ዘዳግም 14:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሌዋዊዉም፥ ከአንተ ጋር ክፍልና ርስት የለውምና፥ በከተማህ ውስጥ ያለ መጻተኛ፥ ድሃ-አደግም፥ መበለትም መጥተው ይበላሉ፤ ይጠግባሉም፤ ይኸውም አምላክህ እግዚአብሔር በምታደርገው በእጅህ ሥራ ሁሉ ይባርክህ ዘንድ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህን የምታደርገው የራሱ ድርሻ ወይም ርስት የሌለው ሌዋዊና መጻተኛ፣ በከተሞችህ የሚኖሩ አባት የሌላቸውና መበለቶች መጥተው እንዲበሉና እንዲጠግቡ፣ አንተንም አምላክህ እግዚአብሔር በእጆችህ ሥራ ሁሉ እንዲባርክህ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህን የምታደርገው የራሱ ድርሻ ወይም ርስት የሌለው ሌዋዊና መጻተኛ፥ በከተሞችህ የሚኖሩ አባት የሌላቸውና መበለቶች መጥተው እንዲበሉና እንዲጠግቡ፥ አንተንም አምላክህ ጌታ በእጆችህ ሥራ ሁሉ እንዲባርክህ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በከተሞቻችሁ የሚኖሩ ከእናንተ ጋር የተካፈሉት ርስት የሌላቸው ሌዋውያን፥ የውጪ አገር ስደተኞች፥ እናትና አባት የሌላቸው የሙት ልጆችና ባሎቻቸው የሞቱባቸው መጥተው ይብሉ፤ ይህን ሁሉ ብታደርጉ አምላካችሁ እግዚአብሔር በምትሠሩት ነገር ሁሉ ይባርካችኋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሌዋዊውም፥ ከአንተ ጋር ክፍልና ርስት የለውምና፥ በአገርህም ደጅ ያለ መጻተኛ ድሀ አደግም መበለትም መጥተው ይበላሉ ይጠግባሉም፤ ይኸውም አምላክህ እግዚአብሔር በምታደርገው በእጅህ ሥራ ሁሉ ይባርክህ ዘንድ ነው። |
እናንተ በግብፅ ምድር እንግዶች ነበራችሁና፤ ወደ እናንተ የመጣ እንግዳ እንደ ሀገር ልጅ ይሁንላችሁ፤ እርሱን እንደ ራሳችሁ ውደዱት፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝና።
እግዚአብሔርም አሮንን አለው፥ “በምድራቸው ርስት አትወርስም፤ በመካከላቸውም ድርሻ አይሆንልህም፤ በእስራኤል ልጆች መካከል ድርሻህና ርስትህ እኔ ነኝ።
አሁንም ጠላቶቻችሁን ውደዱ፤ መልካምም አድርጉላቸው፤ እንዲመልሱላችሁ ተስፋ ሳታደርጉ አበድሩ፤ ዋጋችሁም ብዙ ይሆናል፤ የልዑልም ልጆች ትሆናላችሁ፤ እርሱ ለበጎዎችና ለክፉዎች ቸር ነውና።
ስለዚህ ለሌዋውያን ከወንድሞቻቸው ጋር ክፍልና ርስት የላቸውም፤ አምላክህ እግዚአብሔር እንደ ነገራቸው እግዚአብሔር ርስታቸው ነውና።
እናንተም፥ ወንዶች ልጆቻችሁና ሴቶች ልጆቻችሁም፥ ወንዶችና ሴቶች አገልጋዮቻችሁም፥ ከእናንተ ጋር ክፍልና ርስት ስለሌለው በደጆቻችሁ ውስጥ የተቀመጠው ሌዋዊም በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ፊት ደስ ይበላችሁ።
እጅህን በምትጥልበት ሁሉ አምላክህ እግዚአብሔር ስለዚህ በሥራህ ሁሉ ይባርክሃልና ፈጽመህ ስጠው፤ የለመነህንም ያህል አበድረው፤ በሰጠኸውም ጊዜ በልብህ አትጸጸት።
አንተ፥ ወንድ ልጅህና ሴት ልጅህ፥ ወንድ ባሪያህና ሴት ባሪያህ፥ በሀገርህም ውስጥ ያለው ሌዋዊ፥ በመካከልህም ያሉ መጻተኛና ድሃ-አደግ፥ መበለትም አምላክህ እግዚአብሔር በዚያ ስሙ ይጠራበት ዘንድ በሚመርጠው ስፍራ በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት ደስ ይበላችሁ።
አንተም፥ ወንድ ልጅህና ሴት ልጅህ፥ ወንድ ባሪያህና ሴት ባሪያህ፥ በሀገርህም ውስጥ ያለ ሌዋዊና መጻተኛ፥ ድሃ-አደግና መበለትም በበዓልህ ደስ ይበላችሁ።
“ለአምላክህ ለእግዚአብሔር ስእለት በተሳልህ ጊዜ አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ ፈጽሞ ይሻዋልና፥ ኀጢአትም ይሆንብሃልና መክፈሉን አታዘግይ።
እግዚአብሔር በረከቱን በአንተ ላይ፥ በጎተራህ፥ በእህልህም ሥራ ሁሉ እንዲወርድ ይልካል፤ አምላክህ እግዚአብሔር በሚሰጥህም ምድር ይባርክሃል።
ያልሞላሃቸውንም ሀብትን የሞሉ ቤቶች፥ ያልማስሃቸውንም የተማሱ ጕድጓዶች፥ ያልተከልሃቸውንም ወይንና ወይራ በሰጠህ ጊዜ፥ በበላህና በጠገብህም ጊዜ፤
ንጹሕ የሆነ ነውርም የሌለበት አምልኮ በእግዚአብሔር አብ ዘንድ ይህ ነው፤ ወላጆች የሌላቸውን ልጆች ባልቴቶችንም በመከራቸው መጠየቅ፥ በዓለምም ከሚገኝ እድፍ ሰውነቱን መጠበቅ ነው።