Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሐዋርያት ሥራ 12:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 መጀ​መ​ሪ​ያ​ው​ንና ሁለ​ተ​ኛ​ውን ዘብ አል​ፈው ወደ ከተማ ወደ​ም​ት​ወ​ስ​ደው ወደ ብረቱ መዝ​ጊያ ደረሱ፤ ያን​ጊ​ዜም መዝ​ጊ​ያው ራሱ ተከ​ፈ​ተ​ላ​ቸው፤ ወጥ​ተ​ውም በአ​ንድ ስላች መን​ገድ ሄዱ፤ መል​አ​ኩም ጴጥ​ሮ​ስን ትቶት ሄደ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 የመጀመሪያውንና ሁለተኛውን ዘብ ዐልፈው ወደ ከተማዪቱ በሚወስደው መንገድ ላይ ወዳለው የብረት መዝጊያ ዘንድ ደረሱ። መዝጊያውም ራሱ ዐውቆ ተከፈተላቸው፤ እነርሱም ወጥተው ሄዱ፤ አንዲት ስላች መንገድ እንዳለፉም ወዲያው መልአኩ ተለየው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 የመጀመሪያውንና የሁለተኛውንም ዘብ አልፈው ወደ ከተማ ወደሚያወጣው ወደ ብረቱ መዝጊያ ደረሱ፤ እርሱም ራሱ ዐውቆ ተከፈተላቸው፤ ወጥተውም አንዲት ስላች አለፉ፤ ወዲያውም መልአኩ ከእርሱ ተለየ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 አንደኛውንና ሁለተኛውን ዘብ አልፈው ወደ ከተማ ወደሚወስደው ወደ ብረቱ መዝጊያ ደረሱ። መዝጊያውም ሰው ሳይነካው እንዲሁ ተከፈተላቸውና ወጥተው በአንድ ስላች መንገድ አልፈው ሄዱ፤ በድንገትም መልአኩ ከጴጥሮስ ተለይቶ ሄደ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 የመጀመሪያውንና የሁለተኛውንም ዘብ አልፈው ወደ ከተማ ወደሚያወጣው ወደ ብረቱ መዝጊያ ደረሱ፤ እርሱም አውቆ ተከፈተላቸው፤ ወጥተውም አንዲት ስላች አለፉ ወዲያውም መልአኩ ከእርሱ ተለየ።

Ver Capítulo Copiar




ሐዋርያት ሥራ 12:10
11 Referencias Cruzadas  

የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አክ ግን በሌ​ሊት የወ​ኅኒ ቤቱን ደጃፍ ከፍቶ አወ​ጣ​ቸው፤ እን​ዲ​ህም አላ​ቸው።


ድን​ገ​ትም ታላቅ ንው​ጽ​ው​ጽታ ሆነ፤ የወ​ህኒ ቤቱ መሠ​ረ​ትም ተና​ወጠ፤ በሮ​ችም ሁሉ ያን​ጊዜ ተከ​ፈቱ፤ የሁ​ሉም እግር ብረ​ቶ​ቻ​ቸው እየ​ወ​ለቁ ወደቁ።


ያም ከሳ​ም​ንቱ የመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ቀን በመሸ ጊዜ ደቀ መዛ​ሙ​ርቱ አይ​ሁ​ድን ስለ ፈሩ ተሰ​ብ​ስ​በው የነ​በ​ሩ​በት ቤት ደጁ ተቈ​ልፎ ሳለ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ መጥቶ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ቆመና፥ “ሰላም ለእ​ና​ንተ ይሁን” አላ​ቸው።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጕበኛ ኦር​ያስ ተጠራ፤ እር​ሱም፥ “እነሆ እኔ አለሁ፤ መላ መዓ​ል​ቱ​ንና መላ ሌሊ​ቱን በማማ ላይ ቆሜ አለሁ።


እን​ዴት እን​ደ​ሚ​ያ​ደ​ር​ጉት አል​ፈ​ረ​ዱ​ምና በግ​ዞት ቤት አዋ​ሉት።


ሦስት ቀን ያህ​ልም በግ​ዞት ቤት ጨመ​ራ​ቸው።


በእ​ስር ቤት ውስ​ጥም ዮሴፍ ታስሮ በነ​በ​ረ​በት የግ​ዞት ስፍራ አጋ​ዛ​ቸው።


“በፊላደልፊያም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፡ የዳዊት መክፈቻ ያለው፥ የሚከፍት፥ የሚዘጋም የሌለ፤ የሚዘጋ፥ የሚከፍትም የሌለ፤ ቅዱስና እውነተኛ የሆነው እርሱ እንዲህ ይላል፦


ይዞም ወኅኒ ቤት አስ​ገ​ባው፤ ለሚ​ጠ​ብ​ቁት ለዐ​ሥራ ስድ​ስቱ ወታ​ደ​ሮ​ችም አሳ​ልፎ ሰጠው፤ ከፋ​ሲ​ካም በኋላ ወደ ሕዝብ ሊያ​ቀ​ር​በው ወድዶ ነበር።


ከስ​ም​ንት ቀን በኋ​ላም ዳግ​መኛ ደቀ መዛ​ሙ​ርቱ በው​ስጡ ሳሉ፥ ቶማ​ስም አብ​ሮ​አ​ቸው ሳለ በሩ እንደ ተዘጋ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ መጣ፤ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸ​ውም ቆመና፥ “ሰላም ለእ​ና​ንተ ይሁን” አላ​ቸው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios