Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ዜና መዋዕል 13:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 ክፉ​ዎች ሰዎ​ችና የሕግ ተላ​ላ​ፊ​ዎች ልጆ​ችም ወደ እርሱ ተሰ​በ​ሰቡ፤ ሮብ​ዓም ሕፃን በነ​በ​ረና በልቡ ድፍ​ረት ባል​ነ​በ​ረው ጊዜ፥ ሊቋ​ቋ​መ​ውም ባል​ቻ​ለ​በት ጊዜ፥ በሰ​ሎ​ሞን ልጅ በሮ​ብ​ዓም ላይ በረ​ታ​በት።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 የሰሎሞን ልጅ ሮብዓም ገና ሕፃን ሳለ፣ ምንም ማድረግ በማይችልበትና እነርሱንም ለመቋቋም ዐቅሙ በማይፈቅድለት ጊዜ የማይረቡ ምናምንቴዎች በዙሪያው ተሰበሰቡበት፣ በረቱበትም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ክፉዎች ሰዎችና ምናምንቴዎችም ወደ እርሱ ተሰበሰቡ፤ ሮብዓም ሕፃንና ለጋ በነበረበት ጊዜ፥ ሊቋቋማቸውም ባልቻለበት ጊዜ፥ በሰሎሞን ልጅ በሮብዓም ላይ በረቱበት።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ዘግየት ብሎም ኢዮርብዓም የማይረቡ ወሮበሎችን ሰበሰበ፤ እነርሱም በዕድሜው ማነስና በዕውቀት ያልበሰለ በመሆኑ ሊቋቋማቸው የማይችለውን የሰሎሞንን ልጅ ሮብዓምን በረቱበት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 ክፉዎች ሰዎችና ምናምንቴዎችም ወደ እርሱ ተሰበሰቡ፤ ሮብዓም ሕፃንና ለጋ በነበረበት ጊዜ፥ ሊቋቋማቸውም ባልቻለበት ጊዜ፥ በሰሎሞን ልጅ በሮብዓም ላይ በረቱበት።

Ver Capítulo Copiar




2 ዜና መዋዕል 13:7
20 Referencias Cruzadas  

እኔም ዛሬ ዘመዱ እንደ ሆንሁ፥ እር​ሱም በን​ጉሡ ዘንድ የተ​ሾመ እንደ ሆነ አታ​ው​ቁ​ምን? እነ​ዚ​ህም ሰዎች የሦ​ር​ህያ ልጆች በር​ት​ተ​ው​ብ​ኛል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ክፋት በሠራ ላይ እንደ ክፋቱ ይመ​ል​ስ​በት” አላ​ቸው።


ዳግ​መ​ኛም ወልደ አዴር እን​ዲህ ብሎ ወደ እርሱ ላከ፥ “ሕዝ​ቤና ሠራ​ዊቴ ሁሉ ሀገ​ር​ህን ሰማ​ር​ያን ባያ​ጠ​ፉት፥ የቀ​በ​ሮም ማደ​ሪያ ባያ​ደ​ር​ጉት አማ​ል​ክት እን​ዲህ ያድ​ር​ጉ​ብኝ፤ እን​ዲ​ህም ይግ​ደ​ሉኝ።”


እነ​ሆም፥ አንድ ነቢይ ወደ እስ​ራ​ኤል ንጉሥ ወደ አክ​ዓብ መጥቶ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ይህን ብዙ ሕዝብ ሁሉ ታያ​ለ​ህን? እነሆ፥ ዛሬ በእ​ጅህ አሳ​ልፌ እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እን​ግ​ዲህ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ለህ” አለው።


ንጉሡ ስላ​ል​ሰ​ማ​ቸው ሕዝቡ፥ “በዳ​ዊት ዘንድ ምን ክፍል አለን? በእ​ሴ​ይም ልጅ ዘንድ ምን ርስት አለን? እስ​ራ​ኤል ሆይ፥ ወደ እየ​ድ​ን​ኳ​ኖ​ቻ​ችሁ ተመ​ለሱ፤ ዳዊት ሆይ፥ አሁን ቤት​ህን ተመ​ል​ከት” ብለው ለን​ጉሡ መለ​ሱ​ለት። እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ ወደ እየ​ድ​ን​ኳ​ኖ​ቻ​ቸው ሄዱ።


ንጉ​ሡም ሮብ​ዓም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ጸና፤ ንጉ​ሥም ሆነ፤ ሮብ​ዓ​ምም በነ​ገሠ ጊዜ የአ​ርባ አንድ ዓመት ጐል​ማሳ ነበረ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ስሙን ያኖ​ር​ባት ዘንድ ከእ​ስ​ራ​ኤል ሀገር ሁሉ በመ​ረ​ጣት ከተማ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ዐሥራ ሰባት ዓመት ነገሠ፤ እና​ቱም የአ​ሞን ሴት ንዑማ ነበ​ረች።


የሰ​ነ​ፎ​ችና የክ​ፉ​ዎች ሰዎች ልጆች ናቸው፤ ስማ​ቸ​ውና ክብ​ራ​ቸው ከም​ድር የጠፋ ነው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አን​ዲት ነገር ለመ​ን​ሁት፥ እር​ስ​ዋ​ንም እሻ​ለሁ፤ በሕ​ይ​ወቴ ዘመን ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት እኖር ዘንድ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ደስ የሚ​ያ​ሰ​ኘ​ው​ንም አይ ዘንድ፥ በቤተ መቅ​ደ​ሱም አገ​ለ​ግል ዘንድ።


ምድሩን የሚያርሳት ሰው እንጀራን ይጠግባል፤ ቦዘኔነትን የሚከተል ግን የአእምሮ ድህነትን ይሰበስባል። በወይን ግብዣ ራሱን ደስ የሚያሰኝ ሰው በሰውነቱ ውርደትን ያመጣል።


ንጉ​ሥሽ ሕፃን የሆነ፥ መኳ​ን​ን​ቶ​ች​ሽም ማል​ደው የሚ​በሉ፥ አንቺ ሀገር ሆይ፥ ወዮ​ልሽ!


በእ​ነ​ርሱ ላይ አለ​ቆ​ቻ​ቸው እን​ዲ​ሆኑ ጐል​ማ​ሶ​ችን እሾ​ም​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ዘባ​ቾ​ችም ይገ​ዙ​አ​ቸ​ዋል።


የማ​ያ​ምኑ አይ​ሁድ ግን ቀኑ​ባ​ቸው፤ ከገ​በ​ያም ክፉ​ዎች ሰዎ​ችን አም​ጥ​ተው፥ ሰዎ​ች​ንም ሰብ​ስ​በው ሀገ​ሪ​ቱን አወ​ኳት፤ ፈለ​ጓ​ቸ​ውም፤ የኢ​ያ​ሶ​ንን ቤትም በረ​በሩ፤ ወደ ሕዝ​ቡም ሊያ​ወ​ጧ​ቸው ሽተው ነበር።


ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ በአ​እ​ምሮ እንደ ሕፃ​ናት አት​ሁኑ፤ ነገር ግን ለክፉ ነገር እንደ ሕፃ​ናት ሁኑ፤ በዕ​ው​ቀ​ትም ፍጹ​ማን ሁኑ።


ክፋ​ተ​ኞች ሰዎች ከእ​ና​ንተ ዘንድ ወጥ​ተው፦ ሄደን የማ​ታ​ው​ቋ​ቸ​ውን ሌሎች አማ​ል​ክት እና​ም​ልክ ብለው የከ​ተ​ማ​ቸ​ውን ሰዎች አሳቱ ሲሉ ወሬ ብት​ሰማ፥


የማይታዘዙና ከንቱ የሚናገሩ የሚያታልሉ ይልቁንም ከተገረዙት ወገን የሚሆኑ ብዙ ናቸውና፤


መም​ህ​ራን ልት​ሆኑ ሲገ​ባ​ችሁ፥ ካመ​ና​ችሁ ጀምሮ በት​ም​ህ​ርት ላይ የቈ​ያ​ችሁ ስለ ሆነ፥ እስከ ዛሬም ገና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የቃ​ሉን መጀ​መ​ሪያ ትም​ህ​ርት ሊያ​ስ​ተ​ም​ሩ​አ​ችሁ ትወ​ዳ​ላ​ችሁ፤ ወተ​ት​ንም ሊግ​ቱ​አ​ችሁ ትሻ​ላ​ችሁ፤ ጽኑ ምግ​ብ​ንም አይ​ደ​ለም።


ዮፍ​ታ​ሔም ከወ​ን​ድ​ሞቹ ፊት ሸሽቶ በጦብ ምድር ተቀ​መጠ፤ ድሆች ሰዎ​ችም ተሰ​ብ​ስ​በው ዮፍ​ታ​ሔን ተከ​ተ​ሉት።


ከበ​ዓ​ልም ቤት ሰባ ብር ሰጡት፤ በዚ​ያም አቤ​ሜ​ሌክ ወን​በ​ዴ​ዎ​ች​ንና አስ​ደ​ን​ጋ​ጮ​ችን ቀጠ​ረ​በት፤ እነ​ር​ሱም ተከ​ት​ለ​ውት ሄዱ።


የተ​ጨ​ነ​ቀም ሁሉ፥ ዕዳም ያለ​በት ሁሉ፥ የተ​ከ​ፋም ሁሉ ወደ እርሱ ተሰ​ባ​ሰበ፤ እር​ሱም በላ​ያ​ቸው አለቃ ሆነ፤ ከእ​ር​ሱም ጋር አራት መቶ የሚ​ያ​ህሉ ሰዎች ነበሩ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos