Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




2 ዜና መዋዕል 29:30 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

30 ንጉሡ ሕዝ​ቅ​ያ​ስና አለ​ቆ​ቹም በዳ​ዊ​ትና በነ​ቢዩ በአ​ሳፍ ቃል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያመ​ሰ​ግኑ ዘንድ ሌዋ​ው​ያ​ንን አዘዙ። በደ​ስ​ታም አመ​ሰ​ገኑ፤ አጐ​ነ​በ​ሱም፤ ሰገ​ዱም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

30 ንጉሥ ሕዝቅያስና ሹማምቱ፣ ሌዋውያኑ በዳዊትና በባለራእዩ በአሳፍ ቃል እግዚአብሔርን እንዲያመሰግኑ አዘዙ። እነርሱም ውዳሴውን በደስታ ዘመሩ፤ ራሳቸውንም አጐንብሰው ሰገዱ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

30 ንጉሡም ሕዝቅያስና ሹማምንቱ ሌዋውያንን በዳዊትና በባለ ራእዩ በአሳፍ ቃል ጌታን እንዲያመሰግኑ አዘዙ። በደስታም እያመሰገኑ፥ አጐነበሱም ሰገዱም።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

30 ንጉሡና የሕዝቡ መሪዎች ሁሉ በዳዊትና በነቢዩ አሳፍ የተደረሱትን የምስጋና መዝሙሮች ለእግዚአብሔር ክብር እንዲዘምሩ ሌዋውያንን አዘዙ፤ ስለዚህ ሁሉም ተንበርክከው በመስገድ ላይ ሳሉ በታላቅ ደስታ ይዘምሩ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

30 ንጉሡም ሕዝቅያስና አለቆቹ ሌዋውያንን በዳዊትና በባለ ራእዩ በአሳፍ ቃል እግዚአብሔርን ያመሰግኑ ዘንድ አዘዙ። በደስታም አመሰገኑ፤ አጎነበሱ፤ ሰገዱም።

Ver Capítulo Copiar




2 ዜና መዋዕል 29:30
19 Referencias Cruzadas  

ካህኑ ኢዮ​አ​ዳም በሙሴ ሕግ እንደ ተጻ​ፈው እንደ ዳዊት ትእ​ዛዝ በደ​ስ​ታና በመ​ዝ​ሙር ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት ያቀ​ርቡ ዘንድ ዳዊት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት የከ​ፈ​ላ​ቸ​ውን ካህ​ና​ትና ሌዋ​ው​ያን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አገ​ል​ግ​ሎት ላይ ሾመ።


በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ተገ​ኝ​ተው የነ​በሩ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች በየ​ቀኑ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እያ​መ​ሰ​ገኑ የቂ​ጣ​ውን በዓል በታ​ላቅ ደስታ ሰባት ቀን አደ​ረጉ፤ ሌዋ​ው​ያ​ኑና ካህ​ና​ቱም በዜማ ዕቃ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያመ​ሰ​ግኑ ነበር።


ጉባ​ኤው ሁሉ እንደ ገና ሰባት ቀን በዓል ያደ​ርጉ ዘንድ ተማ​ከሩ፤ በደ​ስ​ታም እንደ ገና ሰባት ቀን በዓል አደ​ረጉ።


በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ታላቅ ደስታ ሆነ፤ ከእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ ከዳ​ዊት ልጅ ከን​ጉሥ ሰሎ​ሞን ዘመን ጀምሮ እን​ደ​ዚህ ያለ በዓል በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም አል​ተ​ደ​ረ​ገም ነበር።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ሁሉ እሳቱ ሲወ​ርድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ክብር በቤቱ ላይ ሲሆን ያዩ ነበር፤ ድን​ጋይ በተ​ነ​ጠ​ፈ​በ​ትም ምድር በግ​ን​ባ​ራ​ቸው ተደ​ፍ​ተው ሰገዱ፥ “እርሱ ቸር ነውና፥ ምሕ​ረ​ቱም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና” እያሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ሰ​ገኑ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ካህ​ና​ቱና ሌዋ​ው​ያኑ፥ የቀ​ሩ​ትም የም​ር​ኮ​ኞች ልጆች የዚ​ህን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ቅዳሴ በደ​ስታ አደ​ረጉ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ደስ አሰ​ኝ​ቶ​አ​ቸ​ዋ​ልና፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም አም​ላክ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ለመ​ሥ​ራት እጃ​ቸ​ውን ያጸና ዘንድ የአ​ሦ​ርን ንጉሥ ልብ ወደ እነ​ርሱ መል​ሶ​አ​ልና የቂ​ጣ​ውን በዓል ሰባት ቀን በደ​ስታ አደ​ረጉ።


በዳ​ዊ​ትም ዘመን አሳፍ የመ​ዘ​ም​ራን አለቃ ነበር፤ እነ​ር​ሱም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በዜማ ያመ​ሰ​ግኑ ነበር።


ልባ​ቸው በመ​ከራ ደከመ፤ ታመሙ የሚ​ረ​ዳ​ቸ​ው​ንም አጡ።


እስ​ራ​ኤል በፈ​ጣ​ሪው ደስ ይለ​ዋል፥ የጽ​ዮ​ንም ልጆች በን​ጉ​ሣ​ቸው ሐሤ​ትን ያደ​ር​ጋሉ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምክር ግን ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይኖ​ራል፥ የል​ቡም ዐሳብ ለልጅ ልጅ ነው።


አቤቱ፥ እንደ ቸር​ነ​ትህ መጠን ማረኝ፤ እንደ ምሕ​ረ​ት​ህም ብዛት ኀጢ​አ​ቴን ደም​ስስ።


እም​ነ​ትና በጎ​ነት በፊቱ፥ ቅድ​ስ​ናና የክ​ብር ገና​ና​ነት በመ​ቅ​ደሱ ውስጥ ናቸው።


አንተ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ በም​ድር ላይ ሁሉ ብቻ​ህን ልዑል ነህና፥ በአ​ማ​ል​ክ​ትም ሁሉ ላይ እጅግ ከፍ ከፍ ብለ​ሃ​ልና።


ዘወ​ትር በጌ​ታ​ችን ደስ ይበ​ላ​ችሁ፤ ደግሜ እላ​ች​ኋ​ለሁ፦ ደስ ይበ​ላ​ችሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos