2 ነገሥት 8:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እስኪያፍርም ድረስ ትኩር ብሎ ፊቱን ተመለከተው፤ የእግዚአብሔርም ሰው አለቀሰ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እስኪያፍር ድረስም፣ አዛሄልን ትኵር ብሎ ተመለከተው፤ ከዚያም የእግዚአብሔር ሰው እንባውን አፈሰሰ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚህ በኋላ ኤልሳዕ ፊቱን በማጥቆር በሚያስፈራ ሁኔታ አዛሄልን ተመለከተው፤ ከዚህም የተነሣ አዛሄል ተጨነቀ፤ ወዲያውም ኤልሳዕ እንባውን ማፍሰስ ጀመረ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ኤልሳዕ ፊቱን በማጥቈር በሚያስፈራ ሁኔታ አዛሄልን ተመለከተው፤ ከዚህም የተነሣ አዛሄል ተጨነቀ፤ ወዲያውም ኤልሳዕ እንባውን ማፍሰስ ጀመረ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እስኪያፍርም ድረስ ትኵር ብሎ ተመለከተው፤ የእግዚአብሔርም ሰው አነባ። |
በእስራኤልም ንጉሥ በፋቁሔ ዘመን የአሶር ንጉሥ ቴልጌልቴልፌልሶር መጣ፤ ኢዮንና አቤልቤትመዓካን፥ ያኖዋንም፥ ቃዴስንና አሶርንም፥ ገለዓድንና ገሊላንም፥ የንፍታሌምንም ሀገር ሁሉ ወሰደ፤ ወደ አሶርም አፈለሳቸው።
ይህን ባትሰሙ ነፍሴ ስለ ትዕቢታችሁ በስውር ታለቅሳለች፤ የእግዚአብሔርም መንጋ ተሰብሮአልና ዐይኔ ታነባለች፤ እንባንም ታፈስሳለች።
“እንደዚህም ብለህ ትነግራቸዋለህ፦ የወገኔ ልጅ ድንግሊቱ በታላቅ ስብራትና እጅግ ክፉ በሆነ ቍስል ተሰብራለችና ዐይኖቻችሁ ሌሊትና ቀን ሳያቋርጡ እንባን ያፍስሱ።
አንጀቴ! አንጀቴ! ልቤ በጣም ታምሞአል፤ ነፍሴም አእምሮዋን አጥታለች፤ በውስጤም ልቤ ታውኮብኛል፤ ነፍሴም የመለከትን ድምፅና የሰልፍን ውካታ ሰምታለችና ዝም እል ዘንድ አልችልም።
እግዚአብሔርን እያገለገልሁ በፍጹም መከራና በልቅሶ ከአይሁድም ሴራ የተነሣ በደረሰብኝ ፈተና እየተጋደልሁ፥
ዘወትር እንደምነግራችሁ፥ ልዩ አካሄድ የሚሄዱ ብዙዎች አሉና፤ አሁንም እነርሱ የክርስቶስ የመስቀሉ ጠላቶች እንደ ሆኑ በግልጥ እያለቀስሁ እነግራችኋለሁ።