ከምድያምም ተነሥተው ወደ ፋራን ሄዱ፤ ከእነርሱም ጋር ከፋራን ሰዎችን ወሰዱ፤ ወደ ግብፅም መጡ፤ ወደ ግብፅም ንጉሥ ወደ ፈርዖን ሄዱ፤ አዴርም ወደ ፈርዖን ገባ። እርሱም ቤት ሰጥቶ ቀለብ ዳረገው።
ዘዳግም 33:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዲህም አለ፦ “እግዚአብሔር ከሲና መጣ፤ በሴይርም ተገለጠልን፤ ከፋራን ተራራ፥ ከቃዴስ አእላፋት ጋር ፈጥኖ መጣ፤ መላእክቱም ከእርሱ ጋር በቀኙ ነበሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲህም አለ፦ “እግዚአብሔር ከሲና መጣ፤ በእነርሱም ላይ ከሴይር እንደ ማለዳ ፀሓይ ወጣ፤ ከፋራን ተራራ አበራላቸው፤ ከአእላፋት ቅዱሳኑ ጋራ መጣ፤ በስተ ቀኙ የሚነድድ እሳት ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲህም አለ፦ “ጌታ ከሲና ተራራ መጣ፥ በሴይርም እንደ ንጋት ተገለጠ፥ ከፋራን ተራራ አበራላቸው፥ በስተቀኙም ከእሳት ነበልባል ጋር፥ ከአእላፋት ቅዱሳኑም ጋር መጣ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሙሴም እንዲህ አለ፦ “እግዚአብሔር ከሲና ተራራ መጣ፤ ከኤዶም ላይ እንደ ንጋት ፀሐይ አበራ፤ ከፋራንም ተራራ ላይ አንጸባረቀ፤ በስተቀኙ የእሳት ነበልባል ነበር፤ ከእርሱም ጋር አእላፍ መላእክት ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲህም አለ፦ 2 እግዚአብሔር ከሲና መጣ፥ 2 በሴይርም ተገለጠ፤ 2 ከፋራን ተራራ አበራላቸው፥ 2 ከአእላፋትም ቅዱሳኑ መጣ፤ 2 በስተቀኙም የእሳት ሕግ ነበረላቸው። |
ከምድያምም ተነሥተው ወደ ፋራን ሄዱ፤ ከእነርሱም ጋር ከፋራን ሰዎችን ወሰዱ፤ ወደ ግብፅም መጡ፤ ወደ ግብፅም ንጉሥ ወደ ፈርዖን ሄዱ፤ አዴርም ወደ ፈርዖን ገባ። እርሱም ቤት ሰጥቶ ቀለብ ዳረገው።
ስለዚያ ስለ አለፈው የፊቱ ብርሃን የእስራኤል ልጆች የሙሴን ፊት መመልከት እስኪሳናቸው ድረስ በዚያች በድንጋይ ላይ በፊደል ለተቀረጸች ለሞት መልእክት ክብር ከተደረገላት፥
በኦሪት ሕግ ያሉ ሁሉ በእርግማን ውስጥ ይኖራሉ፤ መጽሐፍ እንዲህ ብሎአልና፥ “በዚህ በኦሪት መጽሐፍ ውስጥ የተጻፈውን ሁሉ የማይፈጽምና የማይጠብቅ ርጉም ይሁን።”
ታዲያ ኦሪት ለምን ተሠራች? ኦሪትስ ኀጢአትን ታበዛት ዘንድ፥ ተስፋ ያደረገለት ያ ዘር እስኪመጣ ድረስ፥ በመላእክት በኩል በመካከለኛው እጅ ወረደች።
“እግዚአብሔር በተራራው ላይ፤ በእሳትና በጨለማ፥ በጭጋግና በዓውሎ ነፋስ መካከል ሆኖ በታላቅ ድምፅ እነዚህን ቃሎች ለጉባኤያችሁ ሁሉ ተናገረ፤ ምንም አልጨመረም። በሁለቱም የድንጋይ ጽላት ላይ ጻፋቸው፤ ለእኔም ሰጣቸው።
የተነጋገራቸውን ሊሰሙት አልተቻላቸውም ነበርና፥ “እንስሳም ያን ተራራ ቢቀርበው በድንጋይ ይወግሩት” ነበር።
ከአዳም ጀምሮ ሰባተኛ የሆነ ሄኖክ “እነሆ ጌታ በሁሉ ላይ እንዲፈርድ፥ በኀጢአተኝነትም ስላደረጉት ስለ ኀጢአተኛ ሥራቸው ሁሉ ዐመፀኞችም ኀጢአተኞች በእርሱ ላይ ስለ ተናገሩ ስለ ጭከና ነገር ሁሉ ኀጢአተኞችን ሁሉ እንዲወቅስ ከአእላፋት ቅዱሳኑ ጋር መጥቶአል፤” ብሎ ለእነዚህ ደግሞ ትንቢት ተናገረ።
አየሁም፤ በዙፋኑም በእንስሶቹም በሽማግሌዎቹም ዙሪያ የብዙ መላእክትን ድምፅ ሰማሁ፤ ቍጥራቸውም አእላፋት ጊዜ አእላፋትና ሺህ ጊዜ ሺህ ነበር፤