ደሴቶች ሆይ፥ ወደ እኔ ተመለሱ፤ እግዚአብሔር ግን እስራኤልን በዘለዓለማዊ መድኀኒት ያድነዋል፤ እናንተም ለዘለዓለም አታፍሩምና አቷረዱም።”
2 ቆሮንቶስ 5:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሁንም በክርስቶስ የሆነው ሁሉ አዲስ ፍጥረት ነው፤ የቀደመውም አለፈ፤ እነሆ ሁሉም አዲስ ሆነ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው፤ አሮጌው ነገር ዐልፏል፤ እነሆ፤ አዲስ ሆኗል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው፤ አሮጌው ነገር አልፎአል፤ እነሆ፥ ሁሉም አዲስ ሆኖአል! አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ማንም ሰው የክርስቶስ ወገን ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው፤ አሮጌው ፍጥረት አልፎአል፤ በእርሱም ስፍራ አዲስ ፍጥረት ተተክቶአል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው፤ አሮጌው ነገር አልፎአል፤ እነሆ፥ ሁሉም አዲስ ሆኖአል። |
ደሴቶች ሆይ፥ ወደ እኔ ተመለሱ፤ እግዚአብሔር ግን እስራኤልን በዘለዓለማዊ መድኀኒት ያድነዋል፤ እናንተም ለዘለዓለም አታፍሩምና አቷረዱም።”
ሌላ ልብ እሰጣቸዋለሁ፤ በውስጣቸውም አዲስ መንፈስ አሳድራለሁ፤ ከሥጋቸውም ውስጥ የድንጋዩን ልብ አወጣለሁ፤ የሥጋንም ልብ እሰጣቸዋለሁ፤
የበደላችሁትን በደል ሁሉ ከእናንተ ጣሉ፤ አዲስ ልብና አዲስ መንፈስንም ለእናንተ አድርጉ፤ የእስራኤል ቤት ሆይ! ስለ ምን ትሞታላችሁ?
አዲስ ልብንም እሰጣችኋለሁ፤ አዲስ መንፈስንም በውስጣችሁ አኖራለሁ፤ የድንጋዩንም ልብ ከሥጋችሁ አወጣለሁ፤ የሥጋንም ልብ እሰጣችኋለሁ።
በእኔ ያለውን፥ ፍሬ የማያፈራውን ቅርንጫፍም ሁሉ ያስወግደዋል፤ የሚያፈራውን ቅርንጫፍ ሁሉ ግን በብዙ እንዲያፈራ ያጠራዋል።
እኔ የወይን ግንድ ነኝ፤ ቅርንጫፎቹም እናንተ ናችሁ፤ በእኔ የሚኖር እኔም በእርሱ፥ ብዙ ፍሬ የሚያፈራ እርሱ ነው፤ ያለ እኔ ምንም ማድረግ አትችሉምና።
እኔ በእነርሱ እኖራለሁ፤ አንተም በእኔ፤ በአንድ ፍጹማን ይሆኑ ዘንድ፤ አንተም እንደ ላክኸኝና እንደ ወደድኸኝ እኔም እነርሱን እንደ ወደድኋቸው።
ጌታችን ኢየሱስም መልሶ፥ “እውነት እውነት እልሀለሁ፤ ዳግመኛ ያልተወለደ ሰው የእግዚአብሔርን መንግሥት ለማየት አይችልም” አለው።
ጌታችን ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው፥ “እውነት እውነት እልሀለሁ፤ ዳግመኛ ከውኃና ከመንፈስ ቅዱስ ያልተወለደ ሰው ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም።
ከዘመዶች ወገን የሚሆን ሄሮድዮናን ሰላም በሉ፤ በንርቃሶስ ቤት ያሉትንና በክርስቶስ ያመኑትን ምእመናን ሰላም በሉ።
ከዘመዶች ወገን የሚሆኑትን ከእኔ ጋር ያመኑ እንድራናቆስንና ዩልያንን ሰላም በሉ፤ ቀደም ሲል ክርስቶስን እንደ አገለገሉ ሐዋርያት ያውቁአቸዋል።
አሁን ግን ታስረንበት ከነበረው ከኦሪት ሕግ ነፃ ወጥተናል፤ ስለዚህ በብሉይ መጽሐፍ ሳይሆን በአዲሱ መንፈሳዊ ሕይወት እንገዛለን።
እናንተም በኢየሱስ ክርስቶስ ከእርሱ ናችሁ፤ በእርሱም ከእግዚአብሔር ጥበብንና ጽድቅን፥ ቅድስናንና ቤዛነትን አገኘን።
እኔ ልጅ በነበርሁ ጊዜ እንደ ልጅ እናገር ነበር፤ እንደ ልጅም አስብ ነበር፤ እንደ ልጅም እመክር ነበር፤ በአደግሁ ጊዜ ግን የልጅነትን ጠባይ ሁሉ ሻርሁ።
በክርስቶስ ያመነ አንድ ሰው አውቃለሁ፤ ዘመኑ ከዐሥራ አራት ዓመት በፊት ነው፤ ነገር ግን በሥጋው ይሁን በነፍሱ እንጃ፥ እግዚአብሔር ያውቃል፤ ያን ሰው እስከ ሦስተኛው ሰማይ ድረስ ነጥቀው ወሰዱት።
ስለዚህ ከአሁን ጀምሮ በሥጋ የምናውቀው የለም፤ ክርስቶስንም በሥጋ ብናውቀው አሁን ግን ከእንግዲህ ወዲህ የምናውቀው አይደለም።
ኀጢአታቸውን ይቅር ብሎ በደላቸውንም ሳያስብ እግዚአብሔር በክርስቶስ ዓለሙን ከራሱ ጋር አስታርቆአልና፤ የዕርቅ ቃሉንም በእኛ ላይ አደረገ፤ የይቅርታውንም መልእክት ሰጠን።
በዚህም አይሁዳዊ፥ ወይም አረማዊ የለም፤ ገዢ፥ ወይም ተገዢ የለም፤ ወንድ፥ ወይም ሴት የለም፤ ሁላችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ አንድ ናችሁና።
በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ በፍቅር የምትሠራ እምነት እንጂ መገዘር አይጠቅምምና፤ አለመገዘርም ግዳጅ አይፈጽምምና።