ንጉሡም፥ “እናንተ የሶርህያ ልጆች! በእኔና በእናንተ መካከል ምን አለኝ? እግዚአብሔር ዳዊትን ርገመው ብሎ አዝዞታልና ይርገመኝ፤ ለምንስ እንዲህ ታደርጋለህ? የሚለው ማን ነው?” አለ።
2 ሳሙኤል 3:39 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔም ዛሬ ዘመዱ እንደ ሆንሁ፥ እርሱም በንጉሡ ዘንድ የተሾመ እንደ ሆነ አታውቁምን? እነዚህም ሰዎች የሦርህያ ልጆች በርትተውብኛል፤ እግዚአብሔርም ክፋት በሠራ ላይ እንደ ክፋቱ ይመልስበት” አላቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምንም እንኳ ዛሬ የተቀባሁ ንጉሥ ብሆንም፣ እኔ ደካማ ሰው ነኝ፤ እነዚህ የጽሩያ ልጆች እጅግ በርትተውብኛል። እግዚአብሔር ለክፉ አድራጊ የእጁን ይስጠው።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምንም እንኳ ዛሬ የተቀባሁ ንጉሥ ብሆንም፥ እኔ ደካማ ሰው ነኝ፤ እነዚህ የጽሩያ ልጆች እጅግ በርትተውብኛል። ጌታ ለክፉ አድራጊ የእጁን ይስጠው።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ምንም እንኳ እኔ እግዚአብሔር መርጦ የሾመኝ ንጉሥ ብሆን ዛሬ ደካማነት ተሰምቶኛል፤ እነዚህ የጸሩያ ልጆች በእኔ ላይ እጅግ የበረቱ ዐመፀኞች ሆነውብኛል፤ እነዚህን ነፍሰ ገዳዮች እግዚአብሔር ራሱ የሚገባቸውን ቅጣት ይስጣቸው!” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔም ዛሬ ምንም ለመንገሥ የተቀባሁ ብሆን ደካማ ነኝ፥ እነዚህም ሰዎች የጽሩያም ልጆች በርትተውብኛል፥ እግዚአብሔር ክፋት በሠራ ላይ እንደ ክፋቱ ይመልስበት አላቸው። |
ንጉሡም፥ “እናንተ የሶርህያ ልጆች! በእኔና በእናንተ መካከል ምን አለኝ? እግዚአብሔር ዳዊትን ርገመው ብሎ አዝዞታልና ይርገመኝ፤ ለምንስ እንዲህ ታደርጋለህ? የሚለው ማን ነው?” አለ።
ለአሚሳይም፦ አንተ የአጥንቴ ፍላጭና የሥጋዬ ቍራጭ አይደለህምን? በዘመንህም ሁሉ በኢዮአብ ፋንታ በፊቴ የሠራዊት አለቃ ሳትሆን ብትቀር ዛሬ እግዚአብሔር ይህን ያድርግብኝ፤ ይህንም ይጨምርብኝ በሉት።”
ዳዊትም፥ “እናንተ የሶርህያ ልጆች! ዛሬ ታስቱኝ ዘንድ በእኔና በእናንተ መካከል ምን አለኝ? ዛሬስ ከእስራኤል የሚሞት አንድ ሰው የለም። ዛሬስ በእስራኤል ላይ እንደ ነገሥሁ አላውቅምን?”
አባቴ ዳዊት ሳያውቅ ከእርሱ የሚሻሉትን ሁለቱን ጻድቃን ሰዎች፥ የእስራኤልን ሠራዊት አለቃ የኔርን ልጅ አበኔርን፥ የይሁዳንም ሠራዊት አለቃ የኢያቴርን ልጅ አሜሳይን በሰይፍ ገድሎአልና እግዚአብሔር የዐመፅ ደሙን በራሱ ላይ መለሰ።
አንተ ግን ጥበበኛ ሰው ነህና ንጹሕ አታድርገው፤ የምታደርግበትንም አንተ ታውቃለህ፤ ሽበቱንም በደም ወደ መቃብር አውርደው” አለው።
ዳዊትም፥ “ልጄ ሰሎሞን ታናሽና ለጋ ብላቴና ነው፤ ለእግዚአብሔርም የሚሠራው ቤት እጅግ ማለፊያና በሀገሩ ሁሉ ስሙና ክብሩ እንዲጠራ ይሆን ዘንድ ይገባል፤ ስለዚህ አዘጋጅለታለሁ” አለ። ዳዊትም ሳይሞት አስቀድሞ ብዙ አዘጋጀ።
ንጉሡ ዳዊትም ለጉባኤው ሁሉ እንዲህ አለ፥ “እግዚአብሔር ብቻውን የመረጠው ልጄ ሰሎሞን ገና ለጋ ብላቴና ነው፤ ሕንጻው ግን ለእግዚአብሔር ለአምላክ ነው እንጂ ለሰው አይደለምና ሥራው ታላቅ ነው።
ክፉዎች ሰዎችና የሕግ ተላላፊዎች ልጆችም ወደ እርሱ ተሰበሰቡ፤ ሮብዓም ሕፃን በነበረና በልቡ ድፍረት ባልነበረው ጊዜ፥ ሊቋቋመውም ባልቻለበት ጊዜ፥ በሰሎሞን ልጅ በሮብዓም ላይ በረታበት።
እንዲህም በለው፥ “ተጠበቅ፥ ዝምም በል፤ አትፍራ፤ ከእነዚህ ከሚጤሱ ሁለት የእንጨት ጠለሸቶች፥ የተነሣ ልብህ አይደንግጥ፤ ከተቈጣሁ በኋላ ይቅር እላለሁና።
አንተ ሥራህን ታሳምር ዘንድ የእግዚአብሔር መልእክተኞች ናቸውና። ክፉ ብታደርግ ግን ፍራ፤ ሰይፍ የታጠቁም ለከንቱ አይደለም፤ ክፉ አድራጊዎችን ለመቅጣት የእግዚአብሔር አገልጋዮች ናቸውና።
እግዚአብሔርም የሰቂማን ሰዎች ክፋት ሁሉ በራሳቸው ላይ መለሰባቸው፤ የይሩበኣል ልጅ የኢዮአታምም ርግማን ደረሰባቸው።