እነርሱም አሉት፥ “እኛ የጠላንህ አይደለም፤ በመልካም አኑረን፥ በመልካም አሰናበትንህ እንጂ፥ አሁንም አንተ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር ቡሩክ ነህ።
1 ሳሙኤል 11:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዲህም ሆነ፤ ከአንድ ወር በኋላ አሞናዊው ናዖስ መጣ፤ በኢያቢስ ገለዓድም ሰፈረ፤ የኢያቢስም ሰዎች ሁሉ፥ “አሞናዊውን ናዖስን ቃል ኪዳን አድርግልን፤ እኛም እንገዛልሃለን” አሉት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አሞናዊው ናዖስ ወጥቶ ኢያቢስ ገለዓድን ከበባት፤ የኢያቢስም ሰዎች ሁሉ፣ “ከእኛ ጋራ ቃል ኪዳን አድርግ፣ እኛም እንገዛልሃለን” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሞናዊው ናዖስ ወጥቶ ያቢሽ ገለዓድን ከበባት፤ የያቢሽም ሰዎች ሁሉ ናዖስን፥ “ከእኛ ጋር ቃል ኪዳን አድርግ፥ እኛም እንገዛልሃለን” አሉት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከአንድ ወር በኋላ የዐሞን ንጉሥ ናዖስ በገለዓድ ግዛት በምትገኘው በያቤሽ ከተማ ላይ ሠራዊቱን በማዝመት ከበባት፤ የያቤሽም ሰዎች ናዖስን “ከእኛ ጋር የውል ስምምነት አድርግ፤ እኛም የአንተ አገልጋዮች እንሆናለን” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲህም ሆነ፥ ከአንድ ወር በኋላ አሞናዊው ናዖስ ወጣ፥ በኢያቢስ ገለዓድም ሰፈረ፥ የኢያቢስም ሰዎች ሁሉ፦ ቃል ኪዳን አድርግልን፥ እኛም እንገዛልሃለን አሉት። |
እነርሱም አሉት፥ “እኛ የጠላንህ አይደለም፤ በመልካም አኑረን፥ በመልካም አሰናበትንህ እንጂ፥ አሁንም አንተ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር ቡሩክ ነህ።
ዳዊትም፥ “አባቱ ቸርነትን እንዳደረገልኝ እኔ ለናዖስ ልጅ ለሐኖን ቸርነት አደርጋለሁ” አለ። ዳዊትም ስለ አባቱ ያጽናኑት ዘንድ ብላቴኖቹን ላከ፤ የዳዊትም ብላቴኖች ወደ አሞን ልጆች ሀገር መጡ።
ዳዊትም ወደ ምናሄም በመጣ ጊዜ በአሞን ልጆች ሀገር በአራቦት የነበረ የነዓሶን ልጅ ኡኤሴብ፥ የሎዶባርም ሰው የአሜሄል ልጅ ማኪር፥ የሮጌሌምም ሰው ገለዓዳዊው ቤርዜሊ፥
ዳዊትም ወደ ኢያቢስ ገለዓድ ገዦች መልእክተኞችን ላከ፤ ዳዊትም እንዲህ አላቸው፥ “እናንተ እግዚአብሔር ለቀባው ለጌታችሁ ለሳኦል ይህን ቸርነት አድርጋችኋልና፥ እርሱንና ልጁን ዮናታንንም ቀብራችኋቸዋልና በእግዚአብሔር የተባረካችሁ ሁኑ።
ጽኑዓን ሰዎች ሁሉ ከገለዐድ ተነሥተው የሳኦልን ሬሳ የልጆቹንም ሬሳዎች ወሰዱ፥ ወደ ኢያቢስም አመጡአቸው፤ በኢያቢስም ካለው ከትልቁ ዛፍ በታች አጥንቶቻቸውን ቀበሩ፥ ሰባት ቀንም ጾሙ።
ሕዝቅያስንም አትስሙ፤ የአሦር ንጉሥ እንዲህ ይላል፦ በሕይወት ልትኖሩ ብትወድዱ ሁላችሁ ወደ እኔ ውጡ፤ እያንዳንዳችሁም ከወይናችሁና ከበለሳችሁ ትበላላችሁ፤ ከጕድጓዳችሁም ውኃ ትጠጣላችሁ፤
በሞዓብና በአሞንም ልጆች መካከል፥ በኤዶምያስም፥ በምድርም ሁሉ ላይ የነበሩ አይሁድ ሁሉ የባቢሎን ንጉሥ የይሁዳን ቅሬታ እንዳስቀረ፥ የሳፋንንም ልጅ የአኪቃምን ልጅ ጎዶልያስን በላያቸው እንደ ሾመው ሰሙ።
“የአሞን ልጆች ንጉሥ በኣሊስ ይገድልህ ዘንድ የናታንያን ልጅ እስማኤልን እንደ ላከ ታውቃለህን?” አሉት። የአኪቃም ልጅ ጎዶልያስ ግን አላመናቸውም።
“አሞናዊ ወይም ሞዓባዊ ወደ እግዚአብሔር ቤት አይግባ፤ እስከ ዐሥር ትውልድ ድረስ ለዘለዓለም ወደ እግዚአብሔር ቤት አይግባ።
እነርሱም፥ “ከእስራኤል ነገድ ወደ እግዚአብሔር ወደ መሴፋ ያልወጣ ማን ነው?” አሉ። እነሆም፥ ከኢያቢስ ገለዓድ ወደ ሰፈሩ ወደ ጉባኤው ማንም አልወጣም ነበር።
የአሞንም ልጆች ንጉሥ ናዖስ እንደ መጣባችሁ ባያችሁ ጊዜ፥ አምላካችሁ እግዚአብሔር ንጉሣችሁ ሳለ፦ እንዲህ አይሁን፤ ነገር ግን ንጉሥ አንግሥልን አላችሁኝ።
ሳኦልም መንግሥቱን በእስራኤል ላይ አጸና፤ በዙሪያውም ካሉት ከጠላቶቹ ሁሉ ጋር፥ ከሞዓብም፥ ከአሞንም ልጆች፥ ከኤዶምያስም፥ ከቢዖርም፥ ከሱባም ነገሥታት፥ ከፍልስጥኤማውያንም ሁሉ ጋር ይዋጋ ነበር፤ በየሄደበትም ሁሉ ድል ይነሣ ነበር።