ላባም አለው፥ “እኛ አንዳችን ከሌላው እንለያያለንና ራእይን የገለጠልኝ እግዚአብሔር በእኔና በአንተ መካከል ሆኖ ይመልከት።
1 ሳሙኤል 7:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነርሱም ወደ መሴፋ ተሰበሰቡ፤ ውኃም ቀድተው በእግዚአብሔር ፊት በምድር ላይ አፈሰሱ፤ በዚያም ቀን ጾሙ፤ በዚያም፥ “በእግዚአብሔር ፊት በድለናል” አሉ። ሳሙኤልም በእስራኤል ልጆች ላይ በመሴፋ ፈረደ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እስራኤላውያን በምጽጳ በተሰበሰቡ ጊዜ፣ ውሃ ቀድተው በእግዚአብሔር ፊት አፈሰሱ፤ በዚያች ዕለት ጾሙ፤ በዚያም “እግዚአብሔርን በድለናል” ብለው ተናዘዙ። ሳሙኤልም በምጽጳ እስራኤልን ይፈርድ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እስራኤላውያን በምጽጳ በተሰበሰቡ ጊዜ፥ ውሃ ቀድተው በጌታ ፊት አፈሰሱ፤ በዚያች ዕለትም ጾሙ፤ በዚያም “እግዚአብሔርን በድለናል” አሉ። ሳሙኤልም በምጽጳ እስራኤልን ይፈርድ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱም በአንድነት በምጽጳ ተሰበሰቡ፤ ውሃም ቀድተው ለእግዚአብሔር መባ አድርገው በማፍሰስ በዚያን ዕለት ቀኑን ሙሉ ጾሙ፤ “እኛ እግዚአብሔርን በድለናል” ብለውም ተናዘዙ፤ ሳሙኤል በእስራኤላውያን መካከል ይፈርድ የነበረው በምጽጳ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ ምጽጵም ተሰበሰቡ፥ ውኃም ቀድተው በእግዚአብሔር ፊት አፈሰሱ፥ በዚያም ቀን ጾሙ፥ በዚያም፦ እግዚአብሔርን በድለናል አሉ። ሳሙኤልም በእስራኤል ልጆች ላይ በምጽጳ ፈረደ። |
ላባም አለው፥ “እኛ አንዳችን ከሌላው እንለያያለንና ራእይን የገለጠልኝ እግዚአብሔር በእኔና በአንተ መካከል ሆኖ ይመልከት።
ሞትን እንሞታለንና፥ በምድርም ላይ እንደ ፈሰሰና እንደማይመለስ ውኃ እንሆናለንና፥ እግዚአብሔርም ነፍስን ይወስዳል። የተጣለውንም ከእርሱ ያርቅ ዘንድ ያስባል።
በተማረኩበትም ሀገር ሆነው በልባቸው ንስሓ ቢገቡ፥ በተማረኩበትም ሀገር ሳሉ ተመልሰው፦ ኀጢአት ሠርተናል፥ በድለንማል፥ ክፉንም አድርገናል ብለው ቢለምኑህ፥
እነዚህ ሦስቱ ኀያላን የፍልስጥኤማውያንን ሰፈር ሰንጥቀው ሄዱ፥ በበሩም አጠገብ ካለችው ከቤተ ልሔም ምንጭ ውኃ ቀዱ፤ ይዘውም ለዳዊት አመጡለት። እርሱ ግን ሊጠጣ አልወደደም፥ ነገር ግን ለእግዚአብሔር አፍስሶ፦
ስለዚህ በሚያሠቃዩአቸው ሰዎች እጅ አሳልፈህ ሰጠሃቸው፤ አስጨነቋቸውም፤ በመከራቸውም ጊዜ ወደ አንተ ጮኹ፤ ከሰማይም ሰማሃቸው፤ እንደ ምሕረትህም ብዛት ታዳጊዎችን ሰጠሃቸው፤ ከሚያሠቃዩአቸውም እጅ አዳንሃቸው።
“አንተ ስታስተምረኝ እኔ የምመልሰው ምን አለኝ? ይህንስ እየሰማሁ ከእግዚአብሔር ጋር እከራከር ዘንድ እኔ ምንድን ነኝ? እጄን በአፌ ላይ ከማኖር በቀር የምመልሰው ምንድን ነው?
