ነገር ግን በታላቅ ኀይል በተዘረጋችም ክንድ ከግብፅ ምድር ያወጣችሁን እግዚአብሔርን እርሱን ፍሩ፤ ለእርሱም ስገዱ፤ ለእርሱም ሠዉ።
ዘዳግም 6:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከግብፅ ምድር ከባርነት ቤት ያወጣህን እግዚአብሔርን እንዳትረሳ ተጠንቀቅ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከባርነት ምድር ከግብጽ ያወጣህን እግዚአብሔርን እንዳትረሳ ተጠንቀቅ! መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያን ጊዜ ከግብጽ ምድር ከባርነት ቤት ያወጣህን ጌታ እንዳትረሳ ተጠንቀቅ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ባሪያ ሆነህ ትኖርባት ከነበረችው ከግብጽ ምድር ያወጣህን እግዚአብሔርን እንዳትረሳ ጥንቃቄ አድርግ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያን ጊዜ ከግብፅ ምድር ከባርነት ቤት ያወጣህን እግዚአብሔርን እንዳትረሳ ተጠንቀቅ። |
ነገር ግን በታላቅ ኀይል በተዘረጋችም ክንድ ከግብፅ ምድር ያወጣችሁን እግዚአብሔርን እርሱን ፍሩ፤ ለእርሱም ስገዱ፤ ለእርሱም ሠዉ።
እንዲህም ይሆናል፤ ከዚህ በኋላ ልጅህ፦ ‘ይህ ምንድን ነው?’ ብሎ በጠየቀህ ጊዜ እንዲህ ትለዋለህ፦ እግዚአብሔር በብርቱ እጅ ከባርነት ቤት ከግብፅ ምድር አወጣን፤
ሙሴም ሕዝቡን አለ፥ “ከባርነት ቤት ከግብፅ የወጣችሁባትን ይህችን ቀን ዐስቡ፤ እግዚአብሔር ከዚህ ቦታ በበረታች እጅ አውጥቶአችኋልና። ስለዚህ የቦካ እንጀራ አትብሉ።
ስለዚህም ፈጥነህ ለእስራኤል ልጆች እንዲህ በላቸው፥ “እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ ከግብፃውያንም ተገዥነት አወጣችኋለሁ፤ ከባርነታቸውም አድናችኋለሁ፤ በተዘረጋ ክንድ፤ በታላቅ ፍርድም እታደጋችኋለሁ፤
አዳኝህ እግዚአብሔርን ትተኸዋልና፥ ረዳትህ እግዚአብሔርንም አላስብኸውም፤ ስለዚህ የሐሰትን ተክል ተክለሃል፤ የሐሣርንም ዘር ዘርተሃል።
አንቺ ግን ሰማያትን የፈጠረውን፥ ምድርንም የመሠረታትን ፈጣሪሽን እግዚአብሔርን ረስተሻል፤ ያጠፋሽ ዘንድ ባዘጋጀ ጊዜ ከአስጨናቂው ቍጣ የተነሣ ሁልጊዜ ቀኑን ሁሉ ፈርተሻል፤ ይቈጣሽ ዘንድ መክሮአልና፤ አሁን የሚያስጨንቅሽ ቍጣው የት አለ?
“የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ አባቶቻችሁን ከባርነት ቤት ከግብፅ ሀገር በአወጣኋቸው ቀን ከእነርሱ ጋር እንዲህ ስል ቃል ኪዳን አደረግሁ፦
እኔን ረስታ ወዳጆችዋን እየተከተለች፥ በጕትቾችዋና በጌጥዋም እያጌጠች ለበኣሊም የሠዋችበትን ወራት እበቀልባታለሁ፥” ይላል እግዚአብሔር።
እርሱም በዘርፉ ይሁንላችሁ፤ ትመለከቱታላችሁም፤ የእግዚአብሔርንም ትእዛዛት ታስባላችሁ፤ ታደርጉአቸውማላችሁ፤ እነርሱን በመከተል ያመነዘራችሁባትን የሕሊናችሁንና የዐይኖቻችሁን ፈቃድ አትከተሉ።
ከእናንተ ጋር የተማማለውን የአምላካችንን የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን እንዳትረሱ፤ አምላክህ እግዚአብሔር የከለከለውን፥ በማናቸውም ቅርጽ የተቀረጸውን ምስል እንዳታደርጉ እንግዲህ ተጠንቀቁ።
“ለራስህ ዕወቅ፤ ሰውነትህን ፈጽመህ ጠብቅ፤ ዐይኖችህ ያዩትን ይህን ሁሉ ነገር አትርሳ፤ በሕይወትህ ዘመን ሁሉ ከልቡናህ አይውጣ፤ ለልጆችህና ለልጅ ልጆችህም አስተምራቸው።
ለዚህ ዓለም ስሕተት፥ በክርስቶስ ሕግ ያይደለ፥ በሰው ሠራሽ ሥርዐት ለከንቱ የሚያታልሉ ሰዎች በነገር ማራቀቅ እንዳያታልሉአችሁ፥ ተጠንቀቁ።
ከግብፅ ምድርም ያወጣቸውን የአባቶቻቸውን አምላክ እግዚአብሔርን ተዉ፤ ሌሎችንም በዙሪያቸው ያሉ የአሕዛብን አማልክት ተከተሉ፤ ሰገዱላቸውም፤ እግዚአብሔርንም አስቈጡት።