Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘፀአት 23:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 “በዓመት ሦስት ጊዜ ለእኔ በዓልን ታደርግልኛለህ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 “በዓመት ሦስት ጊዜ ለእኔ በዓልን ታከብራላችሁ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 “እኔን የምታከብሩባቸው በዓመት ሦስት በዓላት ይኑሩአችሁ፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 “በዓ​መት ሦስት ጊዜ በዓል አድ​ር​ጉ​ልኝ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 በዓመት ሦስት ጊዜ በዓል ታደርግልኛለህ።

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 23:14
14 Referencias Cruzadas  

“በዓመት ሦስት ጊዜ ወንዶች ሁሉ በቂጣ በዓል፥ በመከርንና በዳስ በዓል፥ በአምላክህ በጌታ ፊት እርሱ በመረጠው ስፍራ ይታዩ፥ በጌታም ፊት ባዶ እጃቸውን አይታዩ።


“ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ተናገር፦ በዚህ በሰባተኛው ወር ከዐሥራ አምስተኛው ቀን ጀምሮ ሰባት ቀን ለጌታ የዳስ በዓል ነው።


እስከ ሰባተኛ ሰንበት ማግስት ድረስ ኀምሳ ቀን ቁጠሩ። ከዚያም አዲሱን የእህል ቁርባን ለጌታ አቅርቡ።


በመጀመሪያው ወር በዓሥራ አራተኛው ቀን ሲመሽ የጌታ ፋሲካ ነው።


በዓመት ሦስት ጊዜ ወንድ ሁሉ በጌታ በእግዚአብሔር ፊት ይታይ።


“እነዚህ የጌታ በዓላት፥ ለእነርሱ በተወሰነላቸው ጊዜ የምታውጁአቸው፥ የተቀደሱ ጉባኤዎች ናቸው።


ያም ሰው በየዓመቱ ለሠራዊት ጌታ ለመስገድና መሥዋዕት ለመሠዋት ከሚኖርበት ከተማ ወደ ሴሎ ይወጣ ነበር። በዚያም ሁለቱ የዔሊ ልጆች ሖፍኒና ፊንሐስ የጌታ ካህናት ነበሩ።


ሰሎሞን ለእግዚአብሔር ባሠራው መሠዊያ ላይ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የኅብረት መሥዋዕት በዓመት ሦስት ጊዜ ያቀርብ ነበር፤ ከዚህም ሁሉ ጋር ለእግዚአብሔር ዕጣን ያሳርግ ነበር፤ በዚህም ዓይነት የቤተ መቅደሱ ሥራ ተፈጸመ።


ሙሴም እንዳዘዘ እንደ ሥርዓታቸው ዘወትር በየቀኑ፥ በየሰንበታቱም፥ በየመባቻዎቹም፥ በየተወሰኑትም በዓላት፥ በየዓመቱ ሦስት ጊዜ በየቂጣው በዓልና በየሰባቱ ሱባዔ በዓል በየዳሱም በዓል ቁርባን ያቀርቡ ነበር።


ቀልጠው የተሠሩ የአማልክት ምስሎች ለአንተ አታድርግ።


“የቂጣውን በዓል ጠብቀው፤ በአቢብ ወር ከግብጽ ወጥተሃልና በተወሰነው ጊዜ በአቢብ ወር እንዳዘዝሁህ ሰባት ቀን ቂጣ ብላ።


“አምላክህ ጌታ በአቢብ ወር ከግብጽ በሌሊት ስላወጣህ፥ የአቢብን ወር ጠብቅ፤ የአምላክህን የጌታ ፋሲካ አክብርበት።


የምድሪቱ ሕዝብ ግን በየክብረ በዓሉ ቀን ወደ ጌታ ፊት በመጡ ጊዜ በሰሜን በር በኩል ሊሰግድ የገባው በደቡብ በር በኩል ይውጣ፥ በደቡብ በር የገባው በሰሜን በር በኩል ይውጣ፤ በፊት ለፊት ባለው ይውጣ እንጂ በገባበት በር አይመለስ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios