Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -


2 ዜና መዋዕል 8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ሰሎ​ሞን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤትና የራ​ሱን ቤት የሠ​ራ​በት ሃያ ዓመት በተ​ፈ​ጸመ ጊዜ፥

2 ኪራም ለሰ​ሎ​ሞን የሰ​ጠ​ውን ከተ​ሞች ሰሎ​ሞን ሠራ​ቸው፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ልጆች አኖ​ረ​ባ​ቸው።

3 ሰሎ​ሞ​ንም ወደ ኤማ​ት​ሱባ ሄደ፤ በረ​ታ​ባ​ትም።

4 በም​ድረ በዳም ያለ​ውን ተድ​ሞ​ርን፥ በኤ​ማ​ትም የጸኑ ከተ​ሞ​ችን ሁሉ ሠራ።

5 ደግ​ሞም ቅጥ​ርና መዝ​ጊያ፥ መወ​ር​ወ​ሪ​ያም የነ​በ​ራ​ቸ​ውን የተ​መ​ሸ​ጉ​ትን ከተ​ሞች ላይ​ኛ​ውን ቤት​ሖ​ርን፥ ታች​ኛ​ው​ንም ቤት​ሖ​ርን ሠራ።

6 ባዕ​ላ​ት​ንም፥ ለሰ​ሎ​ሞ​ንም የነ​በ​ሩ​ትን የዕቃ ቤት ከተ​ሞች ሁሉ፥ የሰ​ረ​ገ​ላ​ው​ንም ከተ​ሞች ሁሉ፥ የፈ​ረ​ሰ​ኞ​ች​ንም ከተ​ሞች፥ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም፥ በሊ​ባ​ኖ​ስም፥ በመ​ን​ግ​ሥ​ቱም ምድር ሁሉ ሰሎ​ሞን ይሠራ ዘንድ የወ​ደ​ደ​ውን ሁሉ ሠራ።

7 ከኬ​ጤ​ዎ​ና​ው​ያን፥ ከአ​ሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያን፥ ከፌ​ር​ዜ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም፥ ከኤ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም፥ ከኢ​ያ​ቡ​ሴ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም የቀ​ሩ​ትን፥ ከእ​ስ​ራ​ኤል ወገን ያል​ሆ​ኑ​ትን ሕዝብ ሁሉ፥

8 የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ያላ​ጠ​ፉ​አ​ቸ​ውን፥ በኋ​ላ​ቸ​ውም በም​ድር ላይ የቀ​ሩ​ትን ልጆ​ቻ​ቸ​ውን ሰሎ​ሞን እስከ ዛሬ ድረስ ገባ​ሮች አደ​ረ​ጋ​ቸው።

9 ሰሎ​ሞ​ንም በመ​ን​ግ​ሥቱ ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ማን​ንም አገ​ል​ጋይ አላ​ደ​ረ​ገም፤ እነ​ርሱ ሰል​ፈ​ኞች፥ የሹ​ሞ​ችም አለ​ቆች፥ የሰ​ረ​ገ​ሎ​ችና የፈ​ረ​ሰ​ኞች ባል​ደ​ራ​ሶች ነበ​ሩና።

10 እነ​ዚ​ህም በሕ​ዝቡ ላይ ያለ​ውን ሥራ የሚ​ቈ​ጣ​ጠሩ የን​ጉሡ የሰ​ሎ​ሞን ዓይ​ነ​ተ​ኞች አለ​ቆች ሁለት መቶ አምሳ ነበሩ።

11 ሰሎ​ሞ​ንም፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቦት የገ​ባ​ች​በት ስፍራ ቅዱስ ነውና ሚስቴ በእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ በዳ​ዊት ቤት አት​ቀ​መ​ጥም” ሲል የፈ​ር​ዖ​ንን ልጅ ከዳ​ዊት ከተማ ወደ ሠራ​ላት ቤት አወ​ጣት።

12 በዚያ ጊዜም ሰሎ​ሞን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ፊት በሠ​ራው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ ላይ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት አቀ​ረበ።

13 ሙሴም እን​ዳ​ዘዘ እንደ ሥር​ዐ​ታ​ቸው በየ​ቀኑ ሁሉ፥ በየ​ሰ​ን​በ​ታ​ቱም፥ በየ​መ​ባ​ቻ​ዎ​ቹም፥ በየ​በ​ዓ​ላ​ቱም፥ በየ​ዓ​መቱ ሦስት ጊዜ በየ​ቂ​ጣው በዓ​ልና በየ​ሰ​ባቱ ሱባዔ በዓል፥ በየ​ዳ​ሱም በዓል ቍር​ባን ያቀ​ርቡ ነበር።

14 የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰው ዳዊት እን​ዲህ አዝዞ ነበ​ርና ካህ​ና​ቱን እንደ አባቱ እንደ ዳዊት ሥር​ዐት በየ​አ​ገ​ል​ግ​ሎ​ታ​ቸው ሰሞን ከፈ​ላ​ቸው፤ ሌዋ​ው​ያ​ንም እንደ ሥር​ዐ​ታ​ቸው ያመ​ሰ​ግኑ ዘንድ፥ በካ​ህ​ና​ቱም ፊት ያገ​ለ​ግሉ ዘንድ በየ​ሰ​ሞ​ና​ቸው ከፈ​ላ​ቸው፤ በረ​ኞ​ቹ​ንም ደግሞ በየ​በሩ ሁሉ በየ​ሰ​ሞ​ና​ቸው ከፈ​ላ​ቸው።

15 እነ​ር​ሱም ንጉሡ ስለ ነገሩ ሁሉና ስለ መዝ​ገቡ ካህ​ና​ቱ​ንና ሌዋ​ው​ያ​ኑን ያዘ​ዘ​ውን ነገር ሁሉ አል​ተ​ላ​ለ​ፉም።

16 እነሆ፥ መሠ​ረቱ ከተ​ጣለ ጀምሮ ሰሎ​ሞን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት እስከ ፈጸመ ድረስ ሥራው ሁሉ የተ​ዘ​ጋጀ ነበረ። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት ተፈ​ጸመ።

17 ሰሎ​ሞ​ንም የዚ​ያን ጊዜ በኤ​ዶ​ም​ያስ ምድር በባ​ሕር ዳር ወዳሉ ወደ ጋሴ​ዎ​ን​ጋ​ብ​ርና ወደ ኤላት ሄደ።

18 ኪራ​ምም መር​ከ​ቦ​ች​ንና የባ​ሕ​ርን ነገር የሚ​ያ​ው​ቁ​ትን መር​ከ​በ​ኞች በአ​ገ​ል​ጋ​ዮቹ እጅ ላከ​ለት፤ እነ​ር​ሱም ከሰ​ሎ​ሞን አገ​ል​ጋ​ዮች ጋር ወደ ሴፌር መጡ፤ ከዚ​ያም አራት መቶ አምሳ መክ​ሊት ወርቅ ወስ​ደው ወደ ንጉሡ ወደ ሰሎ​ሞን አመጡ።

Síguenos en:



Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos