ሕዝቡም ሁሉ ያን ባዩ ጊዜ በግንባራቸው ተደፍተው፥ “እግዚአብሔር በእውነት እርሱ አምላክ ነው፤ እግዚአብሔር እርሱ አምላክ ነው” አሉ።
2 ዜና መዋዕል 7:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእስራኤልም ልጆች ሁሉ እሳቱ ሲወርድ የእግዚአብሔርም ክብር በቤቱ ላይ ሲሆን ያዩ ነበር፤ ድንጋይ በተነጠፈበትም ምድር በግንባራቸው ተደፍተው ሰገዱ፥ “እርሱ ቸር ነውና፥ ምሕረቱም ለዘለዓለም ነውና” እያሉ እግዚአብሔርን አመሰገኑ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እስራኤላውያንም ሁሉ እሳቱ ሲወርድ፣ የእግዚአብሔርንም ክብር ከቤተ መቅደሱ በላይ ሲያዩ፣ በመተላለፊያው ወለል ላይ ተንበረከኩ፤ በግንባራቸውም ወደ መሬት ተደፍተው ሰገዱ፤ እንዲህ እያሉም ለእግዚአብሔር ምስጋና አቀረቡ፤ “እርሱ ቸር ነውና፤ ፍቅሩም ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል።” እያሉም እግዚአብሔርን አመሰገኑ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእስራኤልም ልጆች ሁሉ እሳቱ ሲወርድ የጌታም ክብር በቤቱ ላይ ሲሆን ያዩ ነበር፤ በወለሉም ላይ በግምባራቸው ወደ ምድር ተደፍተው ሰገዱ እንዲህም ብለው ጌታን አመሰገኑ፦ “እርሱ መልካም ነውና፥ ጽኑ ፍቅሩም ለዘለዓለም ነውና።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እስራኤላውያን እሳት ከሰማይ ሲወርድና የእግዚአብሔርም ክብር በቤተ መቅደስ ላይ ማረፉን ባዩ ጊዜ በግንባራቸው ወደ መሬት ተደፍተው፦ “እግዚአብሔር ቸር ነው፤ ፍቅሩም ዘለዓለማዊ ነው!” እያሉ ሰገዱ፤ እግዚአብሔርንም አመሰገኑ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእስራኤልም ልጆች ሁሉ እሳቱ ሲወርድ የእግዚአብሔርም ክብር በቤቱ ላይ ሲሆን ያዩ ነበር፤ በወለሉም ላይ በግምባራቸው ወደ ምድር ተደፍተው ሰገዱ “እርሱ መልካም ነውና፥ ምሕረቱም ለዘላለም ነውና” ብለውም እግዚአብሔርን አመሰገኑ። |
ሕዝቡም ሁሉ ያን ባዩ ጊዜ በግንባራቸው ተደፍተው፥ “እግዚአብሔር በእውነት እርሱ አምላክ ነው፤ እግዚአብሔር እርሱ አምላክ ነው” አሉ።
ምሕረቱም ለዘለዓለም ነውና እግዚአብሔርን ያመሰግኑ ዘንድ ኤማንንና ኤዶታምን፥ በስማቸው የተጻፉትን ተመርጠው የቀሩትን ከእነርሱ ጋር አቆመ።
ዳዊትም ጉባኤውን ሁሉ፥ “አምላካችን እግዚአብሔርን አመስግኑ” አላቸው። ጉባኤውም ሁሉ የአባቶቻቸውን አምላክ እግዚአብሔርን አመሰገኑ፥ በጕልበታቸውም ተንበርክከው ለእግዚአብሔር ሰገዱ፤ ደግሞም ለንጉሡ።
ኢዮሣፍጥም በምድር ላይ ሰገደ፤ ይሁዳም ሁሉ፥ በኢየሩሳሌምም የሚኖሩ በእግዚአብሔር ፊት ወደቁ፤ ለእግዚአብሔርም ሰገዱ።
