La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፀአት 24:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ሙሴም የደ​ሙን እኵ​ሌታ ወስዶ በቆሬ ውስጥ አደ​ረ​ገው፤ የደ​ሙ​ንም እኵ​ሌታ በመ​ሠ​ዊ​ያው ረጨው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ሙሴ የደሙን እኩሌታ ወስዶ በጐድጓዳ ሳሕኖች አኖረው፤ የቀረውንም እኩሌታ በመሠዊያው ላይ ረጨው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ሙሴም የደሙን እኩሌታ ወስዶ በጎድጓዳ ሣህኖች ውስጥ አደረገው፤ የደሙንም እኩሌታ በመሠዊያው ላይ ረጨው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ሙሴም ከእንስሶቹ ደም ከፊሉን ወስዶ በገበቴ ውስጥ አኖረው፤ እኩሌታውንም በመሠዊያው ፊት ረጨው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ሙሴም የደሙን እኵሌታ ወስዶ በቆሬ ውስጥ አደረገው፤ የደሙንም እኵሌታ በመሠዊያው ረጨው።

Ver Capítulo



ዘፀአት 24:6
22 Referencias Cruzadas  

የገ​ባ​ላ​ቸ​ው​ንም ቃል ኪዳን ሁሉ አል​ጠ​በ​ቁም። ከንቱ ነገ​ር​ንም ተከ​ተሉ፤ ከን​ቱም ሆኑ፤ እንደ እነ​ር​ሱም እን​ዳ​ይ​ሠሩ ያዘ​ዛ​ቸ​ውን በዙ​ሪ​ያ​ቸው ያሉ​ትን አሕ​ዛብ ተከ​ተሉ።


ከሂ​ሶጵ ቅጠ​ልም ጭብጥ ውሰዱ፤ በዕቃ ውስጥ ባለ​ውም ደም ንከ​ሩት፤ በዕ​ቃ​ውም ውስጥ ከአ​ለው ደም ሁለ​ቱን መቃ​ኖ​ችና ጉበ​ኑን እርጩ፤ ከእ​ና​ን​ተም አንድ ሰው እስ​ኪ​ነጋ ድረስ ከቤቱ ደጅ አይ​ውጣ።


ከደ​ሙም ወስ​ደው በሚ​በ​ሉ​በት ቤት ሁለ​ቱን መቃ​ንና ጉበ​ኑን ይቅ​ቡት።


ሙሴም ደሙን ወስዶ በሕ​ዝቡ ላይ ረጨው፤ በዚህ ቃል ሁሉ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ና​ንተ ጋር ያደ​ረ​ገው የቃል ኪዳኑ ደም እነሆ” አለ።


አው​ራ​ው​ንም በግ ታር​ደ​ዋ​ለህ፤ ደሙ​ንም ወስ​ደህ በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ በዙ​ሪ​ያው ትረ​ጨ​ዋ​ለህ።


አው​ራ​ው​ንም በግ ታር​ደ​ዋ​ለህ፤ ደሙ​ንም ትወ​ስ​ዳ​ለህ፤ የአ​ሮ​ን​ንም የቀኝ ጆሮ ጫፍ፥ የቀኝ እጁ​ንና የቀኝ እግ​ሩን አውራ ጣት ጫፍ፥ የል​ጆ​ቹ​ንም የቀኝ ጆሮ​አ​ቸ​ውን ጫፍ፥ የቀኝ እጃ​ቸ​ው​ንና የቀኝ እግ​ራ​ቸ​ውን አውራ ጣት ታስ​ነ​ካ​ለህ፤ ደሙ​ንም በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ በዙ​ሪ​ያው ትረ​ጨ​ዋ​ለህ።


ከግ​ብፅ ሀገር አወ​ጣ​ቸው ዘንድ እጃ​ቸ​ውን በያ​ዝ​ሁ​በት ቀን ከአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ጋር እንደ ገባ​ሁት ያለ ቃል ኪዳን አይ​ደ​ለም፤ እነ​ርሱ በኪ​ዳኔ አል​ጸ​ኑ​ምና፥ እኔም ቸል አል​ኋ​ቸው፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


በመ​ሠ​ዊ​ያ​ውም አጠ​ገብ በመ​ስዕ በኩል በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያር​ዱ​ታል፤ የአ​ሮ​ንም ልጆች ካህ​ናቱ ደሙን በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ በዙ​ሪ​ያው ይረ​ጩ​ታል።


በሬ​ው​ንም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያር​ደ​ዋል፤ የአ​ሮ​ንም ልጆች ካህ​ናቱ ደሙን ያቀ​ር​ባሉ፤ ደሙ​ንም በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ ፊት ባለው በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ በዙ​ሪ​ያው ይረ​ጩ​ታል።


እጁ​ንም ለቍ​ር​ባን በቀ​ረ​በው ራስ ላይ ይጭ​ናል፤ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ አጠ​ገብ ያር​ደ​ዋል፤ የአ​ሮ​ንም ልጆች ካህ​ናቱ ደሙን በሚ​ቃ​ጠ​ለው መሥ​ዋ​ዕት፥ በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ በዙ​ሪ​ያው ይረ​ጩ​ታል።


እጁ​ንም ለቍ​ር​ባን በቀ​ረ​በው ራስ ላይ ይጭ​ናል በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ ያር​ደ​ዋል፤ ካህ​ና​ቱም የአ​ሮን ልጆች ደሙን በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ በዙ​ሪ​ያው ይረ​ጩ​ታል።


ካህ​ኑም ጣቱን በደሙ ውስጥ ነክሮ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በመ​ቅ​ደሱ መጋ​ረጃ ፊት ደሙን ሰባት ጊዜ ይረ​ጨ​ዋል።


እን​ዲ​ሁም ኅብ​ስ​ቱን ከተ​ቀ​በሉ በኋላ ጽዋ​ውን አን​ሥቶ፥ “አዲስ ሥር​ዐት የሚ​ጸ​ና​በት ይህ ጽዋ ደሜ ነው እን​ዲህ አድ​ርጉ፤ በም​ት​ጠ​ጡ​በ​ትም ጊዜ አስ​ቡኝ” አላ​ቸው።


ሁሉ​ንም በእ​ርሱ ይቅር ይለው ዘንድ በመ​ስ​ቀሉ ባፈ​ሰ​ሰው ደም በም​ድ​ርና በሰ​ማ​ያት ላሉ ሰላ​ምን አደ​ረገ።


የአ​ዲስ ኪዳ​ንም መካ​ከ​ለኛ ወደ​ሚ​ሆን ወደ ኢየ​ሱስ፥ ከአ​ቤ​ልም ደም ይልቅ የሚ​ሻ​ለ​ውን ወደ​ሚ​ና​ገር ወደ ተረ​ጨው ደሙ ደር​ሳ​ች​ኋል።


እጃ​ቸ​ውን ይዤ ከም​ድረ ግብፅ ባወ​ጣ​ኋ​ቸው ጊዜ ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው እንደ ገባ​ሁት እን​ደ​ዚያ ያለ ኪዳን አይ​ደ​ለም፤ እነ​ርሱ በኪ​ዳኔ አል​ኖ​ሩ​ምና፤ እኔም ቸል ብያ​ቸ​ዋ​ለ​ሁና” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ስለ​ዚ​ህም ፊተ​ኛው ኪዳን እንኳ ያለ ደም አል​ከ​በ​ረም።


ሙሴ የኦ​ሪ​ትን ትእ​ዛዝ ሁሉ ለመ​ላው ሕዝብ ከነ​ገረ በኋላ፥ የላ​ምና የፍ​የል ደም ከውኃ ጋር ቀላ​ቅሎ፥ ቀይ የበግ ጠጕ​ርና የስ​ሚዛ ቅጠል ነክሮ መጽ​ሐፈ ኦሪ​ቱ​ንና ሕዝ​ቡን ሁሉ ይረጭ ነበር።


ድን​ኳ​ኑ​ንና የመ​ገ​ል​ገ​ያ​ውን ዕቃ ሁሉ በደሙ ይረጭ ነበር።