Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መዝሙር 68:35 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

35 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጽዮ​ንን አድ​ኗ​ታ​ልና፥ የይ​ሁ​ዳም ከተ​ሞች ይሠ​ራ​ሉና፤ በዚ​ያም ይቀ​መ​ጣሉ ይወ​ር​ሷ​ታ​ልም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

35 እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ በመቅደስህ ድንቅ ነህ፤ የእስራኤል አምላክ ለሕዝቡ ኀይልና ብርታትን ይሰጣል። እግዚአብሔር ይባረክ!

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

35 ለእግዚአብሔር ክብርን ስጡ፥ ግርማው በእስራኤል ላይ፥ ኃይሉም በደመናት ላይ ነው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

35 የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ከመቅደሱ በሚገለጥበት ጊዜ እጅግ ያስፈራል፤ እርሱ ለሕዝቡ ብርታትንና ኀይልን ይሰጣል። እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን!

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 68:35
23 Referencias Cruzadas  

ልቅ​ሶ​ዬን መል​ሰህ ደስ አሰ​ኘ​ኸኝ። ማቄን ቀድ​ደህ ደስ​ታን አስ​ታ​ጠ​ቅ​ኸኝ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሥራ ታዩ ዘንድ ኑ። ምክሩ ከሰው ልጆች ይልቅ ግሩም ነው።


በፍ​ጹም ኀይል፥ በክ​ብሩ ጽናት፥ በፍ​ጹም ትዕ​ግ​ሥት፥ በተ​ስ​ፋና በደ​ስ​ታም ጸን​ታ​ችሁ።


ለደ​ካ​ሞች ኀይ​ልን ይሰ​ጣል፤ መከራ የሚ​ቀ​በ​ሉ​ት​ንም አያ​ሳ​ዝ​ና​ቸ​ውም።


በሚ​ያ​ስ​ች​ለኝ በክ​ር​ስ​ቶስ ሁሉን እች​ላ​ለሁ።


አቤቱ፥ አሕ​ዛብ ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ሃል። አሕ​ዛብ ሁሉ ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ሃል።


በአምላካቸው በእግዚአብሔር አበረታቸዋለሁ፥ በስሙም ይመካሉ፥ ይላል እግዚአብሔር።


“አቤቱ የሰ​ማይ አም​ላክ ሆይ፥ ለሚ​ወ​ድ​ዱ​ህና ትእ​ዛ​ዝ​ህን ለሚ​ያ​ደ​ርጉ ቃል ኪዳ​ን​ንና ምሕ​ረ​ትን የም​ት​ጠ​ብቅ፥ ታላ​ቅና የተ​ፈ​ራህ አም​ላክ ሆይ፥


እንደ ጌት​ነቱ ምላት ይሰ​ጣ​ችሁ ዘንድ፥ በመ​ን​ፈስ ቅዱ​ስም ኀይል ያጸ​ና​ችሁ ዘንድ።


የሚ​ና​ገሩ ከሆነ ከጥ​ንት ጀምሮ ይህን ምስ​ክ​ር​ነት ያደ​ረገ ማን እንደ ሆነ በአ​ን​ድ​ነት ያውቁ ዘንድ ይቅ​ረቡ። ያሳ​የ​ሁም የተ​ና​ገ​ር​ሁም እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አይ​ደ​ለ​ሁ​ምን? ከእ​ኔም በቀር ሌላ አም​ላክ የለም፤ እኔ ጻድቅ አም​ላ​ክና መድ​ኀ​ኒት ነኝ፥ እንደ እኔም ያለ ማንም የለም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ተስፋ የሚ​ያ​ደ​ር​ጉና የሚ​ታ​ገሡ ግን ኀይ​ላ​ቸ​ውን ያድ​ሳሉ፤ እንደ ንስር ክንፍ ያወ​ጣሉ፤ ይሮ​ጣሉ፤ አይ​ታ​ክ​ቱ​ምም፤ ይሄ​ዳሉ፤ አይ​ራ​ቡ​ምም።


በም​ግ​ባ​ር​ህም ሁሉ እና​ገ​ራ​ለሁ፥ በሥ​ራ​ህም እጫ​ወ​ታ​ለሁ።


ለም​ድር ሁሉ ደስ​ታን የሚ​ያ​ዝዝ፥ የጽ​ዮን ተራ​ራ​ዎች በመ​ስዕ በኩል ናቸው። የታ​ላቁ ንጉሥ ከተማ ናት።


ፈሳሽ ወንዝ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ከተማ ደስ ያሰ​ኛል፤ ልዑል ማደ​ሪ​ያ​ውን ቀደሰ።


ጫማህ ብረ​ትና ናስ ይሆ​ናል፤ እንደ ዕድ​ሜህ እን​ዲሁ ኀይ​ልህ ይሆ​ናል።


በዚያ ጊዜም ሙሴና የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ይህን መዝ​ሙር ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘመሩ፤ እን​ዲ​ህም ብለው ተና​ገሩ፦ “ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዘ​ም​ራ​ለን፤ በክ​ብር እጅግ ከፍ ከፍ ብሎ​አ​ልና፤ ፈረ​ሱ​ንና ፈረ​ሰ​ኛ​ውን በባ​ሕር ጣለ።


እንደ ፍቁሩ አም​ላክ ማንም የለም፤ በሰ​ማይ የሚ​ኖ​ረው፥ በጠ​ፈ​ርም በታ​ላ​ቅ​ነት ያለው እርሱ ረዳ​ትህ ነው።


ከሰ​ሜን እንደ ወርቅ የሚ​ያ​በራ ደመና ይወ​ጣል፤ በዚ​ህም ሁሉን የሚ​ችል የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታላቅ ክብ​ርና ምስ​ጋና አለ።


አቤቱ፥ ተቀ​ብ​ለ​ኸ​ኛ​ልና፥ የጠ​ላ​ቶቼ መዘ​ባ​በቻ አላ​ደ​ረ​ግ​ኸ​ኝ​ምና አመ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ለሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios