Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኤፌሶን 2:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ሁለ​ቱ​ንም አድሶ አንድ ያደ​ር​ጋ​ቸው ዘንድ በሥ​ር​ዐቱ የት​እ​ዛ​ዝን ሕግ አጠፋ፤ ዕር​ቅ​ንም አደ​ረገ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ሕግንም፣ ከትእዛዞቹና ከሥርዐቱ ጋራ በሥጋው ሻረ። ዐላማውም ከሁለቱ አንድን አዲስ ሰው በራሱ ፈጥሮ ሰላምን ለማድረግ ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ሕግን ከትእዛዛቱና ከሥርዓቱ ጋር ሻረ፤ ከሁለቱ አንድ አዲስ ሕዝብ ፈጥሮ ሰላምን አደረገ፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ከሁለቱ ሕዝቦች ከእርሱ ጋር የሚተባበር አንድ አዲስ ሕዝብን ለመፍጠር የሕግን ትእዛዞችና ደንቦች በሥጋው ሽሮ ሰላምን አደረገ።

Ver Capítulo Copiar




ኤፌሶን 2:15
21 Referencias Cruzadas  

ከባ​ላ​ጋ​ራ​ችን የተ​ነሣ በት​እ​ዛዝ የተ​ጻ​ፈ​ውን የዕ​ዳ​ች​ንን ደብ​ዳቤ ደመ​ሰ​ሰ​ልን፤ ከመ​ካ​ከ​ላ​ች​ንም አራ​ቀው፤ በመ​ስ​ቀ​ሉም ቸነ​ከ​ረው።


በኦ​ሪት ሕግ ያሉ ሁሉ በእ​ር​ግ​ማን ውስጥ ይኖ​ራሉ፤ መጽ​ሐፍ እን​ዲህ ብሎ​አ​ልና፥ “በዚህ በኦ​ሪት መጽ​ሐፍ ውስጥ የተ​ጻ​ፈ​ውን ሁሉ የማ​ይ​ፈ​ጽ​ምና የማ​ይ​ጠ​ብቅ ርጉም ይሁን።”


አዲስ ትእ​ዛዝ በማ​ለቱ የቀ​ደ​መ​ች​ቱን አስ​ረ​ጃት፤ አሮ​ጌና ውራጅ የሆ​ነ​ውስ ለጥ​ፋት የቀ​ረበ ነው።


ፈጣ​ሪ​ውን ለመ​ም​ሰል በዕ​ው​ቀት የሚ​ታ​ደ​ሰ​ውን አዲ​ሱን ሰው ልበ​ሱት።


ከዚህ ዓለም ኑሮ ከክ​ር​ስ​ቶስ ጋር ከሞ​ታ​ችሁ እን​ደ​ገና በዓ​ለም እን​ደ​ሚ​ኖሩ ሰዎች እን​ዴት ትሠ​ራ​ላ​ችሁ?


በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ዘንድ አዲስ ፍጥ​ረት መሆን ነው እንጂ መገ​ዘር አይ​ጠ​ቅ​ምም፤ አለ​መ​ገ​ዘ​ርም ግዳጅ አይ​ፈ​ጽ​ምም።


በዚ​ህም አይ​ሁ​ዳዊ፥ ወይም አረ​ማዊ የለም፤ ገዢ፥ ወይም ተገዢ የለም፤ ወንድ፥ ወይም ሴት የለም፤ ሁላ​ችሁ በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ አንድ ናች​ሁና።


ከእ​ርሱ የተ​ነሣ አካል ሁሉ እያ​ን​ዳ​ንዱ ክፍል በልክ እን​ደ​ሚ​ሠራ፥ በተ​ሰ​ጠው በሥር ሁሉ እየ​ተ​ጋ​ጠ​መና እየ​ተ​ያ​ያዘ፥ ራሱን በፍ​ቅር ለማ​ነጽ አካ​ሉን ያሳ​ድ​ጋል።


አሁ​ንም በክ​ር​ስ​ቶስ የሆ​ነው ሁሉ አዲስ ፍጥ​ረት ነው፤ የቀ​ደ​መ​ውም አለፈ፤ እነሆ ሁሉም አዲስ ሆነ።


ይኸ​ውም በማ​ያ​ልፍ ሕይ​ወት ኀይል እንጂ ለሥ​ጋና ለደም በተ​ሠራ ሕግ አይ​ደ​ለም።


በሰ​ማይ ባለው አም​ሳል የተ​ሠ​ራው ይህ ሥራ፥ በዚህ ደም የሚ​ነጻ ከሆነ፥ ይህ ሰማ​ያዊ መሥ​ዋ​ዕ​ትስ ከዚህ ይበ​ል​ጣል።


ሕፃን ተወ​ል​ዶ​ል​ና​ልና፥ ወንድ ልጅም ተሰ​ጥ​ቶ​ና​ልና፤ አለ​ቅ​ነ​ትም በጫ​ን​ቃው ላይ ይሆ​ናል፤ ስሙም ድንቅ መካር፥ ኀያል አም​ላክ፥ የዘ​ለ​ዓ​ለም አባት፥ የሰ​ላም አለቃ ተብሎ ይጠ​ራል፤


እን​መ​ላ​ለ​ስ​በት ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አስ​ቀ​ድሞ ላዘ​ጋ​ጀው በጎ ሥራ በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ የፈ​ጠ​ረን ፍጥ​ረቱ ነንና።


ሁለ​ቱን አንድ ያደ​ረገ ሰላ​ማ​ችን እርሱ ነውና፥ በሥ​ጋ​ውም በመ​ካ​ከል የነ​በ​ረ​ውን የጥል ግድ​ግዳ አፍ​ርሶ ጥልን ሻረ።


በመ​ስ​ቀ​ሉም በአ​ንድ ሥጋው ሁለ​ቱን ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አቀ​ረ​ባ​ቸው፤ በእ​ር​ሱም ጥልን አጠፋ።


በእ​ርሱ ዘንድ አይ​ሁ​ዳዊ፥ ግሪ​ካ​ዊም፥ የተ​ገ​ዘረ፥ ያል​ተ​ገ​ዘ​ረም፥ አረ​መ​ኔም፥ ባላ​ገ​ርም፥ ቤተ ሰብ​እና አሳ​ዳሪ ማለት የለም ነገር ግን ክር​ስ​ቶስ ለሁሉ በሁ​ሉም ዘንድ ነው።


በአ​ንድ አካል የተ​ጠ​ራ​ች​ሁ​ለት የክ​ር​ስ​ቶስ ሰላም በል​ባ​ችሁ ጸንቶ ይኑር፤ ክር​ስ​ቶ​ስ​ንም በማ​መ​ስ​ገን ኑሩ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios