La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ሐዋርያት ሥራ 20:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እኛ ግን ከፋ​ሲካ በኋላ ከፊ​ል​ጵ​ስ​ዩስ ተነ​ሥ​ተን በባ​ሕር ላይ ተጕ​ዘን በአ​ም​ስት ቀን ወደ ጢሮ​አስ ደረ​ስን፤ በዚ​ያም ሰባት ቀን ተቀ​መ​ጥን።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እኛ ግን የቂጣ በዓል ካለፈ በኋላ፣ ከፊልጵስዩስ በመርከብ ተነሣን፤ ከዐምስት ቀንም በኋላ ከሌሎቹ ጋራ በጢሮአዳ ተገናኘን፤ በዚያም ሰባት ቀን ተቀመጥን።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እኛ ግን ከቂጣ በዓል ቀን በኋላ ከፊልጵስዩስ በመርከብ ተነሥተን በአምስት ቀን ወደ ጢሮአዳ ወደ እነርሱ ደረስንና በዚያ ሰባት ቀን ተቀመጥን።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እኛ ግን ከቂጣ በዓል በኋላ ከፊልጵስዩስ በመርከብ ተሳፍረን በአምስት ቀን እነርሱ ወዳሉበት ወደ ጢሮአዳ ደረስንና እዚያ ሰባት ቀን አሳለፍን።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እኛ ግን ከቂጣ በዓል ቀን በኋላ ከፊልጵስዩስ በመርከብ ተነሥተን በአምስት ቀን ወደ ጢሮአዳ ወደ እነርሱ ደረስንና በዚያ ሰባት ቀን ተቀመጥን።

Ver Capítulo



ሐዋርያት ሥራ 20:6
18 Referencias Cruzadas  

የቂ​ጣ​ውን በዓል ጠብቁ፤ በአ​ዲስ ወር ከግ​ብፅ ምድር ወጥ​ታ​ች​ኋ​ልና በዚህ ወር እን​ዳ​ዘ​ዝ​ኋ​ችሁ ሰባት ቀን ቂጣ ትበ​ላ​ላ​ችሁ።


“የቂ​ጣ​ውን በዓል ትጠ​ብ​ቀ​ዋ​ለህ። በሚ​ያ​ዝያ ወር ከግ​ብፅ ወጥ​ተ​ሃ​ልና በታ​ዘ​ዘው ዘመን በሚ​ያ​ዝያ ወር እን​ዳ​ዘ​ዝ​ሁህ ሰባት ቀን ቂጣ ብላ።


አይ​ሁ​ድ​ንም ደስ እን​ዳ​ላ​ቸው አይቶ ጴጥ​ሮ​ስን ደግሞ ያዘው፤ ያን​ጊ​ዜም የፋ​ሲካ በዓል ነበር።


ራእ​ዩ​ንም ባየ ጊዜ ወዲ​ያ​ውኑ ወደ መቄ​ዶ​ንያ ልን​ሄድ ወደ​ድን፤ ወን​ጌ​ልን እን​ሰ​ብ​ክ​ላ​ቸው ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ጠ​ራን መስ​ሎ​ና​ልና።


ከዚ​ያም ወደ ፊል​ጵ​ስ​ዩስ ሄድን፤ ይህ​ች​ውም የመ​ቄ​ዶ​ንያ ዋና ከተ​ማና የሮም ቅኝ ግዛት ነበ​ረች፤ በዚ​ያ​ችም ሀገር ጥቂት ቀን ሰነ​በ​ትን።


ከሚ​ስ​ያም ዐል​ፈው ወደ ጢሮ​አዳ ወረዱ።


ጳው​ሎ​ስም በእ​ስያ እን​ዳ​ይ​ዘ​ገይ በኤ​ፌ​ሶን በኩል ሊሄድ ቈርጦ ነበር፤ የሚ​ቻ​ለ​ውም ቢሆን ለበ​ዓለ ኀምሳ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ለመ​ድ​ረስ ቸኵሎ ነበ​ርና።


እነ​ር​ሱም ቀድ​መ​ውን ሄደው በጢ​ሮ​አስ ቆዩን።


በዚ​ያም ደቀ መዛ​ሙ​ር​ትን አገ​ኘ​ንና በእ​ነ​ርሱ ዘንድ ሰባት ቀን ተቀ​መ​ጥን፤ እነ​ር​ሱም በመ​ን​ፈስ ቅዱስ ተገ​ል​ጾ​ላ​ቸው ጳው​ሎ​ስን ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም እን​ዳ​ይ​ወጣ ነገ​ሩት።


በማ​ግ​ሥ​ቱም ወጥ​ተን ወደ ቂሳ​ርያ ሄድን፤ ወደ ወን​ጌ​ላ​ዊው ወደ ፊል​ጶስ ቤትም ገባን፤ እር​ሱም ከሰ​ባቱ ወን​ድ​ሞች ዲያ​ቆ​ናት አንዱ ነው።


በዚ​ያም ወን​ድ​ሞ​ችን አግ​ኝ​ተን ተቀ​በ​ሉን፤ በእ​ነ​ርሱ ዘን​ድም ሰባት ቀን እን​ድ​ን​ቀ​መጥ ለመ​ኑን፤ ከዚ​ያም በኋላ ሄደን ወደ ሮሜ ደረ​ስን።


ከኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ባር​ያ​ዎች ከጳ​ው​ሎ​ስና ከጢ​ሞ​ቴ​ዎስ፥ በፊ​ል​ጵ​ስ​ዩስ ለሚ​ኖሩ፤ ከቀ​ሳ​ው​ስ​ትና ከዲ​ያ​ቆ​ናት ጋር በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ላሉ ቅዱ​ሳን ሁሉ፤


ነገር ግን እንደምታውቁት በፊልጵስዩስ አስቀድመን መከራ ተቀብለን ተንገላትተንም፥ በብዙ ገድል የእግዚአብሔርን ወንጌል ለእናንተ እንናገር ዘንድ በአምላካችን ደፈርን።


ስትመጣ በጢሮአዳ ከአክርጳ ዘንድ የተውሁትን በርኖሱንና መጻሕፍቱን ይልቁንም በብራና የተጻፉትን አምጣልኝ።