Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሐዋርያት ሥራ 1:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 እነ​ዚህ ሁሉ ከሴ​ቶ​ችና ከጌ​ታ​ችን ከኢ​የ​ሱስ እናት ከማ​ር​ያም፥ ከወ​ን​ድ​ሞ​ቹም ጋር በአ​ን​ድ​ነት ለጸ​ሎት ይተጉ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 እነዚህ ሁሉ ከሴቶቹና ከኢየሱስ እናት ከማርያም ጋራ እንዲሁም ከወንድሞቹ ጋራ በአንድ ልብ ሆነው ያለ ማቋረጥ ተግተው ይጸልዩ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 እነዚህ ሁሉ ከሴቶችና ከኢየሱስ እናት ከማርያም ከወንድሞቹም ጋር በአንድ ልብ ሆነው ለጸሎት ይተጉ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 እነዚህ ሁሉ ዘወትር ለጸሎት በአንድነት ይሰበሰቡ ነበር፤ ከእነርሱም ጋር አንዳንድ ሴቶችና የኢየሱስ እናት ማርያም፥ እንዲሁም የኢየሱስ ወንድሞች ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 እነዚህ ሁሉ ከሴቶችና ከኢየሱስ እናት ከማርያም ከወንድሞቹም ጋር በአንድ ልብ ሆነው ለጸሎት ይተጉ ነበር።

Ver Capítulo Copiar




ሐዋርያት ሥራ 1:14
27 Referencias Cruzadas  

በጸ​ሎ​ትና በም​ልጃ ሁሉ ዘወ​ትር በመ​ን​ፈስ ጸልዩ፤ ከዚ​ህም ጋር ስለ ቅዱ​ሳን ሁሉ ለመ​ጸ​ለይ ሁል​ጊዜ ትጉ፤


እኛ ግን ለጸ​ሎ​ትና ቃሉን ለማ​ስ​ተ​ማር እን​ተ​ጋ​ለን።”


በም​ስ​ጋና እየ​ተ​ጋ​ችሁ ለጸ​ሎት ፅሙ​ዳን ሁኑ።


በሐ​ዋ​ር​ያት ትም​ህ​ር​ትና በአ​ን​ድ​ነት ማዕ​ድን በመ​ባ​ረክ፥ በጸ​ሎ​ትም ጸን​ተው ይኖሩ ነበር።


በተ​ስፋ ደስ ይበ​ላ​ችሁ፤ በመ​ከራ ታገሡ፤ ለጸ​ሎት ትጉ።


ዘወ​ትር እን​ዲ​ጸ​ልዩ፥ እን​ዳ​ይ​ሰ​ለ​ቹም በም​ሳሌ ነገ​ራ​ቸው።


አምናችሁም በጸሎት የምትለምኑትን ሁሉ ትቀበላላችሁ፤” አላቸው።


ኀም​ሳው ቀንም በተ​ፈ​ጸመ ጊዜ፥ ሁሉም በአ​ን​ድ​ነት በአ​ንድ ቦታ ተሰ​ብ​ስ​በው ነበር።


እና​ንተ ክፉ​ዎች ስት​ሆኑ ለል​ጆ​ቻ​ችሁ መል​ካም ስጦ​ታን መስ​ጠ​ትን የም​ታ​ውቁ ከሆነ፥ የሰ​ማይ አባ​ታ​ች​ሁማ ለሚ​ለ​ም​ኑት መል​ካ​ሙን ሀብተ መን​ፈስ ቅዱስ እን​ዴት አብ​ዝቶ ይሰ​ጣ​ቸው ይሆን?”


ሁል​ጊ​ዜም አንድ ልብ ሆነው በቤተ መቅ​ደስ ያገ​ለ​ግሉ ነበር፤ በቤ​ትም ኅብ​ስ​ትን ይቈ​ርሱ ነበር፤ በደ​ስ​ታና በልብ ቅን​ን​ነ​ትም ምግ​ባ​ቸ​ውን ይመ​ገቡ ነበር።


በቤተ መቅ​ደ​ስም ዘወ​ትር እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እያ​መ​ሰ​ገ​ኑና እያ​ገ​ለ​ገሉ ኖሩ። ከሰባ ሁለቱ አር​ድ​እት አንዱ ወን​ጌ​ላዊ ሉቃስ የጻ​ፈው ወን​ጌል ተፈ​ጸመ። የጻ​ፈ​ውም ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ወደ ሰማይ በዐ​ረገ በሃያ አንድ ዓመት ቀላ​ው​ዴ​ዎስ ቄሣር በነ​ገሠ በዐ​ሥራ አራት ዓመት በጽ​ርዕ ቋንቋ ለመ​ቄ​ዶ​ንያ ሰዎች ነው። ምስ​ጋና ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይሁን። አሜን።


ገናም ለሕዝቡ ሲናገር፥ እነሆ፥ እናቱና ወንድሞቹ ሊነጋገሩት ፈልገው በውጭ ቆመው ነበር።


እነ​ዚ​ያም መግ​ደ​ላ​ዊት ማር​ያም፥ ዮሐና፥ የያ​ዕ​ቆብ እናት ማር​ያም፥ አብ​ረ​ዋ​ቸው የነ​በ​ሩት ባል​ን​ጀ​ሮ​ቻ​ቸ​ውም ይህን ለሐ​ዋ​ር​ያት ነገ​ሩ​አ​ቸው።


ከገ​ሊ​ላም ከእ​ርሱ ጋር የመጡ ሁለት ሴቶች ተከ​ት​ለው፥ መቃ​ብ​ሩን፥ ሥጋ​ው​ንም እን​ዴት እን​ዳ​ኖ​ሩት አዩ። ተመ​ል​ሰ​ውም ሽቱና ዘይት አዘ​ጋጁ፤ ነገር ግን በሰ​ን​በት አል​ሄ​ዱም፤ ሕጋ​ቸው እን​ዲህ ነበ​ርና።


የሚ​ያ​ው​ቁት ሁሉና ከገ​ሊላ ጀምሮ የተ​ከ​ተ​ሉ​ትም ሴቶች በሩቁ ቆመው ይህን ያዩ ነበር።


ሰንበትም ካለፈ በኋላ መግደላዊት ማርያም የያዕቆብም እናት ማርያም ሰሎሜም መጥተው ሊቀቡት ሽቶ ገዙ።


ሴቶችም ደግሞ በሩቅ ሆነው ይመለከቱ ነበር፤ ከእነርሱም በገሊላ ሳለ ይከተሉትና ያገለግሉት የነበሩ መግደላዊት ማርያም የታናሹ ያዕቆብና የዮሳም እናት ማርያም ሰሎሜም ነበሩ፤


ኢየሱስን እያገለገሉ ከገሊላ የተከተሉት ብዙ ሴቶች በሩቅ ሆነው ሲመለከቱ በዚያ ነበሩ፤


በዚ​ያ​ችም ሰዓት ተነ​ሥ​ተው ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ተመ​ለሱ፤ ዐሥራ አን​ዱን ደቀ መዛ​ሙ​ር​ትና አብ​ረ​ዋ​ቸው የነ​በ​ሩ​ት​ንም ተሰ​ብ​ስ​በው አገ​ኙ​አ​ቸው፤


“እና​ት​ህና ወን​ድ​ሞ​ችህ ከውጭ ቆመ​ዋል፤ ሊያ​ዩ​ህም ይሻሉ” አሉት።


በማ​ያ​ው​ቀው ቋንቋ የሚ​ና​ገር ሰውም መተ​ር​ጐም እን​ዲ​ችል ይጸ​ልይ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios