Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዕብራውያን 13:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 እን​ግዳ መቀ​በ​ል​ንም አት​ርሱ፤ በዚህ ምክ​ን​ያት ሳያ​ውቁ መላ​እ​ክ​ትን በእ​ን​ግ​ድ​ነት ለመ​ቀ​በል ያታ​ደሉ አሉና።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 እንግዶችን መቀበል አትርሱ፤ አንዳንዶች ይህን ሲያደርጉ፣ ሳያውቁ መላእክትን አስተናግደዋልና።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 እንግዶችን መቀበል አትርሱ፤ አንዳንዶች በዚህ ሳቢያ ሳያውቁ መላእክትን በእንግድነት ተቀብለዋል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 እንግዳ ተቀብሎ ማስተናገድን አትርሱ፤ እንደዚህ እንግዶችን እየተቀበሉ በማስተናገድ አንዳንድ ሰዎች ሳያውቁ መላእክትን ተቀብለው አስተናግደዋል።

Ver Capítulo Copiar




ዕብራውያን 13:2
21 Referencias Cruzadas  

ተርቤ አብልታችሁኛልና፤ ተጠምቼ አጠጥታችሁኛልና፤ እንግዳ ሆኜ ተቀብላችሁኛልና፤ ታርዤ አልብሳችሁኛልና፤


በቀ​ት​ርም ጊዜ አብ​ር​ሃም በድ​ን​ኳኑ ደጃፍ ተቀ​ምጦ ሳለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በመ​ምሬ ዛፍ ሥር ተገ​ለ​ጠ​ለት።


በች​ግ​ራ​ቸው ቅዱ​ሳ​ንን ለመ​ር​ዳት ተባ​በሩ፤ እን​ግዳ መቀ​በ​ል​ንም አዘ​ው​ትሩ።


ያለ ማንጐራጐር እርስ በርሳችሁ እንግድነትን ተቀባበሉ፤


እንግዳ ሆኜ አልተቀበላችሁኝምና፤ ታርዤ አላለበሳችሁኝምና፤ ታምሜ ታስሬም አልጠየቃችሁኝምና።’


ነገር ግን እንግዳ ተቀባይ፥ በጎ የሆነውን ነገር የሚወድ፥ ጠንቃቃ፥ ጻድቅ፥ ቅዱስ፥ ራሱን የሚገዛ ይሁን፤


መጻ​ተ​ኛው ግን በሜዳ አያ​ድ​ርም ነበር፥ ደጄ​ንም ለመ​ጣው ሁሉ እከ​ፍት ነበር፤


እና​ንተ በግ​ብፅ ምድር እን​ግ​ዶች ነበ​ራ​ች​ሁና፤ ወደ እና​ንተ የመጣ እን​ግዳ እንደ ሀገር ልጅ ይሁ​ን​ላ​ችሁ፤ እር​ሱን እንደ ራሳ​ችሁ ውደ​ዱት፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ ነኝና።


ንጉሡም መልሶ ‘እውነት እላችኋለሁ፤ ከሁሉ ከሚያንሱ ከእነዚህ ወንድሞቼ ለአንዱ እንኳ ስላደረጋችሁት ለእኔ አደረጋችሁት፤’ ይላቸዋል።


ልጆችን በማሳደግ፥ እንግዶችንም በመቀበል፥ የቅዱሳንንም እግሮች በማጠብ፥ የተጨነቁትንም በመርዳት፥ በጎንም ሥራ ሁሉ በመከተል፥ ይህን መልካም ሥራ በማድረግ የተመሰከረላት ልትሆን ይገባል።


እንግዲህ ኤጲስ ቆጶስ እንዲህ ሊሆን ይገባዋል፤ የማይነቀፍ፥ የአንዲት ሚስት ባል፥ ልከኛ፥ ራሱን የሚገዛ፥ እንደሚገባው የሚሠራ፥ እንግዳ ተቀባይ፥ ለማስተማር የሚበቃ፥


እኔ​ንና አብ​ያተ ክር​ስ​ቲ​ያ​ና​ትን ሁሉ በእ​ን​ግ​ድ​ነት የተ​ቀ​በለ ጋይ​ዮ​ስም ሰላም ብሎ​አ​ች​ኋል፤ የከ​ተ​ማው መጋቢ አር​ስ​ጦ​ስና ወን​ድ​ማ​ችን ቁአ​ስ​ጥ​ሮ​ስም ሰላም ብለ​ዋ​ች​ኋል።


ለተ​ራ​በ​ውም እን​ጀ​ራ​ህን አጥ​ግ​በው፤ ድሆ​ችን ወደ ቤትህ አስ​ገ​ብ​ተህ አሳ​ድ​ራ​ቸው፤ የተ​ራ​ቈ​ተ​ው​ንም ብታይ አል​ብ​ሰው፤ ከሥጋ ዘመ​ድህ አት​ሸ​ሽግ።


እር​ስ​ዋም ከቤተ ሰቦ​ችዋ ጋር ተጠ​መ​ቀች፤ “ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አማኝ ካደ​ረ​ጋ​ች​ሁ​ኝስ ወደ ቤቴ ገብ​ታ​ችሁ እደሩ” ብላ ማለ​ደ​ችን፤ የግ​ድም አለ​ችን።


ራቁ​ቱን የሆ​ነው ሰው በብ​ርድ ሲሞት አይቼ፥ አላ​ለ​በ​ስ​ሁት እንደ ሆነ፥


ከዚ​ህም በኋላ አንድ ቀን እን​ዲህ ሆነ፤ ኤል​ሳዕ ወደ ሱማን አለፈ፤ በዚ​ያም ታላቅ ሴት ነበ​ረች፤ እን​ጀ​ራም ይበላ ዘንድ አቆ​መ​ችው፤ በዚ​ያም ባለፈ ቍጥር እን​ጀራ ሊበላ ወደ​ዚያ ይገባ ነበር።


ሁለ​ቱም መላ​እ​ክት በመሸ ጊዜ ወደ ሰዶም ደረሱ፤ ሎጥም በሰ​ዶም ከተማ በር ተቀ​ምጦ ነበር። ሎጥም ባያ​ቸው ጊዜ ሊቀ​በ​ላ​ቸው ተነሣ፤ ፊቱ​ንም ወደ ምድር ደፍቶ ሰገ​ደ​ላ​ቸው፤


ወዳጅ ሆይ! ምንም እንግዶች ቢሆኑ፥ ለወንድሞች በምታደርገው ሁሉ የታመነ ሥራ ትሠራለህ፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios