ሰሎሞንም በየዓመቱ ሦስት ጊዜ የሚቃጠለውንና የሰላሙን መሥዋዕት ለእግዚአብሔር በሠራው መሠዊያ ላይ ያሳርግ ነበር፤ በእግዚአብሔርም ፊት ባለው መሠዊያ ላይ ዕጣን ያሳርግ ነበር፤ ቤቱንም ጨረሰ።
ዘፀአት 23:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “በዓመት ሦስት ጊዜ በዓል አድርጉልኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “በዓመት ሦስት ጊዜ ለእኔ በዓልን ታከብራላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “በዓመት ሦስት ጊዜ ለእኔ በዓልን ታደርግልኛለህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እኔን የምታከብሩባቸው በዓመት ሦስት በዓላት ይኑሩአችሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዓመት ሦስት ጊዜ በዓል ታደርግልኛለህ። |
ሰሎሞንም በየዓመቱ ሦስት ጊዜ የሚቃጠለውንና የሰላሙን መሥዋዕት ለእግዚአብሔር በሠራው መሠዊያ ላይ ያሳርግ ነበር፤ በእግዚአብሔርም ፊት ባለው መሠዊያ ላይ ዕጣን ያሳርግ ነበር፤ ቤቱንም ጨረሰ።
ሙሴም እንዳዘዘ እንደ ሥርዐታቸው በየቀኑ ሁሉ፥ በየሰንበታቱም፥ በየመባቻዎቹም፥ በየበዓላቱም፥ በየዓመቱ ሦስት ጊዜ በየቂጣው በዓልና በየሰባቱ ሱባዔ በዓል፥ በየዳሱም በዓል ቍርባን ያቀርቡ ነበር።
“የቂጣውን በዓል ትጠብቀዋለህ። በሚያዝያ ወር ከግብፅ ወጥተሃልና በታዘዘው ዘመን በሚያዝያ ወር እንዳዘዝሁህ ሰባት ቀን ቂጣ ብላ።
“የሀገሩ ሕዝብ ግን በየክብረ በዓሉ ቀን ወደ እግዚአብሔር ፊት በመጡ ጊዜ በሰሜን በር በኩል ሊሰግድ የሚገባው በደቡብ በር በኩል ይውጣ፤ በደቡብም በር የሚገባው በሰሜን በር በኩል ይውጣ፤ በፊት ለፊት ይውጣ እንጂ በገባበት በር አይመለስ።
“ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ በዚህ በሰባተኛው ወር ከዐሥራ አምስተኛው ቀን ጀምሮ ሰባት ቀን ለእግዚአብሔር የዳስ በዓል ይሆናል።
“በሚያዝያ ወር ከግብፅ ሀገር በሌሊት ወጥተሃልና የሚያዝያን ወር ጠብቀህ፥ የአምላክህ የእግዚአብሔርን ፋሲካ አድርግ።
በዓመት ሦስት ጊዜ በቂጣ በዓል፥ በሰባቱ ሱባዔም በዓል፥ በዳስም በዓል ወንድ ልጅህ ሁሉ በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት እግዚአብሔር በመረጠው ስፍራ ይታይ፤
ያም ሰው በሴሎ ይሰግድ ዘንድ፥ ለሠራዊት ጌታም ለእግዚአብሔር ይሠዋ ዘንድ ከከተማው ከአርማቴም በየዓመቱ ይወጣ ነበር። የእግዚአብሔርም ካህናት ሁለቱ የዔሊ ልጆች አፍኒንና ፊንሐስ በዚያ ነበሩ።