ሐዋርያት ሥራ 6:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኛ ግን ለጸሎትና ቃሉን ለማስተማር እንተጋለን።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኛ ግን በጸሎትና በቃሉ አገልግሎት እንተጋለን።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኛ ግን ለጸሎትና ቃሉን ለማገልገል እንተጋለን።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኛ ግን በመጸለይና የእግዚአብሔርን ቃል በማስተማር እንተጋለን።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኛ ግን ለጸሎትና ቃሉን ለማገልገል እንተጋለን።” |
ባለማቋረጥ በምጸልየው ጸሎት እንደማስባችሁ ልጁ በአስተማረው ወንጌል በፍጹም ልቡናዬ የማመልከው እግዚአብሔር ምስክሬ ነው።
ስለ እናንተ እና በሎዶቅያ ስላሉ፥ ፊቴንም በሥጋ ስላላዩት ምእመናን ሁሉ ምን ያህል እንደምጋደል ልታውቁ እወዳለሁ።
ከእናንተ ወገን የሚሆን ኤጳፍራስም ሰላም ይላችኋል፥ እርሱ የክርስቶስ አገልጋይ ነው፤ እግዚአብሔር በሚወደው ነገር ሁሉ ምሉኣንና ፍጹማን እንድትሆኑ፥ ስለ እናንተ ዘወትር ይጸልያል፤ ይማልዳልም።