Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢሳይያስ 36:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ሕዝ​ቅ​ያ​ስ​ንም አት​ስሙ፤ የአ​ሦር ንጉሥ እን​ዲህ ይላል፦ በሕ​ይ​ወት ልት​ኖሩ ብት​ወ​ድዱ ሁላ​ችሁ ወደ እኔ ውጡ፤ እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ች​ሁም ከወ​ይ​ና​ች​ሁና ከበ​ለ​ሳ​ችሁ ትበ​ላ​ላ​ችሁ፤ ከጕ​ድ​ጓ​ዳ​ች​ሁም ውኃ ትጠ​ጣ​ላ​ችሁ፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 “ሕዝቅያስን አትስሙ። የአሦር ንጉሥ የሚለው ይህ ነው፤ ‘ከእኔ ጋራ ተስማሙ፤ ወደ እኔም ውጡ። ከዚያም እያንዳንዳችሁ ከወይናችሁና ከበለሳችሁ ትበላላችሁ፤ ከጕድጓዳችሁም ውሃ ትጠጣላችሁ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ሕዝቅያስን አትስሙ፤’ የአሦር ንጉሥ እንዲህ ይላል፦ ‘ከእኔ ጋር ታረቁ ወደ እኔም ኑ፤ እያንዳንዳችሁም ከወይናችሁና ከበለሳችሁ ብሉ፥ ከጉድጓዳችሁም ውኃ ጠጡ፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ሕዝቅያስ የሚላችሁን አታዳምጡ! የአሦር ንጉሥ የሚለው ይህ ነው፦ ወደ እኔ ኑና ከእኔ ጋር ተስማምታችሁ ኑሩ፤ ይህን ብታደርጉ ሁላችሁ እያንዳንዳችሁ የወይን ተክሎቻችሁን ዘለላ የበለስ ዛፎቻችሁን ፍሬ ትበላላችሁ፤ ከጒድጓዶቻችሁም ውሃ ትጠጣላችሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ሕዝቅያስንም አትስሙ፥ የአሦር ንጉሥ እንዲህ ይላል፦ ከእኔ ጋር ታረቁ ወደ እኔም ውጡ፥ እያንዳንዳችሁም ከወይናችሁና ከበለሳችሁ ብሉ፥ ከጕድጓዳችሁም ውኃ ጠጡ፥

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 36:16
16 Referencias Cruzadas  

እን​ዲ​ህም በሉ፦ እነሆ አገ​ል​ጋ​ይህ ያዕ​ቆብ ከኋ​ላ​ችን ነው። በፊቴ በሚ​ሄ​ደው እጅ መንሻ እታ​ረ​ቀ​ዋ​ለሁ፤ ከዚ​ያም በኋላ ምና​ል​ባት ይራ​ራ​ል​ኛል፤ ፊቱ​ንም አያ​ለሁ ብሎ​አ​ልና።”


ከወ​ደ​ድ​ኸ​ኝስ ይህ​ችን ያመ​ጣ​ሁ​ል​ህን በረ​ከ​ቴን ተቀ​በል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ራር​ቶ​ል​ኛ​ልና፥ ለእ​ኔም ብዙ አለ​ኝና።” እስ​ኪ​ቀ​በ​ለ​ውም ድረስ ግድ አለው፤ ተቀ​በ​ለ​ውም።


ዳዊ​ትም በደ​ማ​ስቆ ሶርያ ጭፍ​ሮች አኖረ፤ ሶር​ያ​ው​ያ​ንም ለዳ​ዊት ገባ​ሮች ሆኑ፤ ግብ​ርም አመ​ጡ​ለት፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ዳዊ​ትን በሄ​ደ​በት ሁሉ ጠበ​ቀው።


ይሁ​ዳና እስ​ራ​ኤ​ልም እንደ ባሕር አሸዋ ብዛት ብዙ ነበሩ፤ ይበ​ሉና ይጠ​ጡም፥ ደስም ይላ​ቸው ነበር።


በሰ​ሎ​ሞ​ንም ዘመን ሁሉ ይሁ​ዳና እስ​ራ​ኤል ከዳን ጀምሮ እስከ ቤር​ሳ​ቤህ ድረስ እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው ከወ​ይ​ኑና ከበ​ለሱ በታች ተዘ​ል​ለው ይቀ​መጡ ነበር።


ሕዝ​ቅ​ያ​ስ​ንም አት​ስሙ፤ የአ​ሶር ንጉሥ እን​ዲህ ይላል፦ ከእኔ ጋር ታረቁ፤ ወደ እኔም ውጡ፤ እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ች​ሁም ከወ​ይ​ና​ች​ሁና ከበ​ለ​ሳ​ችሁ ብሉ፤ ከጕ​ድ​ጓ​ዳ​ች​ሁም ውኃ ጠጡ፤


እር​ሱም ከጭ​ፍ​ራው ሁሉ ጋር ወደ ኤል​ሳዕ ተመ​ለሰ፤ ወደ እር​ሱም ደርሶ በፊቱ ቆመና፥ “እነሆ፥ በእ​ስ​ራ​ኤል ነው እንጂ በም​ድር ሁሉ አም​ላክ እን​ደ​ሌለ ዐወ​ቅሁ፤ አሁ​ንም ከአ​ገ​ል​ጋ​ይህ በረ​ከት ተቀ​በል” አለው።


ከማድጋህ ውኃ፥ ከምንጭህም የሚፈልቀውን ውኃ ጠጣ።


ይህም መጥቼ ምድ​ራ​ች​ሁን ወደ​ም​ት​መ​ስ​ለው ምድር፥ እህ​ልና የወ​ይን ጠጅ፥ እን​ጀ​ራና ወይን ወዳ​ለ​ባት ምድር እስ​ካ​ፈ​ል​ሳ​ችሁ ድረስ ነው።


የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር አፍም ተናግሮአልና ሰው እያንዳንዱ ከወይኑና ከበለሱ በታች ይቀመጣል፥ የሚያስፈራውም የለም።


በዚያ ቀን፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፥ እያንዳንዱ ከወይኑና ከበለሱ በታች ሆኖ ባልንጀራውን ይጠራል።


ስለ​ዚ​ህም አስ​ቀ​ድ​መው ወደ እና​ንተ መጥ​ተው በቅ​ድ​ሚያ የተ​ና​ገ​ራ​ች​ኋ​ትን በረ​ከ​ታ​ች​ሁን እን​ዲ​ያ​ዘ​ጋጁ ወን​ድ​ሞ​ችን ማለ​ድሁ፤ እን​ደ​ዚ​ህም የተ​ዘ​ጋጀ ይሁን፤ በረ​ከ​ትን እን​ደ​ም​ታ​ገ​ኙ​በት እንጂ በን​ጥ​ቂያ እንደ ተወ​ሰ​ደ​ባ​ችሁ አይ​ሁን።


የኢ​ያ​ቢ​ስም ሰዎች፥ “ወደ እስ​ራ​ኤል ሀገር ሁሉ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን እን​ድ​ን​ልክ ሰባት ቀን ቈይ​ልን፤ ከዚ​ያም በኋላ የሚ​ያ​ድ​ነን ባይ​ኖር ወደ አንተ እን​መ​ጣ​ለን” አሉት።


አሁ​ንም ባሪ​ያህ ወደ ጌታዬ ያመ​ጣ​ች​ውን ይህን መተ​ያያ ተቀ​በል፤ በጌ​ታ​ዬም ዘንድ ለሚ​ቆሙ ሰዎች ስጣ​ቸው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos