘ​ዘ​ውን ሁሉ ያድ​ርግ።


እን​ዲ​ሁም የም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ሥራ ሁሉ ተፈ​ጸመ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው ሁሉ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች አደ​ረጉ፤ እን​ዲሁ አደ​ረጉ።


በመ​ቅ​ደስ ውስጥ ለማ​ገ​ል​ገል በብ​ል​ሃት የተ​ሠ​ሩ​ትን ልብ​ሶች፥ በክ​ህ​ነ​ትም ያገ​ለ​ግ​ሉ​በት ዘንድ የተ​ቀ​ደ​ሱ​ትን የካ​ህ​ኑን የአ​ሮ​ንን ልብ​ሶች፥ የል​ጆ​ቹ​ንም ልብ​ሶች አመጡ።


ሙሴም ሥራ​ውን ሁሉ አየ፤ እነ​ሆም፥ አድ​ር​ገ​ውት ነበር፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ዘ​ዘው እን​ዲሁ አድ​ር​ገ​ውት ነበር፤ ሙሴም ባረ​ካ​ቸው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዳ​ዘ​ዘኝ ሄድሁ፤ በኤ​ፍ​ራ​ጥ​ስም ወንዝ አጠ​ገብ ሸሸ​ግ​ኋት።


ደመ​ና​ውም እስከ ወር ቈይቶ በድ​ን​ኳኑ ላይ ቢቀ​መጥ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች በሰ​ፈ​ራ​ቸው ይቀ​መጡ ነበር፤ አይ​ጓ​ዙ​ምም ነበር፤ ነገር ግን በተ​ነሣ ጊዜ ይጓዙ ነበር።


“እኔ ዛሬ የማ​ዝ​ዝ​ህን ነገር ሁሉ ታደ​ር​ገው ዘንድ ጠብቅ፤ ምንም በእ​ርሱ ላይ አት​ጨ​ምር፤ ከእ​ር​ሱም ምንም አታ​ጕ​ድል።


የእውነትን ቃል በቅንነት የሚናገር የማያሳፍርም ሠራተኛ ሆነህ፥ የተፈተነውን ራስህን ለእግዚአብሔር ልታቀርብ ትጋ።


መልካሙን ገድል ተጋድዬአለሁ፤ ሩጫውን ጨርሼአለሁ፤ ሃይማኖትን ጠብቄአለሁ፤