እግዚአብሔርም አብራምን አለው፥ “ዘርህ ለእነርሱ ባልሆነች ምድር ስደተኞች እንዲሆኑ በእርግጥ ዕወቅ፤ አራት መቶ ዓመታትም ባሪያዎች አድርገው ይገዙአቸዋል፤ ያሠቃዩአቸዋል፤ ያስጨንቋቸዋልም።
ሐዋርያት ሥራ 12:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያንጊዜም የጴጥሮስ ልቡና ተመለሰለትና፥ “እግዚአብሔር መልአኩን ልኮ ከሄሮድስ እጅና የአይሁድ ሕዝብ ይጠብቁት ከነበረው ሁሉ እንደ አዳነኝ በእውነት አሁን ዐወቅሁ” አለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጴጥሮስም ሲረጋጋ፣ “ጌታ መልአኩን ልኮ ከሄሮድስ እጅና አይሁድ ካሰቡብኝ ሁሉ እንዳወጣኝ አሁን ያለ ጥርጥር ዐወቅሁ” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጴጥሮስም ወደ ልቡ ተመልሶ “ጌታ መልአኩን ልኮ ከሄሮድስ እጅና የአይሁድ ሕዝብ ይጠብቁት ከነበረው ሁሉ እንደ አዳነኝ አሁን በእውነት አወቅሁ፤” አለ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጴጥሮስም ወደ ልቡናው ተመልሶ፥ “ጌታ መልአኩን ልኮ ከሄሮድስ እጅና የአይሁድ ሕዝብ ይጠባበቁት ከነበረው ነገር ሁሉ ያዳነኝ መሆኑን አሁን ገና በእውነት ዐወቅሁ!” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጴጥሮስም ወደ ልቡ ተመልሶ፦ “ጌታ መልአኩን ልኮ ከሄሮድስ እጅና የአይሁድ ሕዝብ ይጠብቁት ከነበረው ሁሉ እንደ አዳነኝ አሁን በእውነት አወቅሁ” አለ። |
እግዚአብሔርም አብራምን አለው፥ “ዘርህ ለእነርሱ ባልሆነች ምድር ስደተኞች እንዲሆኑ በእርግጥ ዕወቅ፤ አራት መቶ ዓመታትም ባሪያዎች አድርገው ይገዙአቸዋል፤ ያሠቃዩአቸዋል፤ ያስጨንቋቸዋልም።
እግዚአብሔርም አብርሃምን አለው፥ “ሣራን ለብቻዋ በልብዋ ምን አሳቃት? እስከ ዛሬ ገና ነኝን? በእውነትስ እወልዳለሁን? ጌታዬም አርጅትዋል እነሆ፥ እኔም አርጅቻለሁ ብላለችና።
አቤሜሌክም ይስሐቅን ጠራ፤ እንዲህም አለው፥ “እነሆ፥ ሚስትህ ናት፤ እንዴትስ እርስዋን፦ ‘እኅቴ ናት’ አልህ?” ይስሐቅም፥ “በእርስዋ ምክንያት እንዳልሞት ብዬ ነው” አለው።
እግዚአብሔር ልቡ በእርሱ ዘንድ ፍጹም የሆነውን ያጸና ዘንድ ዐይኖቹ በምድር ሁሉ ይመለከታሉና። አሁንም ባለማወቅህ በድለሃል፤ ስለዚህም ከዛሬ ጀምሮ ጦርነት ይሆንብሃል።”
የእግዚአብሔርም መልአክ ወርዶ በአጠገቡ ቆመ፤ በቤትም ውስጥ ብርሃን ሆነ፤ ጴጥሮስንም ጎኑን ነክቶ ቀሰቀሰውና፥ “ፈጥነህ ተነሥ” አለው፥ ሰንሰለቶቹም ከእጆቹ ወልቀው ወደቁ።
ሁለት ዓመትም ካለፈ በኋላ፥ ፊልክስ ተሻረና ጶርቅዮስ ፊስጦስ የሚባል ሌላ ሀገረ ገዢ በእርሱ ቦታ መጣ፤ ፊልክስም በግልጥ ለአይሁድ ሊያዳላ ወደደ፤ ስለዚህም ጳውሎስን እንደ ታሰረ ተወው።
ፊስጦስ ግን አይሁድ እንዲያመሰግኑት ወዶ ጳውሎስን፥ “ወደ ኢየሩሳሌም ወጥተህ ስለዚህ ነገር በዚያ ከእኔ ዘንድ ልትከራከር ትሻለህን?” አለው።
መላእክት ሁሉ መናፍስት አይደሉምን? የዘለዓለም ሕይወትን ይወርሱ ዘንድ ስለ አላቸው ሰዎችስ ለአገልግሎት ይላኩ የለምን?
ጌታ እግዚአብሔርን የሚያመልኩትን ከፈተና እንዴት እንዲያድን በደለኞችንም ይልቁንም በርኵስ ምኞት የሥጋን ፍትወት እየተከተሉ የሚመላለሱትን ጌትነትንም የሚንቁትን እየቀጣቸው ለፍርድ ቀን እንዴት እንዲጠብቅ ያውቃል። ደፋሮችና ኵሩዎች ሆነው ሥልጣን ያላቸውን ሲሳደቡ አይንቀጠቀጡም፤