Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሐዋርያት ሥራ 21:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 በዚ​ያም ደቀ መዛ​ሙ​ር​ትን አገ​ኘ​ንና በእ​ነ​ርሱ ዘንድ ሰባት ቀን ተቀ​መ​ጥን፤ እነ​ር​ሱም በመ​ን​ፈስ ቅዱስ ተገ​ል​ጾ​ላ​ቸው ጳው​ሎ​ስን ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም እን​ዳ​ይ​ወጣ ነገ​ሩት።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ደቀ መዛሙርትንም በዚያ አግኝተን፣ ሰባት ቀን ከእነርሱ ጋራ ተቀመጥን። እነርሱም በመንፈስ ሆነው ጳውሎስ ወደ ኢየሩሳሌም እንዳይሄድ ነገሩት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ደቀ መዛሙርትንም ባገኘን ጊዜ በዚያ ሰባት ቀን ተቀመጥን፤ እነርሱም ጳውሎስን ወደ ኢየሩሳሌም እንዳይወጣ በመንፈስ ተመርተው ነገሩት።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 እዚያ ምእመናንን ፈልገን አገኘንና ከእነርሱ ጋር ሰባት ቀን ቈየን። እነርሱም በመንፈስ ቅዱስ ተመርተው ጳውሎስን “ወደ ኢየሩሳሌም አትሂድ” ብለው ነገሩት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 ደቀ መዛሙርትንም ባገኘን ጊዜ በዚያ ሰባት ቀን ተቀመጥን፤ እነርሱም ጳውሎስን ወደ ኢየሩሳሌም እንዳይወጣ በመንፈስ አሉት።

Ver Capítulo Copiar




ሐዋርያት ሥራ 21:4
11 Referencias Cruzadas  

በዚ​ያም ወን​ድ​ሞ​ችን አግ​ኝ​ተን ተቀ​በ​ሉን፤ በእ​ነ​ርሱ ዘን​ድም ሰባት ቀን እን​ድ​ን​ቀ​መጥ ለመ​ኑን፤ ከዚ​ያም በኋላ ሄደን ወደ ሮሜ ደረ​ስን።


ከዚ​ህም በኋላ አጵ​ሎስ በቆ​ሮ​ን​ቶስ ሳለ፥ ጳው​ሎስ ላይ ላዩን ሄዶ ወደ ኤፌ​ሶን መጣ፤ በዚ​ያም ጥቂት ደቀ መዛ​ሙ​ር​ትን አገኘ።


በቤተ ክር​ስ​ቲ​ያ​ንም አንድ ዓመት አብ​ረው ተቀ​መጡ፤ ብዙ ሕዝ​ብ​ንም አስ​ተ​ማሩ፤ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ትም መጀ​መ​ሪያ በአ​ን​ጾ​ኪያ ክር​ስ​ቲ​ያን ተብ​ለው ተጠሩ።


በምትገቡባትም በማናቸይቱም ከተማ ወይም መንደር፥ በዚያ የሚገባው ማን እንደ ሆነ በጥንቃቄ መርምሩ፤ እስክትወጡም ድረስ በዚያ ተቀመጡ።


በጌታ ቀን በመንፈስ ነበርሁ፤ በኋላዬም የመለከትን ድምፅ የሚመስል ታላቅ ድምፅ ሰማሁ፤


በሰንሰለቴም አላፈረበትም፤ ነገር ግን በሮሜ ባደረ ጊዜ ፈልጎ ፈልጎ አገኘኝ፤


እኔም ስለ ስሜ መከ​ራን ይቀ​በል ዘንድ እን​ዳ​ለው አሳ​የ​ዋ​ለሁ።”


ከደቀ መዛ​ሙ​ር​ትም ከቂ​ሳ​ርያ አብ​ረ​ውን የመጡ ነበሩ፤ ሄደ​ንም ከመ​ጀ​መ​ሪ​ያ​ዎቹ ደቀ መዛ​ሙ​ርት ወገን ከሆ​ነው በቆ​ጵ​ሮስ በሚ​ኖ​ረው በም​ና​ሶን ቤት አደ​ርን።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios