Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ዜና መዋዕል 20:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥም ፈራ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ሊፈ​ልግ ፊቱን አቀና፤ በይ​ሁ​ዳም ሁሉ ጾም አወጀ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ኢዮሣፍጥም እጅግ ስለ ፈራ እግዚአብሔርን ለመፈለግ ፊቱን አቀና፤ በይሁዳም ሁሉ ጾም ዐወጀ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ኢዮሣፍጥም ፈራ፥ ጌታንም ሊፈልግ ፊቱን አቀና፤ በይሁዳም ሁሉ ጾም አወጀ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ኢዮሣፍጥ እጅግ ስለ ፈራ ፈቃዱን እንዲገልጥለት ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፤ ከዚህ በኋላ በመላው አገሪቱ ሕዝቡ ሁሉ እንዲጾም ትእዛዝ አስተላለፈ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ኢዮሳፍጥም ፈራ፤ እግዚአብሔርንም ሊፈልግ ፊቱን አቀና፤ በይሁዳም ሁሉ ጾም አወጀ።

Ver Capítulo Copiar




2 ዜና መዋዕል 20:3
20 Referencias Cruzadas  

ደግ​ሞም ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው አም​ላክ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይሠዉ ዘንድ ከእ​ስ​ራ​ኤል ነገድ ሁሉ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ለመ​ፈ​ለግ ልባ​ቸ​ውን የሰጡ ሁሉ እነ​ር​ሱን ተከ​ት​ለው ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም መጡ።


ነገር ግን የማ​ም​ለ​ኪያ ዐፀ​ዶ​ችን ከም​ድረ ይሁዳ አስ​ወ​ግ​ደ​ሃ​ልና፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ትፈ​ልግ ዘንድ ልብ​ህን አዘ​ጋ​ጅ​ተ​ሃ​ልና መል​ካም ነገር ተገ​ኝ​ቶ​ብ​ሃል” አለው።


በስሜ የተ​ጠ​ሩት ሕዝቤ ሰው​ነ​ታ​ቸ​ውን አዋ​ር​ደው ቢጸ​ልዩ፥ ፊቴ​ንም ቢፈ​ልጉ፥ ከክፉ መን​ገ​ዳ​ቸ​ውም ቢመ​ለሱ፥ በሰ​ማይ ሆኜ እሰ​ማ​ለሁ፥ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ው​ንም ይቅር እላ​ለሁ፤ ምድ​ራ​ቸ​ው​ንም እፈ​ው​ሳ​ለሁ።


በዚ​ህም ወር በሃያ አራ​ተ​ኛው ቀን የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ጾመው፥ ማቅም ለብ​ሰው፥ በራ​ሳ​ቸ​ውም ላይ ትቢያ ነስ​ን​ሰው ተሰ​በ​ሰቡ።


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ የይ​ሁዳ ንጉሥ የኢ​ዮ​ስ​ያስ ልጅ ኢዮ​አ​ቄም በነ​ገሠ በአ​ም​ስ​ተ​ኛው ዓመት በዘ​ጠ​ነ​ኛው ወር በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም የተ​ቀ​መጡ ሕዝብ ሁሉ፥ ከይ​ሁ​ዳም ከተ​ሞች ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም የመጡ ሕዝብ ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ለመ​ጾም ዐዋጅ ነገሩ።


ጾምን ቀድሱ፤ ምህ​ላ​ንም ዐውጁ፤ ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ቹ​ንና በም​ድር የሚ​ኖ​ሩ​ትን ሁሉ ወደ አም​ላ​ካ​ችን ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ሰብ​ስቡ፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በአ​ን​ድ​ነት ጩኹ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለእ​ስ​ራ​ኤል ቤት እን​ዲህ ይላ​ልና፥ “እኔን ፈልጉ፤ በሕ​ይ​ወ​ትም ትኖ​ራ​ላ​ችሁ፤


ሰዎ​ቹም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እጅግ ፈሩ፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መሥ​ዋ​ዕት አቀ​ረቡ፤ ስእ​ለ​ት​ንም ተሳሉ።


ሥጋንም የሚገድሉትን ነፍስን ግን መግደል የማይቻላቸውን አትፍሩ፤ ይልቅስ ነፍስንም ሥጋንም በገሃነም ሊያጠፋ የሚቻለውን ፍሩ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ሁሉ ሕዝ​ቡም ሁሉ ወጥ​ተው ወደ ቤቴል መጡ፤ አለ​ቀ​ሱም፤ በዚ​ያም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ተቀ​መጡ፤ በዚ​ያም ቀን እስከ ማታ ድረስ ጾሙ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕ​ት​ንና የደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕ​ትን አቀ​ረቡ።


እነ​ር​ሱም ወደ መሴፋ ተሰ​በ​ሰቡ፤ ውኃም ቀድ​ተው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በም​ድር ላይ አፈ​ሰሱ፤ በዚ​ያም ቀን ጾሙ፤ በዚ​ያም፥ “በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በድ​ለ​ናል” አሉ። ሳሙ​ኤ​ልም በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ላይ በመ​ሴፋ ፈረደ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos