እግዚአብሔር አምላክም መልካሙን መዓዛ አሸተተ፤ እግዚአብሔርም በልቡ አለ፥ “ምድርን ዳግመኛ ስለ ሰዎች ሥራ አልረግምም፤ በሰው ልብ ከታናሽነቱ ጀምሮ ክፋት ሁል ጊዜ ይኖራል፤ ደግሞም ከዚህ ቀደም እንዳደረግሁት ሕያዋንን ሁሉ እንደገና አልመታም።
አሞጽ 5:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዓመት በዓላችሁን ጠልችዋለሁ፤ አርቄውማለሁ፤ መዓዛ መሥዋዕታችሁን አላሸትም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ዓመት በዓላችሁን ተጸይፌአለሁ፤ ጠልቼውማለሁ፤ ጉባኤዎቻችሁ ደስ አያሰኙኝም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ዓመት በዓላችሁን ጠልቼዋለሁ፤ ተጸይፌዋለሁም፤ የተቀደሰውም ጉባኤአችሁ ደስ አያሰኘኝም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የዓመት በዓሎቻችሁን ሁሉ እጠላለሁ፤ እንቃለሁም፤ የአምልኮ ስብሰባዎቻችሁም አያስደስቱኝም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዓመት በዓላችሁን ጠልቼዋለሁ ተጸይፌውማለሁ፥ የተቀደሰውም ጉባኤአችሁ ደስ አያሰኘኝም። |
እግዚአብሔር አምላክም መልካሙን መዓዛ አሸተተ፤ እግዚአብሔርም በልቡ አለ፥ “ምድርን ዳግመኛ ስለ ሰዎች ሥራ አልረግምም፤ በሰው ልብ ከታናሽነቱ ጀምሮ ክፋት ሁል ጊዜ ይኖራል፤ ደግሞም ከዚህ ቀደም እንዳደረግሁት ሕያዋንን ሁሉ እንደገና አልመታም።
በሬን የሚሠዋልኝ ኃጥእ ውሻን እንደሚያርድልኝ ነው፤ የእህልን ቍርባን የሚያቀርብም የእሪያን ደም እንደሚያቀርብ ነው፤ ዕጣንንም ለመታሰቢያ የሚያጥን አምላክን እንደሚፀርፍ ነው፤ እነዚህ የገዛ መንገዳቸውን መረጡ፤ ነፍሳቸውም በርኵሰታቸው ደስ ይላታል።
ቢጾሙ ጸሎታቸውን አልሰማም፤ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የእህሉን ቍርባን ቢያቀርቡም ደስ አልሰኝባቸውም፤ በሰይፍና በራብ በቸነፈርም አጠፋቸዋለሁ።”
ስለ ምንስ ከሳባ ዕጣንን፥ ከሩቅም ሀገር ቀረፋን ታቀርቡልኛላችሁ? የሚቃጠለውን መሥዋዕታችሁን አልቀበለውም፤ ቍርባናችሁም ደስ አያሰኘኝም።
እግዚአብሔርንም ለመሻት ከበጎቻቸውና ከላሞቻቸው ጋር ይሄዳሉ፤ ነገር ግን እርሱ ከእነርሱ ተለይቶአልና አያገኙትም።
መሥዋዕትንም ቢሠዉ፥ ሥጋንም ቢበሉ፤ እግዚአብሔር አይቀበላቸውም፤ አሁንም በደላቸውን ያስባል፤ በኀጢአታቸውም ይበቀላቸዋል፤ እነርሱም ወደ ግብፅ ይመለሳሉ፤ በአሦርም ርኩስ ነገርን ይበላሉ።
ከተሞቻችሁንም ባድማ አደርጋለሁ፤ መቅደሶቻችሁንም አፈርሳለሁ፤ የመሥዋዕታችሁንም መዓዛ አላሸትትም።
“ወደ ቤቴል ገብታችሁ ኀጢአትን ሠራችሁ፤ በጌልገላም ኀጢአትን አበዛችሁ፤ በየማለዳውም መሥዋዕታችሁን፥ በየሦስተኛውም ቀን ዐሥራታችሁን አቀረባችሁ፤
ሕጉን በውጭ አነበባችሁ፤ የታመነም አላችሁት፤ በፈቃዳችሁም የምታቀርቡትን አውጁና አውሩ፥” ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
ጌታ እግዚአብሔር፥ “የያዕቆብን ትዕቢት አረክሳለሁ፤ ሀገሮቹንም ጠላሁ፤ ከተሞቹንም ከሚኖሩባቸው ሰዎች ጋር አጠፋለሁ” ብሎ በራሱ ምሎአልና።
ዓመት በዓላችሁንም ወደ ልቅሶ፥ ዝማሬያችሁንም ወደ ዋይታ እለውጣለሁ፤ ማቅንም በወገብ ሁሉ ላይ፥ ቡሃነትንም በራስ ሁሉ ላይ ላይ አመጣለሁ፤ እንደ ወዳጅ ልቅሶ አደርጋችኋለሁ፤ ከእርሱም ጋር ያሉት እንደ መከራ ቀን ይሆናሉ።
“እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን! መንግሥተ ሰማያትን በሰው ፊት ስለምትዘጉ ወዮላችሁ፤ እናንተ አትገቡም፤ የሚገቡትንም እንዳይገቡ ትከለክላላችሁ።
ክርስቶስ እንደ ወደዳችሁ፥ ራሱንም ለእግዚአብሔር በጎ መዓዛ የሚሆን መሥዋዕትና ቍርባን አድርጎ እንደ ሰጠላችሁ በፍቅር ተመላለሱ።
ነገር ግን ሁሉ አለኝ፤ ይበዛልኝማል፤ የመዓዛ ሽታና የተወደደ መሥዋዕት የሚሆነውን፥ ለእግዚአብሔርም ደስ የሚያሰኘውን ስጦታችሁን ከአፍሮዲጡ ተቀብዬ አሟልቻለሁ።