ከሕዝቡም ጋር ተማክሮ በሠራዊቱ ፊት የሚሄዱትን፥ “ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና እግዚአብሔርን አመስግኑ” የሚሉትንም፥ በቅድስና የሚያመሰግኑትን፥ ለእግዚአብሔርም የሚዘምሩትን መዘምራን አቆመ።
የሚቃጠለውም መሥዋዕት እስኪፈጸም ድረስ ጉባኤው ሁሉ ይሰግዱ ነበር፤ መዘምራኑም ይዘምሩ ነበር፤ መለከተኞችም ይነፉ ነበር።
ንጉሡ ሕዝቅያስና አለቆቹም በዳዊትና በነቢዩ በአሳፍ ቃል እግዚአብሔርን ያመሰግኑ ዘንድ ሌዋውያንን አዘዙ። በደስታም አመሰገኑ፤ አጐነበሱም፤ ሰገዱም።
መለከቱንም የሚነፉ መዘምራኑ በአንድነት ሆነው እግዚአብሔርን እያመሰገኑና እያከበሩ፥ “እግዚአብሔር ቸር ነውና፥ ምሕረቱም ለዘለዓለም ነውና እግዚአብሔርን አመስግኑ” እያሉ በአንድ ቃል ድምፃቸውን ወደ ላይ ከፍ አድርገው በመለከትና በጸናጽል፥ በዜማም ዕቃ ሁሉ እግዚአብሔርን ባመሰገኑ ጊዜ፥ የእግዚአብሔር የክብሩ ደመና የእግዚአብሔርን ቤት ሞላው።
ደግሞ፥ “ቸር ነውና፥ ለእስራኤልም ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና” እያሉ እግዚአብሔርን እያመሰገኑና እያከበሩ እርስ በርሳቸው ያስተዛዝሉ ነበር፤ የእግዚአብሔርም ቤት በተመሠረተ ጊዜ ሕዝቡ ሁሉ እግዚአብሔርን እያከበሩ በታላቅ ድምፅ ዘመሩ።
ባልንጀራውን በስውር የሚያማን እርሱን አሳደድሁ፤ በዐይኑ ትዕቢተኛ የሆነውና ልቡ የሚሳሳው ከእኔ ጋር አይተባበርም።
ሕዝቡም አመኑ፤ ደስም አላቸው፤ እግዚአብሔር የእስራኤልን ልጆች ጐብኝቶአልና፤ ጭንቀታቸውንም አይቶአልና፤ ሕዝቡም ራሳቸውን ዝቅ አድርገው ሰገዱ።
በስጦታው ሁሉ የእግዚአብሔርን ቸርነትና የእግዚአብሔርን ምስጋና ዐሰብሁ፤ እግዚአብሔር ለእስራኤል ወገኖች እውነተኛ ፈራጅ ነው፤ እንደ ቸርነቱና እንደ ጽድቁ ብዛትም ይቅርታውን ያመጣልናል።
የሐሤት ድምፅና የደስታ ድምፅ፥ የወንድ ሙሽራ ድምፅና የሴት ሙሽራ ድምፅ፦ እግዚአብሔር ቸር ነውና፥ ምሕረቱም ለዘለዓለም ነውና የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርን አመስግኑ የሚሉ ሰዎች ድምፅ፥ ወደ እግዚአብሔርም ቤት የምስጋናን መሥዋዕት የሚያመጡ ሰዎች ድምፅ እንደ ገና ይሰማል። የዚያችን ምድር ምርኮኞች ቀድሞ እንደ ነበረ አድርጌ እመልሳለሁና፥” ይላል እግዚአብሔር።
እሳትም ከእግዚአብሔር ዘንድ ወጣ፤ በመሠዊያውም ላይ የሚቃጠለውን መሥዋዕት፥ ስቡንም በላ፤ ሕዝቡም ሁሉ አይተው ተደነቁ፤ በግምባራቸውም ወደቁ።
እነርሱም በግንባራቸው ወድቀው፥ “የነፍስና የሥጋ ሁሉ አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፥ አንድ ሰው ኀጢአት ቢሠራ የእግዚአብሔር ቍጣ በማኅበሩ ላይ ይሆናልን?” አሉ።