Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘፀአት 34:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 እርሱም እንዲህ አለው፦ “እነሆ እኔ ቃል ኪዳን አደርጋለሁ፤ በምድር ሁሉና በአሕዛብ ሁሉ ዘንድ እንደ እርሱ ያለ ከቶ ያልተደረገ ተአምራት ፊት አደርጋለሁ፤ እኔ በአንተ የምሠራው ነገር የሚያስፈራ ነውና በመካከላቸው የምትኖርባቸው ሕዝብ ሁሉ የጌታን ሥራ ያያል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ከዚያም እግዚአብሔር እንዲህ አለ፤ “ከአንተ ጋራ ኪዳን እገባለሁ፤ ከዚህ ቀደም በዓለም ሁሉ ለየትኛውም ሕዝብ ከቶ ያልተደረገ፣ በሕዝብህ ሁሉ ፊት ድንቅ አደርጋለሁ፤ በመካከላቸው ዐብረሃቸው የምትኖር ሕዝብ እኔ እግዚአብሔር ለአንተ የማደርግልህ ሥራ የቱን ያህል አስፈሪ እንደ ሆነ ያያሉ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፦ “እነሆ ከእስራኤል ሕዝብ ጋር ቃል ኪዳን እገባለሁ፤ ከዚህ በፊት በምድር ላይ በማንኛውም ሕዝብ ዘንድ ሆኖ የማያውቅ ድንቅ ነገር በሕዝብህ ፊት አደርጋለሁ፤ አስፈሪ የሆነ ድንቅ ነገር ስለማደርግ እኔ እግዚአብሔር የማደርጋቸውን ድንቅ ነገሮች በመካከላቸው የምትኖርባቸው ሕዝቦች ሁሉ ያያሉ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “እነሆ፥ እኔ በሕ​ዝ​ብህ ፊት ሁሉ ቃል ኪዳን አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ በም​ድር ሁሉ፥ በአ​ሕ​ዛ​ብም ሁሉ ዘንድ እንደ እርሱ ያለ ከቶ ያል​ተ​ደ​ረ​ገ​ውን ታላቅ ተአ​ም​ራ​ትን አደ​ር​ግ​ል​ሃ​ለሁ፤ እኔም የማ​ደ​ር​ግ​ልህ ነገር ድንቅ ነውና አንተ በመ​ካ​ከሉ ያለ​ህ​በት ይህ ሕዝብ ሁሉ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሥራ ያያል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 እርሱም አለው፦ እነሆ እኔ ቃል ኪዳን አደርጋለሁ፤ በምድር ሁሉ፥ በአሕዛብም ሁሉ ዘንድ እንደ እርሱ ያለ ከቶ ያልተደረገውን ተአምራት በሕዝብህ ሁሉ ፊት አደርጋለሁ፤ እኔም በአንተ ዘንድ የምሠራው ነገር የሚያስፈራ ነውና አንተ ያለህበት ይህ ሕዝብ ሁሉ የእግዚአብሔርን ሥራ ያያል።

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 34:10
28 Referencias Cruzadas  

ዐይኖችህ ያዩትን እነዚህን ታላላቅና የሚያስፈሩ ነገሮችን ያደረገልህ እርሱ ክብርህ ነው፥ እርሱ አምላክህ ነው።


አቤቱ፥ መንገድህ በመቅደስ ውስጥ ነው፥ እንደ እግዚአብሔር ያለ ታላቅ አምላክ ማን ነው?


ያልተጠባበቅነውን የክብርህን ሥራ ባደረግህ ጊዜ፥ አንተ ወረድህ፥ ተራሮችም በፊትህ ተንቀጠቀጡ።


ኑ የእግዚአብሔርንም ሥራ እዩ፥ ከሰው ልጆች ይልቅ በግብሩ ግሩም ነው።


በምልክትና በድንቅ ነገር፥ በብርቱ እጅና በተዘረጋች ክንድ በታላቅም ግርማ ሕዝብህን እስራኤልን ከግብጽ ምድር አወጣህ።


ለራሱ ሕዝብ ይሆን ዘንድ ሊታደገው፥ እግዚአብሔር በፊቱ እንደሄደለት ሕዝብ፥ ለራሱም ስም ያደርግ ዘንድ አሕዛብንና አማልክቶቻቸውን ከፊቱ አሳዶ ታላቅና አስፈሪ ታምራት እንዳደረገለትና ከግብጽም እንደ ተቤዠው እንደ ሕዝብህ እንደ እስራኤል ያለ በምድር ላይ ማን አለ?


በግብጽ አገርና በጾዓን አገር በአባቶቻቸው ፊት የሠራውን ተኣምራት።


እግዚአብሔርን እንዲህ በሉት፦ “ሥራህ እንዴት ግሩም ነው፥ ኃይልህ ብዙ ሲሆን ጠላቶች ዋሹብህ።


እርሱ አንባቸው ካልሸጣቸው፥ ጌታም አሳልፎ ካልሰጣቸው፥ እንዴት አንዱ ሺህን ያሳድዳል? ሁለቱስ እንዴት ዐሥር ሺህ ያባርራሉ?


ሕዝቡም ጮኹ፥ ካህናቱም ቀንደ መለከቱን ነፉ፤ ሕዝቡም የቀንደ መለከቱን ድምፅ በሰሙ ጊዜ ታላቅ ጩኸት ጮኹ፥ ቅጥሩም ወደቀ፤ ሕዝቡም ሁሉ እያንዳንዱ በቀጥታ አቅንቶ ወደ ከተማይቱ ወጣ፥ ከተማይቱንም ያዝዋት።


ጌታም ሙሴን፦ “በእነዚህ ቃሎች መጠን ከአንተና ከእስራኤል ጋር ቃል ኪዳን አድርጌአለሁና እነዚህን ቃሎች ጻፍ” አለው።


የግርማህንም ኃይል ይናገራሉ፥ ታላቅነትህንም ይነጋገራሉ፥ ብርታትህንም ይነጋገራሉ።


ለአምላካችሁ ለእግዚአብሔር ስእለትን ክፈሉ፥ በዙሪያው ያሉ ሁሉ ለሚያስፈራው እጅ መንሻን ያስገቡ።


አንተ የመረጥኸው በአደባባዮችህም ለማደር የተቀበልኸው ምስጉን ነው፥ ከቤትህ፥ ከቅዱስ መቅደስህ፥ በረከት እንጠግባለን።


ለሌሎች አሕዛብ ሁሉ እንዲህ አላደረገም፥ ፍርዱንም አልገለጠላቸውም። ሃሌ ሉያ።


እንድታደርጉትም ያዘዛችሁን ቃል ኪዳኑን፥ ዓሥሩን ትእዛዝ፥ ገለጸላችሁ፤ በሁለት የድንጋይ ጽላቶች ላይም ጻፋቸው።


ለእግዚአብሔር ክብርን ስጡ፥ ግርማው በእስራኤል ላይ፥ ኃይሉም በደመናት ላይ ነው።


በዚያም አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ከጌታ ጋር ነበረ፤ ምግብ አልበላም፥ ውኃም አልጠጣም። በጽላቶቹም ዓሥሩን የቃል ኪዳን ቃሎች ጻፈ።


እግዚአብሔር ሊያጠፋችሁ በመነሳቱ ከቁጣውና ከመዓቱ የተነሣ ፈራሁ። ጌታ ግን ልመናዬን ደግሞ ሰማኝ።


ብቻውን ተኣምራትን የሚያደርግ የእስራኤል አምላክ ጌታ ይባረክ።


ብቻውን ታላቅ ተኣምራትን ያደረገውን፥ ፍቅሩ ለዘለዓለም ነውና፥


ከግብጽ ምድር እንደ ወጣህበት ዘመን ተአምራትን አሳየዋለሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios