ያዘዝኋቸውንም ሁሉ ፥ ባሪያዬም ሙሴ ያዘዛቸውን ሕግ ሁሉ ቢያደርጉ ቢጠብቁም ለአባቶቻቸው ከሰጠኋት ምድር የእስራኤልን እግር እንደገና አላንቀሳቅስም” ባለው ቤት የሠራውን የማምለኪያ ዐፀድ የተቀረጸውንም ምስል አቆመ።
2 ሳሙኤል 7:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለሕዝቤም ለእስራኤል ስፍራ አደርጋለሁ፤ እተክላቸውማለሁ፤ ብቻቸውን ይቀመጣሉ፤ ከዚያም በኋላ የሚጠራጠሩት የለም፤ እንደ ቀድሞው ዘመን የኀጢአት ልጅ መከራ አያጸናባቸውም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የራሳቸውም መኖሪያ ስፍራ እንዲኖራቸው፣ ከእንግዲህ በኋላም እንዳይናወጡ ለሕዝቤ ለእስራኤል መኖሪያ ስፍራ እሰጣቸዋለሁ። ከዚህ ቀደም እንዳደረጉት ክፉዎች ከእንግዲህ አይጨቍኗቸውም፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የራሱ የሆነ መኖሪያ እንዲኖረውና ከእንግዲህ ወዲያ እንዳይናወጥ፥ ለሕዝቤ ለእስራኤል ቦታ እሰጠዋለሁ፤ አጸናዋለሁም። ከእንግዲህ ወዲህ ክፉ ሕዝብ አይጨቁነውም፤ ከዚህ በፊት እንደ ሆነው፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለሕዝቤ ለእስራኤል መኖሪያ አዘጋጅቴ በራሳቸው ቦታ እንዲኖሩ አደርጋለሁ፤ ለእነርሱ መሳፍንትን ከሾምኩበት ጊዜ ጀምሮ ክፉ አድራጊዎች ቀድሞ ያደርጉት እንደ ነበረው አያስጨንቋቸውም፤ አንተንም ከጠላቶችህ ሁሉ አሳርፍሃለሁ፤ እንዲሁም እግዚአብሔር ከቤትህ አልጋህን የሚወርሱ ልጆች እተካልሃለሁ ብሎ ይገልጥልሃል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለሕዝቤም ለእስራኤል ስፍራ አደርግለታለሁ፥ |
ያዘዝኋቸውንም ሁሉ ፥ ባሪያዬም ሙሴ ያዘዛቸውን ሕግ ሁሉ ቢያደርጉ ቢጠብቁም ለአባቶቻቸው ከሰጠኋት ምድር የእስራኤልን እግር እንደገና አላንቀሳቅስም” ባለው ቤት የሠራውን የማምለኪያ ዐፀድ የተቀረጸውንም ምስል አቆመ።
ለሕዝቤም ለእስራኤል ስፍራ አደርግለታለሁ፥ በዚያም እተክለዋለሁ፥ በስፍራውም ይቀመጣል፤ ከዚያም በኋላ አይናወጥም፤ የኀጢአትም ልጆች እንደ ቀድሞው አያስጨንቁትም፤
ያዘዝኋቸውንም ሁሉ፥ በሙሴ የተሰጠውን ሕግና ሥርዐት ፍርድንም ሁሉ ቢያደርጉ ቢጠብቁም፥ ለአባቶቻችሁ ከሰጠኋት ምድር የእስራኤልን እግር እንደ ገና አላርቅም” ባለበት በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ የሠራውን ጣዖትና የተቀረጸውን ምስል አቆመ።
ፈርዖንም፥ “የሚወለደውን ወንድ ልጅ ሁሉ ወደ ወንዝ ጣሉት፤ ሴትን ልጅ ሁሉ ግን በሕይወት አድኑአት” ብሎ ሕዝቡን ሁሉ አዘዘ።
አቤቱ፥ አንተ ታስገባቸዋለህ፤ በመመስገኛህ ተራራም ትተክላቸዋለህ፤ አቤቱ፥ ለማደሪያህ ባደረግኸው ስፍራ፥ አቤቱ፥ እጆችህ ባዘጋጁት መቅደስ፤
አጥር አጠርሁ፤ በዙሪያውም ቈፈርሁ፤ ድንጋዮችንም ለቅሜ አወጣሁ፤ ምርጥ የሆነውንም ወይን ተከልሁ፤ በመካከሉም ግንብ ሠራሁ፤ ደግሞም የመጥመቂያ ጕድጓድ ማስሁለት፤ ወይንንም ያፈራ ዘንድ ጠበቅሁት፤ ዳሩ ግን እሾህን አፈራ።
የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር ወይን ቦታ እርሱ የእስራኤል ቤት ነው፤ ተወዳጁ አዲስ ተክልም የይሁዳ ሰዎች ናቸው፤ ፍርድን ያደርጋል ብየ እጠብቅ ነበር፤ እነሆም፥ ዐመፅን አደረገ፤ ጽድቅንም አይደለም፥ ጩኸትን እንጂ።
እንግዲህ በምድርሽ ውስጥ ግፍ፥ በዳርቻሽም ውስጥ ጕስቍልናና ቅጥቃጤ አይሰማም፤ ቅጥሮችሽ ድኅነት ይባላሉ፤ በሮችሽም በጥርብ ድንጋይ ይሠራሉ።
ዐይኔንም ለበጎነት በእነርሱ ላይ አደርጋለሁ፤ ወደዚህችም ምድር ለመልካም እመልሳቸዋለሁ፤ እሠራቸዋለሁ እንጂ አላፈርሳቸውም፤ እተክላቸዋለሁ እንጂ አልነቅላቸውም።
ከእንግዲህም ወዲያ ለእስራኤል ቤት የሚወጋ እሾህ፥ በዙሪያቸውም ከአሉ ከናቋቸው ሁሉ የሚያቈስል ኩርንችት አይሆንም፤ እኔም ጌታ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።
በዚያም ቀን ከምድር አራዊትና ከሰማይ ወፎች፥ ከመሬትም ተንቀሳቃሾች ጋር ቃል ኪዳን አደርግላቸዋለሁ። ቀስትንና ሰይፍን፥ ጦርንም ከምድሩ እሰብራለሁ፤ ተዘልለሽም ትቀመጫለሽ።
በምድራቸውም እተክላቸዋለሁ፤ ከእንግዲህም ወዲህ ከሰጠኋቸው ከምድራቸው አይነቀሉም” ይላል ሁሉን የሚችል እግዚአብሔር አምላክ።
እንባዎችንም ሁሉ ከዐይኖቻቸው ያብሳል፤ ሞትም ከእንግዲህ ወዲህ አይሆንም፤ ሐዘንም ቢሆን ወይም ጩኸት ወይም ሥቃይ ከእንግዲህ ወዲህ አይሆንም፤ የቀደመው ሥርዐት አልፎአልና፤” ብሎ ሲናገር ሰማሁ።
የእስራኤልም ልጆች ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፤ ዘጠኝ መቶ የብረት ሰረገሎች ነበሩትና፥ የእስራኤልንም ልጆች ሃያ ዓመት እጅግ ያስጨንቃቸው ነበር።