Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘሌዋውያን 23:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 እነ​ዚህ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዓ​ላት፥ በየ​ዘ​መ​ና​ቸው የም​ታ​ው​ጁ​አ​ቸው፥ የተ​ቀ​ደሱ ጉባ​ኤ​ያት ናቸው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 “ ‘የተመረጡ የእግዚአብሔር በዓላት ብላችሁ በተወሰኑላቸው ጊዜያት የምታውጇቸው የተቀደሱ ጉባኤዎች እነዚህ ናቸው፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 “እነዚህ የጌታ በዓላት፥ ለእነርሱ በተወሰነላቸው ጊዜ የምታውጁአቸው፥ የተቀደሱ ጉባኤዎች ናቸው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ለእያንዳንዳቸው በተወሰነላቸው ጊዜ በእግዚአብሔር ፊት እየተሰበሰባችሁ የምታከብሩአቸው ዋና ዋናዎቹ በዓላት እነዚህ ናቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 እነዚህ የእግዚአብሔር በዓላት፥ በየዘመናቸው የምታውጁአቸው፥ የተቀደሰ ጉባኤ ናቸው።

Ver Capítulo Copiar




ዘሌዋውያን 23:4
9 Referencias Cruzadas  

ዕዝ​ራም አላ​ቸው፥ “ወደ ተራራ ሂዱ፤ የዘ​ይ​ትና የበ​ረሃ ወይራ፥ የባ​ር​ሰ​ነ​ትም፥ የዘ​ን​ባ​ባም፥ የለ​መ​ለ​መ​ው​ንም ዛፍ ቅር​ን​ጫፍ አምጡ፤ እንደ ተጻ​ፈ​ውም ዳሶ​ችን ሥሩ።”


ይህም ቀን መታ​ሰ​ቢያ ይሁ​ና​ችሁ፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በዓል ታደ​ር​ጉ​ታ​ላ​ችሁ፤ ለልጅ ልጃ​ች​ሁም ሥር​ዐት ሆኖ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ታደ​ር​ጉ​ታ​ላ​ችሁ።


“በዓ​መት ሦስት ጊዜ በዓል አድ​ር​ጉ​ልኝ።


ዳዊት ለሰ​ፈ​ረ​ባት ከተማ ለአ​ር​ኤል ወዮ​ላት! የዓ​መ​ቱን አዝ​መራ ሰብ​ስቡ፤ ከሞ​ዓብ ጋር ትበ​ላ​ላ​ች​ሁና።


ክር​ክ​ርም በሆነ ጊዜ ለመ​ፍ​ረድ ይቁሙ፤ እንደ ፍርዴ ይፍ​ረዱ፤ በበ​ዓ​ላቴ ሁሉ ሕጌ​ንና ሥር​ዐ​ቴን ይጠ​ብቁ፤ ሰን​በ​ታ​ቴ​ንም ይቀ​ድሱ።


“ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እን​ዲህ ብለህ ንገ​ራ​ቸው፦ ቅዱ​ሳት ጉባ​ኤ​ያት ብላ​ችሁ የም​ት​ጠ​ሩ​አ​ቸው በዓ​ላቴ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዓ​ላት እነ​ዚህ ናቸው።


ያች​ንም ቀን ቅድ​ስት ጉባኤ ብላ​ችሁ ታው​ጃ​ላ​ችሁ፤ የተ​ግ​ባር ሥራ ሁሉ አታ​ድ​ር​ጉ​ባት፤ በም​ት​ቀ​መ​ጡ​በት ሀገር ሁሉ ለልጅ ልጃ​ችሁ የዘ​ለ​ዓ​ለም ሥር​ዐት ነው።


“የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት፥ የእ​ህ​ሉ​ንም ቍር​ባን፥ መሥ​ዋ​ዕ​ቱ​ንም፥ የመ​ጠ​ጡ​ንም ቍር​ባን፥ በየ​ቀኑ የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቀ​ር​ቡ​ባ​ቸው ዘንድ የተ​ቀ​ደሱ በዓ​ላት እን​ዲ​ሆኑ የም​ታ​ው​ጁ​አ​ቸው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዓ​ላት እነ​ዚህ ናቸው።


እነሆ፥ የምስራችን የሚያመጣ ሰላምንም የሚያወራ ሰው እግር በተራሮች ላይ ነው! ይሁዳ ሆይ፥ አጥፊው ፈጽሞ ጠፍቶአልና፥ ከእንግዲህም ወዲህ በአንተ ዘንድ አያልፍምና ዓመት በዓሎችህን አድርግ፥ ስእለቶችህን ክፈል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos