ለእርሱ ለራሱ እንዲሆን ሕዝብን ይቤዥ ዘንድ ለእርሱ ለራሱም ታላቅ ስምን ያደርግ ዘንድ አሕዛብንና ሰፈሮቻቸውን በመበተን ከግብፅ በተቤዠኸው ሕዝብህ ፊት ታምራትንና ድንቅን ያደርግ ዘንድ እግዚአብሔር እንደ መራው እንደ ሕዝብህ እንደ እስራኤል ያለ በምድር ላይ ምን ሕዝብ አለ?
ዘፀአት 34:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፥ “እነሆ፥ እኔ በሕዝብህ ፊት ሁሉ ቃል ኪዳን አደርጋለሁ፤ በምድር ሁሉ፥ በአሕዛብም ሁሉ ዘንድ እንደ እርሱ ያለ ከቶ ያልተደረገውን ታላቅ ተአምራትን አደርግልሃለሁ፤ እኔም የማደርግልህ ነገር ድንቅ ነውና አንተ በመካከሉ ያለህበት ይህ ሕዝብ ሁሉ የእግዚአብሔርን ሥራ ያያል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም እግዚአብሔር እንዲህ አለ፤ “ከአንተ ጋራ ኪዳን እገባለሁ፤ ከዚህ ቀደም በዓለም ሁሉ ለየትኛውም ሕዝብ ከቶ ያልተደረገ፣ በሕዝብህ ሁሉ ፊት ድንቅ አደርጋለሁ፤ በመካከላቸው ዐብረሃቸው የምትኖር ሕዝብ እኔ እግዚአብሔር ለአንተ የማደርግልህ ሥራ የቱን ያህል አስፈሪ እንደ ሆነ ያያሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም እንዲህ አለው፦ “እነሆ እኔ ቃል ኪዳን አደርጋለሁ፤ በምድር ሁሉና በአሕዛብ ሁሉ ዘንድ እንደ እርሱ ያለ ከቶ ያልተደረገ ተአምራት ፊት አደርጋለሁ፤ እኔ በአንተ የምሠራው ነገር የሚያስፈራ ነውና በመካከላቸው የምትኖርባቸው ሕዝብ ሁሉ የጌታን ሥራ ያያል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፦ “እነሆ ከእስራኤል ሕዝብ ጋር ቃል ኪዳን እገባለሁ፤ ከዚህ በፊት በምድር ላይ በማንኛውም ሕዝብ ዘንድ ሆኖ የማያውቅ ድንቅ ነገር በሕዝብህ ፊት አደርጋለሁ፤ አስፈሪ የሆነ ድንቅ ነገር ስለማደርግ እኔ እግዚአብሔር የማደርጋቸውን ድንቅ ነገሮች በመካከላቸው የምትኖርባቸው ሕዝቦች ሁሉ ያያሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም አለው፦ እነሆ እኔ ቃል ኪዳን አደርጋለሁ፤ በምድር ሁሉ፥ በአሕዛብም ሁሉ ዘንድ እንደ እርሱ ያለ ከቶ ያልተደረገውን ተአምራት በሕዝብህ ሁሉ ፊት አደርጋለሁ፤ እኔም በአንተ ዘንድ የምሠራው ነገር የሚያስፈራ ነውና አንተ ያለህበት ይህ ሕዝብ ሁሉ የእግዚአብሔርን ሥራ ያያል። |
ለእርሱ ለራሱ እንዲሆን ሕዝብን ይቤዥ ዘንድ ለእርሱ ለራሱም ታላቅ ስምን ያደርግ ዘንድ አሕዛብንና ሰፈሮቻቸውን በመበተን ከግብፅ በተቤዠኸው ሕዝብህ ፊት ታምራትንና ድንቅን ያደርግ ዘንድ እግዚአብሔር እንደ መራው እንደ ሕዝብህ እንደ እስራኤል ያለ በምድር ላይ ምን ሕዝብ አለ?
እግዚአብሔርም ሙሴን፥ “በእነዚህ ቃሎች ከአንተና ከእስራኤል ጋር ቃል ኪዳን አድርጌአለሁና እነዚህን ቃሎች ጻፍ” አለው።
በዚያም አርባ ቀንና አርባ ሌሊት በእግዚአብሔር ፊት ነበረ፤ እንጀራም አልበላም፤ ውኃም አልጠጣም። በጽላቱም ዐሥሩን የቃል ኪዳን ቃሎች ጻፈ።
በምልክትና በድንቅ ነገር፥ በብርቱ እጅና በተዘረጋች ክንድ፥ በታላቅም ግርማ ሕዝብህን እስራኤልን ከግብፅ ምድር አወጣህ።
ዐይኖችህ ያዩአቸውን እነዚህን ታላላቆች የከበሩትን ነገሮች ያደረገልህ እርሱ መመኪያችሁ ነው፤ እርሱም አምላክህ ነው።
አንዱ ሽሁን እንዴት ያሳድዳቸዋል? ሁለቱስ ዐሥሩን ሽህ እንዴት ያባርሩአቸዋል? እግዚአብሔር ፍዳውን አምጥቶባቸዋልና። አምላካችንም አሳልፎ ሰጥቶአቸዋልና።
እግዚአብሔርም ሊያጠፋችሁ ከተቈጣባችሁ ከቍጣውና ከመዓቱ የተነሣ ፈራሁ፤ እግዚአብሔርም በዚያን ጊዜ ደግሞ ሰማኝ።
ሕዝቡም ጮኹ፥ ካህናቱም ቀንደ መለከቱን ነፉ፤ ሕዝቡም የቀንደ መለከቱን ድምፅ በሰሙ ጊዜ ታላቅ ጩኸት ጮኹ፤ ቅጥሩም ወደቀ፤ ሕዝቡም ሁሉ ወደ ከተማዪቱ ገቡ፤ ሁሉም ወደ ፊታቸው ወደ ከተማዪቱ ሮጡ፤ ከተማዪቱንም እጅ አደረጉ።