ከተመለስሁ በኋላ ተጸጸትሁ፤ ከተገሠጽሁም በኋላ ጭኔን ጸፋሁ፤ የብላቴንነቴንም ስድብ ተሸክሜአለሁና አፈርሁ፥ ተዋረድሁም።
እንዲህም ሆነ፤ የይሁዳ ንጉሥ የኢዮስያስ ልጅ ኢዮአቄም በነገሠ በአምስተኛው ዓመት በዘጠነኛው ወር በኢየሩሳሌም የተቀመጡ ሕዝብ ሁሉ፥ ከይሁዳም ከተሞች ወደ ኢየሩሳሌም የመጡ ሕዝብ ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት ለመጾም ዐዋጅ ነገሩ።
ካፍ። ሕፃኑና ጡት የሚጠባው በከተማዪቱ ጎዳና ላይ ሲዝሉ፥ ዐይኔ በእንባ ደከመች፤ ልቤም ታወከ፤ ስለ ወገኔ ሴት ልጅ መከራ ክብሬ በምድር ላይ ተዋረደ።
ካህናት ሆይ! ይህን ስሙ፤ የእስራኤል ቤት ሆይ! አድምጡ፤ የንጉሥ ቤት ሆይ! ልብ አድርጉ፤ ለሚመለከት ወጥመድ፥ በታቦርም ላይ የተዘረጋ አሽክላ ሆናችኋልና ፍርድ በእናንተ ላይ ነው።
“እንደ ከዱኝ፥ ቸልም እንዳሉኝ፥ በፊቴም አግድመው እንደ ሄዱ፥ ኀጢአታቸውንና፥ የአባቶቻቸውን ኀጢአት ይናዘዛሉ።
የእስራኤልም ልጆች፥ “አንተን አምላካችንን ትተን በዓሊምን አምልከናልና ኀጢአት ሠርተናል” ብለው ወደ እግዚአብሔር ጮኹ።
የእስራኤልም ልጆች እግዚአብሔርን፥ “እኛ ኀጢአትን ሠርተናል፤ አንተ በፊትህ ደስ የሚያሰኝህን አድርግብን፤ ዛሬ ግን እባክህ አድነን” አሉት።
የእግዚአብሔርም መልአክ ይህን ቃል ለእስራኤል ልጆች ሁሉ በተናገረ ጊዜ ሕዝቡ ሁሉ ድምፃቸውን አንሥተው አለቀሱ።
የእስራኤልም ልጆች ወጥተው በእግዚአብሔር ፊት እስከ ማታ ድረስ አለቀሱ፤ እግዚአብሔርንም፥ “ከወንድሞቻችን ከብንያም ልጆች ጋር ለመዋጋት ዳግመኛ እንቀርባለን?” ብለው ጠየቁ። እግዚአብሔርም “በእነርሱ ላይ ውጡ” አለ።
የእስራኤልም ልጆች ሁሉ ሕዝቡም ሁሉ ወጥተው ወደ ቤቴል መጡ፤ አለቀሱም፤ በዚያም በእግዚአብሔር ፊት ተቀመጡ፤ በዚያም ቀን እስከ ማታ ድረስ ጾሙ፤ በእግዚአብሔርም ፊት የሚቃጠል መሥዋዕትንና የደኅንነት መሥዋዕትን አቀረቡ።
የእግዚአብሔርም መንፈስ በእርሱ ላይ አደረ፤ በእስራኤልም ላይ ይፈርድ ነበር፤ ለጦርነትም ወጣ፤ እግዚአብሔርም በወንዞች መካከል ያለች የሶርያ ንጉሥ ኩሳርሳቴምን በእጁ አሳልፎ ሰጠው፤ እጁም በኩሳርሳቴም ላይ በረታች።
ሐናም መልሳ እንዲህ አለችው፥ “ጌታዬ ሆይ፥ አይደለም፤ እኔስ ወራት የባሳት ሴት ነኝ፤ ጠጅና ሌላ የሚያሰክር ነገር አልጠጣሁም፤ ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት ነፍሴን አፈሰስሁ፤
እነርሱም፦ እግዚአብሔርን ትተን በዓሊምንና ምስሎቹን በማምለካችን በድለናል፤ አሁንም ከጠላቶቻችን እጅ አድነን፤ እናመልክሃለንም” ብለው ወደ እግዚአብሔር ጮኹ ።