La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ሐዋርያት ሥራ 3:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እና​ንተ ግን ቅዱ​ሱ​ንና ጻድ​ቁን ካዳ​ች​ሁት፤ ነፍሰ ገዳ​ዩን ሰውም እን​ዲ​ያ​ድ​ን​ላ​ችሁ ለመ​ና​ችሁ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ቅዱሱንና ጻድቁን ክዳችሁ ነፍሰ ገዳዩ እንዲፈታላችሁ ለመናችሁ፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እናንተ ግን ቅዱሱን ጻድቁንም ክዳችሁ ነፍሰ ገዳዩን ሰው ይሰጣችሁ ዘንድ ለመናችሁ፤

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እናንተ ቅዱሱንና ጻድቁን ‘አንፈልገውም’ ብላችሁ አንድ ነፍሰ ገዳይ እንዲፈታላችሁ ለመናችሁ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እናንተ ግን ቅዱሱን ጻድቁንም ክዳችሁ ነፍሰ ገዳዩን ሰው ይሰጣችሁ ዘንድ ለመናችሁ፥

Ver Capítulo



ሐዋርያት ሥራ 3:14
22 Referencias Cruzadas  

አን​ጀ​ታ​ቸ​ውን ቋጠሩ፥ አፋ​ቸ​ውም ትዕ​ቢ​ትን ተና​ገረ።


አንቺ የጽዮን ልጅ ሆይ፥ እጅግ ደስ ይበልሽ፣ አንቺ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ፥ እልል በዪ፣ እነሆ፥ ንጉሥሽ ጻድቅና አዳኝ ነው፣ ትሑትም ሆኖ በአህያም፥ በአህያይቱ ግልገል በውርጫንይቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል።


የካህናት አለቆችና ሽማግሎች ግን በርባንን እንዲለምኑ ኢየሱስን ግን እንዲያጠፉ ሕዝቡን አባበሉ።


እርሱም “የናዝሬቱ ኢየሱስ ሆይ! ከአንተ ጋር ምን አለን? ልታጠፋን መጣህን? ማን እንደ ሆንህ አውቄአለሁ! የእግዚአብሔር ቅዱሱ!” ብሎ ጮኸ።


የካህናት አለቆች ግን በርባንን በእርሱ ፈንታ ይፈታላቸው ዘንድ ሕዝቡን አወኩአቸው።


በዐመፅም ነፍስ ከገደሉት ከዐመፀኞች ጋር የታሰረ በርባን የተባለ ነበረ።


መል​አ​ኩም መልሶ እን​ዲህ አላት፥ “መን​ፈስ ቅዱስ ያድ​ር​ብ​ሻል፤ የል​ዑል ኀይ​ልም ይጋ​ር​ድ​ሻል፤ ከአ​ንቺ የሚ​ወ​ለ​ደ​ውም ቅዱስ ነው፤ የል​ዑል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጅም ይባ​ላል።


ያን የለ​መ​ኑ​ትን፥ ነፍስ በመ​ግ​ደ​ልና ሁከት በማ​ድ​ረግ የታ​ሰ​ረ​ው​ንም ሰው ፈታ​ላ​ቸው፤ ኢየ​ሱ​ስን ግን ለፈ​ቃ​ዳ​ቸው አሳ​ልፎ ሰጣ​ቸው።


ስለ ጽድቅ፥ እኔ ወደ አብ እሄ​ዳ​ለ​ሁና፥ እን​ግ​ዲህ ወዲ​ህም አታ​ዩ​ኝ​ምና ነው።


ዳግ​መ​ኛም ድም​ፃ​ቸ​ውን ከፍ አድ​ር​ገው፥ “በር​ባ​ንን እንጂ ይህን አይ​ደ​ለም፤” አሉ፤ በር​ባን ግን ወን​በዴ ነበር።


ለሞ​ትም የሚ​ያ​በቃ ምንም በደል ባላ​ገ​ኙ​በት ጊዜ እን​ዲ​ገ​ድ​ለው ጲላ​ጦ​ስን ለመ​ኑት።


ነፍ​ሴን በሲ​ኦል አት​ተ​ዋ​ት​ምና፥ ጻድ​ቅ​ህ​ንም ጥፋ​ትን ያይ ዘንድ አት​ሰ​ጠ​ው​ምና።


እን​ዲ​ህም አለኝ፤ ‘የአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን አም​ላክ ፈቃ​ዱን ታው​ቅና ጽድ​ቁ​ንም ታይ ዘንድ፥ ቃሉ​ንም ከአ​ን​ደ​በቱ ትሰማ ዘንድ መረ​ጠህ።


በቀ​ባ​ኸው በቅ​ዱስ ልጅህ ላይ ሄሮ​ድ​ስና ጰን​ጤ​ና​ዊው ጲላ​ጦስ ከወ​ገ​ኖ​ቻ​ቸ​ውና ከእ​ስ​ራ​ኤል ሕዝብ ጋር በእ​ው​ነት በዚች ሀገር ላይ ዶለቱ።


“በኢ​የ​ሱስ ስም ለማ​ንም እን​ዳ​ታ​ስ​ተ​ምሩ ከል​ክ​ለ​ና​ችሁ አል​ነ​በ​ረ​ምን? እነሆ፥ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን በት​ም​ህ​ር​ታ​ችሁ ሞላ​ች​ኋት፤ የዚ​ያ​ንም ሰው ደም በእኛ ላይ ታመ​ጡ​ብን ዘንድ ትሻ​ላ​ች​ሁን?” አላ​ቸው።


አባ​ቶ​ቻ​ችሁ ከነ​ቢ​ያት ያላ​ሳ​ደ​ዱት ማን አለ? ዛሬም እና​ንተ አሳ​ል​ፋ​ችሁ የሰ​ጣ​ች​ሁ​ት​ንና የገ​ደ​ላ​ች​ሁ​ትን የጻ​ድ​ቁን መም​ጣት አስ​ቀ​ድ​መው የተ​ና​ገ​ሩ​ትን ገደ​ሉ​አ​ቸው።


ኀጢ​አት የሌ​ለ​በት እርሱ እኛን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያጸ​ድ​ቀን ዘንድ ስለ እኛ ራሱን እንደ ኃጥእ አድ​ር​ጓ​ልና።


ጻድቁን ኰንናችሁታል፤ ገድላችሁትማል፤ እናንተን አይቃወምም።


ክርስቶስ ደግሞ ወደ እግዚአብሔር እንዲያቀርበን እርሱ ጻድቅ ሆኖ ስለ ዐመፀኞች አንድ ጊዜ በኀጢአት ምክንያት ሞቶአልና፤ በሥጋ ሞተ፤ በመንፈስ ግን ሕያው ሆነ፤


ልጆቼ ሆይ፥ ኃጢአትን እንዳታደርጉ ይህን እጽፍላችኋለሁ። ማንም ኃጢአትን ቢያደርግ ከአብ ዘንድ ጠበቃ አለን እርሱም ጻድቅ የሆነ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።


“በፊላደልፊያም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፡ የዳዊት መክፈቻ ያለው፥ የሚከፍት፥ የሚዘጋም የሌለ፤ የሚዘጋ፥ የሚከፍትም የሌለ፤ ቅዱስና እውነተኛ የሆነው እርሱ እንዲህ ይላል፦