Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ገላትያ 6:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ዘንድ አዲስ ፍጥ​ረት መሆን ነው እንጂ መገ​ዘር አይ​ጠ​ቅ​ምም፤ አለ​መ​ገ​ዘ​ርም ግዳጅ አይ​ፈ​ጽ​ምም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 መገረዝም ሆነ አለመገረዝ አይጠቅምም፤ የሚጠቅመው አዲስ ፍጥረት መሆን ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 አዲስ ፍጥረት መሆን እንጂ፥ መገረዝ ወይም አለመገረዝ አይጠቅምምና።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ስለዚህ መገረዝም ሆነ አለመገረዝ ምንም አይጠቅምም፤ የሚጠቅመውስ አዲስ ፍጥረት መሆን ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 በክርስቶስ ኢየሱስ አዲስ ፍጥረት መሆን ይጠቅማል እንጂ መገረዝ ቢሆን ወይም አለመገረዝ አይጠቅምምና።

Ver Capítulo Copiar




ገላትያ 6:15
14 Referencias Cruzadas  

አንተ ሳት​ገ​ዘር ብት​ኖር፥ ኦሪ​ት​ንም ብት​ጠ​ብቅ አለ​መ​ገ​ዘ​ርህ መገ​ዘር ትሆ​ን​ል​ሃ​ለች።


በውኑ ለሰው ይም​ሰል አይ​ሁ​ዳዊ መሆን ይገ​ባ​ልን? ለሰው ፊትስ ተብሎ ይገ​ዘ​ሩ​አ​ልን?


በሞ​ቱም እን​መ​ስ​ለው ዘንድ ከእ​ርሱ ጋር በጥ​ም​ቀት ተቀ​በ​ርን፤ እርሱ ክር​ስ​ቶስ በአ​ባቱ ጌት​ነት ከሙ​ታን እንደ ተነሣ እኛም እንደ እርሱ በሐ​ዲስ ሕይ​ወት እን​ኖ​ራ​ለን።


እን​ግ​ዲህ በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ላሉት በመ​ን​ፈስ እንጂ በሥጋ ለማ​ይ​መ​ላ​ለሱ ፍርድ የለ​ባ​ቸ​ውም።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛዝ መጠ​በቅ ነው እንጂ መገ​ዘ​ርም አይ​ጠ​ቅ​ምም፤ አለ​መ​ገ​ዘ​ርም አይ​ጎ​ዳም።


አሁ​ንም በክ​ር​ስ​ቶስ የሆ​ነው ሁሉ አዲስ ፍጥ​ረት ነው፤ የቀ​ደ​መ​ውም አለፈ፤ እነሆ ሁሉም አዲስ ሆነ።


በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ዘንድ በፍ​ቅር የም​ት​ሠራ እም​ነት እንጂ መገ​ዘር አይ​ጠ​ቅ​ም​ምና፤ አለ​መ​ገ​ዘ​ርም ግዳጅ አይ​ፈ​ጽ​ም​ምና።


እን​መ​ላ​ለ​ስ​በት ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አስ​ቀ​ድሞ ላዘ​ጋ​ጀው በጎ ሥራ በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ የፈ​ጠ​ረን ፍጥ​ረቱ ነንና።


ሁለ​ቱ​ንም አድሶ አንድ ያደ​ር​ጋ​ቸው ዘንድ በሥ​ር​ዐቱ የት​እ​ዛ​ዝን ሕግ አጠፋ፤ ዕር​ቅ​ንም አደ​ረገ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ው​ነት፥ በቅ​ን​ነ​ትና በን​ጽ​ሕና ያደ​ሰ​ውን አዲ​ሱን ሰው​ነት ልበ​ሱት።


ግዙ​ራ​ንስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በመ​ን​ፈስ የም​ና​ገ​ለ​ግ​ለ​ውና የም​ና​መ​ል​ከው እኛ ነን፤ እኛም በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ እን​መ​ካ​ለን እንጂ በሥ​ጋ​ችን የም​ን​መካ አይ​ደ​ለም።


ነገር ግን ከግ​ብፅ ከወጡ በኋላ በመ​ን​ገድ፥ በም​ድረ በዳ የተ​ወ​ለዱ ሕዝብ ሁሉ አል​ተ​ገ​ረ​ዙም ነበ​ርና፥ ኢያሱ እነ​ዚ​ህን ሁሉ ገረ​ዛ​ቸው።


በዙፋንም የተቀመጠው “እነሆ ሁሉን አዲስ አደርጋለሁ፤” አለ። ለእኔም “እነዚህ ቃሎች የታመኑና እውነተኛዎች ናቸውና ጻፍ፤” አለኝ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos